MAP

የ 'ናዎ ፓርትነርስ ፋውንዴሽን' በመላው ዸም አግሮ ኢኮሎጂን በዘላቂነት ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበ ዸም አቀፍ ተነሳሽነት ነው የ 'ናዎ ፓርትነርስ ፋውንዴሽን' በመላው ዸም አግሮ ኢኮሎጂን በዘላቂነት ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበ ዸም አቀፍ ተነሳሽነት ነው  (©NOW Partners Foundation)

የተፈጥሮአዊ ግብርና ሥነ ምህዳር ወይም የ ‘አግሮኤኮሎጂ’ እንቅስቃሴ የፍትህ መንገድ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ተነገረ

‘ናው ፓርትነርስ ፋውንዴሽን’ ተብሎ የሚታወቀው ተቋም በዸም ዙሪያ አግሮኤኮሎጂን ወይንም ተፈጥሮአዊ የግብርና ሥነ ምህዳርን በዘላቂነት ተግባራዊ ለማድረግ እና ከአካባቢያችን መሠረታዊ ክፍሎች ጀምሮ ከእግራችን በታች እስካለው አፈር ድረስ ምድርን ለመጠበቅ ብሎም ለመንከባከብ በቁርጠኝነት እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ተፈጥሮአዊ የግብርና ስነ-ምህዳር ወይም የአግሮኤኮሎጂ ዘርፍ ሳይንስን፣ በግብርናው መስክ ላይ ያሉ ልምዶችን እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በአንድ ላይ የሚያዋህድ እንዲሁም ለዘላቂ የምግብ ዋስትና እና የግብርና ሥርዓቶች መሻሻል የሚሰራ አጠቃላይ ዘርፍ ሲሆን፥ የዓለማችንን ሥነ ምህዳር እያናጋ ከሚገኘው የአካባቢ መራቆት እና የማይካድ የኢኮኖሚ ልዩነት ተንሰራፍቶ ባለበት በአሁኑ ወቅት የአፈርን እና የገበሬዎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚደረገው ዸም አቀፋዊ እንቅስቃሴ አዲስ ህይወት እና አዲስ ተስፋ እያመጣ እንደሆነ ይነገራል።

እንደ ማኅበራዊ ንቅናቄ፣ አግሮኤኮሎጂ የአካባቢያዊ የምግብ ሥርዓቶችን፣ አነስተኛ ገበሬዎችን እና የምግብ ሉዓላዊነትን የሚበረታታ ሲሆን፥ ከአካባቢያዊ እስከ ዸም አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ፍትሃዊነት እና ጠንካራ የምግብ ሥርዓቶችን ለማስፈን በትጋት እየሰራ የሚገኝ ዘርፍ እንደሆነ ተገልጿል።

በእርግጥ ስግብግብነት እና ኬሚካሎች ነገሮችን ወደ መጥፎ ነገር መለወጥ ከመጀመራቸው በፊት አፈር በተፈጥሮ ላይ የተመሰረተ አብዮት ከተደረገባቸው ነገሮች ግንባር ቀደሙ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን፥ ብራዚል ውስጥ ከሚገኘው የአማዞን ጫካ እስከ አንድራ ፕራዴሽ ሸለቆዎች ድረስ፣ ከዛምቢያ ሸንተረራማ ሜዳዎች እስከ ስሪላንካ መንደሮች ድረስ ገበሬዎች እና ደኖች አፈሩን እንደገና ለማልማት እና ለራሳቸው እና ለፕላኔቷ የበለጠ አስተማማኝ፣ ዘላቂ እና የበለጸገ የወደፊት ጊዜ ለመፍጠር እጅግ አስደናቂ የአግሮኢኮሎጂ ፈጠራዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ይገለፃል።

በዚህም ላይ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ የሚገኘው የናዎ ፋውንዴሽን ከ100 በላይ ዸም አቀፍ አጋሮች ያሉት ሲሆን፥ መሪዎችን እና ተቋሞቻቸውን በኢንዱስትሪ እና በግብርና፣ በፋይናንስ፣ በማህበረሰብ ግንባታ እና በመንግስታዊ አወቃቀር አወንታዊ ተፅእኖን ከኢኮኖሚ ስኬት ጋር እንዲያዋህዱ የሚያበረታታ ተቋም ሲሆን፥ ከዚህም ባለፈ በመላው ዸም ተፈጥሮአዊ የግብርና ሥነ ምህዳርን በዘላቂነት ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፋውንዴሽኑን የሚመሩት ዋልተር ሊንክ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን አዲስ የግብርና አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ገልጸው፥ ይህ እንደ ህልም ሳይሆን በመረጃ የተደገፈ እውነት መሆኑን እናሳያለን ብለዋል።

“እኛ እየሰራን ያለንበት በከፍተኛ ሁኔታ የተሻሻሉ የግብርና ሥነ ምህዳር ወይም የአግሮኢኮሎጂ ዘዴዎች ለምድራችን የተሻሉ ብቻ ሳይሆኑ የአርሶ አደሮችን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ ናቸው” ያሉት ሊቀ መንበሩ፥ እነዚህ ተለምዷዊ እና ሊለወጡ የሚችሉ ዘዴዎች አፈሩን እንደሚያድሱ፣ ብዝሃ-ህይወትን እንደሚያሳድጉ እንዲሁም ውድ እና በርካታ አሉታዊ የጎንዮሽ ጉዳቶች በሚያስከትሉ የኬሚካል እርሻ ግብአቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት እንደሚፈታ አክለው አስረድተዋል።

