MAP

የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ (UNIFIL) የሊባኖስን እና የእስራኤልን ድንበር ላይ ተልእኮውን ሲፈጽም የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ (UNIFIL) የሊባኖስን እና የእስራኤልን ድንበር ላይ ተልእኮውን ሲፈጽም  

የተ. መ. የፀጥታው ምክር ቤት በደቡባዊ ሊባኖስ የነበረውን የሰላም ማስከበር ተልእኮውን ለማቆም መወሰኑ ተነገረ

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በደቡባዊ ሊባኖስ የነበረውን የሰላም ማስከበር ተልእኮ ለማቆም መወሰኑን ተከትሎ የቤይሩት ሃዋሪያዊ አስተዳደር ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ሴሳር ኢሳያን ውሳኔውን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለው ነገር እንደሚያሳስባቸው ጠቁመው፥ በሌላ በኩል በዩክሬን እና በመካከለኛው ምስራቅ 'የተከበረ ሰላም' እንዲሰፍን ያላቸውን ጽኑ ተስፋ ገልጸዋል።

   አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት፥ በዋነኛነት በዩናይትድ ስቴትስ እና በፈረንሣይ መካከል ለሁለት ሳምንታት በተደረገ ውይይት እ.አ.አ. በ 1978 ዓ.ም. የተመሰረተው በሊባኖስ የተባበሩት መንግስታት ጊዜያዊ ጦር (UNIFIL) በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል የሊባኖስን መንግስት ብቸኛ የጸጥታ ዋስትና ለማድረግ በማለም ከታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከደቡብ ሊባኖስ መውጣት እንደሚጀምር አስታውቋል።

በዚህ የአንድ ዓመት የሽግግር ወቅት ጊዜያዊ ጦሩ በመልቀቂያው ጊዜያት ከ10,000 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞቹን ደህንነት እና ድጋፍ የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት በጣሊያን የሚመራው ተልዕኮው ለሲቪሉ ማህበረሰብ ጥበቃ የማድረግ እና በሲቪል ተቋማት በኩል የሰብአዊ እርዳታን የማድረስ ኃላፊነትን ወስዶ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የውሳኔ ሃሳቡ የእስራኤል መንግስት የሊባኖስ ግዛት የሆኑትን አምስት ቦታዎች ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ድንበር ከሆነው ደቡባዊ ሰማያዊ መስመር እንዲወጣ የጠየቀ ሲሆን፥ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምንም አይነት አስተያየት እንዳልሰጠ ተነግሯል።

የተለያዩ ትርጓሜዎች
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የተላለፈው ውሳኔ ሐሙስ ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በሙሉ ድምፅ የጸደቀ ሲሆን፥ 15 ቱም አባል ሀገራት በውሳኔው ላይ ድምጽ በሰጡበት ወቅት በሙሉ ድምጽ ማሳለፋቸው ተነግሯል።

ይህ የውሳኔ ሃሳብ በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ የተደገፈ ቢሆንም ጥብቅ የነበሩ ለቆ የመውጣት የጊዜ ገደቦችን በማስቀረት ከዋናው የውሳኔ ሃሳብ ቅጂ ለዘብ ያለ መሆኑ ተነግሯል።

በተባበሩት መንግስታት ታሪክ ውስጥ እ.አ.አ. በ 1978 የተጀመረው እጅግ በጣም ረጅም ጊዜ ያለው ተልዕኮ ማብቃቱ ይፋ ሲደረግ የመጀመሪያዎቹ ዸም አቀፍ ግብረ መልሶች የተደበላለቁ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፥ በዚህም ምክንያት ይህ ውሳኔ ውጤቱ ምን እንደሚሆን እርግጠኛ ያለመሆን ስሜት መፍጠሩ እየተነገረ ይገኛል።

ተለዋዋጩ የመካከለኛው ምስራቅ አውድ
በጣሊያን ዸም አቀፍ የፖለቲካ ሳይንስ ጥናት ተቋም (ISPI) ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ክላውዲዮ በርቶሎቲ የሊባኖሱ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን በሊባኖስ የተባበሩት መንግስታት ጊዜያዊ ጦር ኦፕሬሽን ማብቂያ ላይ ያለውን አተረጓጎም በመጠኑ የመቀየሩ ሁኔታ አስደሳች እንደሆነ ገልጸው፥ በርግጥ ፕሬዚዳንት አውን ዸም አቀፉ ተቋም ተልእኮውን ዩናይትድ ስቴትስ መደበኛ ባልሆነ መንገድ እስራኤልን እንደጠየቀችው ለስድስት ወራት ብቻ ሳይሆን እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ስላራዘመው ማመስገናቸውን ገልጸዋል።

እየተፈጠረ ያለው ሁኔታ ወደፊት በርካታ ሊሆኑ የሚችሉ ውጤቶችን እንደሚያመጣ የተገመተ ሲሆን፥ ነገር ግን በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ቀጣይነት ያላቸው ለውጦች እንደሚኖሩ በግልፅ ያሳያል ተብሏል።

አቶ ክላውዲዮ በማከልም በተለይም ከሊታኒ ወንዝ በስተደቡብ የሚገኘውን ቦታ ሄዝቦላህ የጦር መሳሪያዎቹን እና ትጥቆቹን ለማከማቸት እንዳይችል ወይም ታጣቂዎቹ በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ አንዳንድ ጥቅማጥቅሞች ቢኖሩትም ዓላማውን ያላሳካ ተልዕኮ እንደነበር ገልጸዋል።

ሊባኖስን የሚተው ውሳኔ አይደለም
ለሊባኖሳዊያን ትልቁ ስጋት የዚህ ዸም አቀፍ ተቋም ከስፍራው መልቀቅ ደቡባዊ ሊባኖስን ጨለማ ውስጥ መክተት እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፥ ይሄንን ስጋት ለቫቲካን ዜና ያጋሩት የቤይሩት ሐዋርያዊ አስተዳደር ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ሴዛር ኢሳያን "ለሊባኖሳዊያን በተለይም በደቡባዊው ክልል ለሚገኙ ህዝቦች የሰላም አስከባሪ ሃይሉ መገኘት የደህንነት ማረጋገጫ ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው፥ እነዚህ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በጭንቅ ጊዜያትን እንኳን ሳይቀር ሁልጊዜም ሰዎችን ለመርዳት የሚሞክሩ ወታደሮች ናቸው ብለዋል።

ይህ የዸም አቀፍ ቡድን ከአሁን በኋላ እዚያ የማይኖር ከሆነ አደጋው በደቡባዊ ሊባኖስ ምን እየተካሄደ እንዳለ ማንም ሊያውቅ እንደማይችል የተገለጸ ሲሆን፥ ሆኖም ግን ‘የጸጥታ አስከባሪው ቡድን ተልዕኮውን ለማቆም መወሰኑ ሊባኖስን መተው ማለት ነው ብዬ አላምንም’ ካሉ በኋላ፥ “ሌላ አፍጋኒስታንን ማየት የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም” በማለት አክለዋል።

ተመራማሪው በማከልም፥ ይልቁንስ ከዩናይትድ ስቴትስ ጀምሮ ለሊባኖስ ቀጥተኛ ድጋፍ ሊደረግ እንደሚችል ገልጸው፥ የጋራ ግቡ በሊባኖስ መንግስት ላይ ስጋት ሊፈጥር የሚችለውን ወታደራዊ ድጋፍ እና አደረጃጀት ያላቸውን የፖለቲካ ቡድኖች ማዳከም እንደሆነ አስረድተዋል።

ለሰላም እና መረጋጋት ያለው ተስፋ
በዚህ መንፈስ ፈረንሳይ በፕሬዚዳንት ማክሮን፣ በፕሬዚዳንት አውን እና በሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም መካከል በተካሄደው ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው ተሳትፎዋን እያጠናከረች እንደሆነ የገለጹት አቶ ክላውዲዮ፥ ፕረዚዳንት ማክሮን ይሄንን አስመልክተው ‘በዓመቱ መጨረሻ ሁለት ጉባኤዎችን ማለትም የመጀመርያው የሀገሪቱ የሉዓላዊነት መሰረት የሆነውን የሊባኖስን ጦር ለመደገፍ፣ ሁለተኛው ደግሞ ሊባኖስን መልሶ ለማቋቋም እና ለመገንባት ዓላማ ያደረገ ጉባኤ ለማካሄድ ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለሁ’ ማለታቸውን አስታውሰዋል።

ብጹእ አቡነ ኢሳያን በመጨረሻም “በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ዸም በአውሮፓም ሆነ እዚህ በመካከለኛው ምስራቅ የሰላም መንገዶችን ታገኛለች” በማለት ያላቸውን ተስፋ ከገለጹ በኋላ፥ ስለዚህም በሊባኖስ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ አስከባሪ ቡድን ከሃገሪቷ መውጣት ማለት ለሰላም ያለውን ዝግጁነት እንደሚገልጽ እና ነገር ግን ሌላውን በማጥፋት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ትክክለኛ ሰላም መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል።

02 Sep 2025, 14:26