የቀጥተኛ ተሳትፎ አቀራረብ
የናዎ ፋውንዴሽን እየተገበረ እና እያበረታታ እንደሚገኘው ነገሮችን ወደ ነበሩበት ሁኔታ የመመለስ ህልም ሳይሆን፥ ከዚህ ይልቅ ፈጠራ የተሞላበት፣ ሳይንሳዊ፣ ከፍተኛ ምርት፣ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያለው እና የሰው ልጅን እና ተፈጥሮን ያማከለ አሰራርን እንደሚከተል ተነግሯል።

ፋውንዴሽኑ በሚያስደንቅ ሁኔታ በዸም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ ለሆኑት እና በተለያዩ ሰብሎች፣ መልክዓ ምድሮች እና የአየር ንብረቶች ውስጥ ኬሚካልን በከፍተኛ ሁኔታ ለሚጠቀመው የአንድራ ፕራዴሽ ማህበረሰብ ተኮር የተፈጥሮ እርሻ (APCNF) ለመሳሰሉ ተቋማት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ ይህ ማህበረሰብ ተኮር እርሻ በደቡባዊ የህንድ ግዛት በምትገኘው አንድራ ፕራዴሽ ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ ከአንድ ሚሊዮን ለሚበልጡ ገበሬዎች አዲስ የወደፊት ዕድል እንደከፈተ እና የገቢዎቻቸውን ብዛት እና ዓይነት በከፍተኛ ሁኔታ እነደጨመረ ተገልጿል።

እ.አ.አ. በ 2030 ዓ.ም. በአንድራ ፕራዴሽ ውስጥ ከ 65 በመቶ በላይ የሚሆኑ ገበሬዎች የተፈጥሮ እርሻን ይጠቀማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ በዚህም ምክንያት አግሮኢኮሎጂ በስፋት ከጣሊያን በሚበልጠው በዚህ የህንድ ግዛት ውስጥ አዲሱ ዋና የግብርና ዘርፍ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል ተብሏል።
ናዎ ፋውንዴሽን እና የአንድራ ፕራዴሽ የተፈጥሮ እርሻ ተቋም ስልቱን በዸም አቀፍ ደረጃ ለማላመድ እና ለመለካት ጥንካሬዎቻቸውን አጣምረው እንደሚሰሩ የተነገረ ሲሆን፥ በዚህም ወቅት ገበሬዎችን እና ማህበረሰቦችን ማዳመጥ ብሎም ከተለያዩ የተፈጥሮ ሁኔታዎች እና ሰብአዊ ባህሎች ጋር መላመድን ይጠይቃል ተብሏል።

በሁሉም መልኩ ለም መሬት ተገኝቷል 
ብራዚል የዘላቂ ልማት አርአያ ሆና እየወጣች ባለችበት በአሁኑ ወቅት የናዎ ፋውንዴሽን በሀገሪቱ ውስጥ በሁሉም መልኩ ለም መሬቶችን ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን፥ ከፋውንዴሽኑ ጋር በቅርበት የሚሰሩት የግብርና ልማት እና የቤተሰብ እርሻ ሚኒስትር ፓውሎ ቴይሴራ ለቫቲካን ዜና እንደተናገሩት ብራዚል “ለእርሻ በጣም ምቹ የሆነ ጊዜ” ላይ እንደምትገኝ ገልጸው፥ ሀገሪቷ ሀገራዊ የመኸር እቅድ ማውጣት ብቻ ሳይሆን የደን መጨፍጨፍን በእጅጉ በመቀነስ፣ የተባይ ማጥፊያ ኬሚካሎችን ለማስወገድ ደፋር ፕሮግራሞችን በማስተዋወቅ እና በአግሮ ደን ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ አነስተኛ የቤተሰብ አርሶ አደሮችን ወደ አግሮ ኢኮሎጂ እንዲሸጋገሩ ማድረጉን አብራርተዋል።

አቶ ፓውሎ እነዚህን ተነሳሽነቶች “በክልሎች እና በማህበረሰቦች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን በመግለጽ፥ ይህም የአገሬው ተወላጆች የሆኑትን ‘አፍሮ-ብራዚላዊያን’ ማህበረሰቦች እና አነስተኛ የቤተሰብ ገበሬዎች ላይ ያለውን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ እንደሆነ አስረድተዋል።

በጣም የተለያዩ ባህሎች ባሉባት ብራዚል ውስጥ ግብርና ኢኮኖሚውን እንደሚመራ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን የሚያገለግለው፣ በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ለረጅም ጊዜ ውክልና የሌላቸው እና የግብአት አቅርቦት የሌላቸው ማህበረሰቦችን እንደሚደግፍ የገለጹት አቶ ዋልተር በበኩላቸው፣ አዲሱ የግብርና ሥነ ምግባር እና አዳዲስ ፖሊሲዎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሃዋሪያዊ መልዕክታቸው በሆነው ላውዳቶ ሲ' ላይ ለጋራ ቤታችን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ ያሳሰቡንን ሃሳብ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልጸው፥ የናዎ ፋውንዴሽን ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተገበራቸው ያሉት አሰራሮች ከላውዳቶ ሲ ጋር ሙሉ በሙሉ የተጣመሩ መሆናቸውን አረጋግጠው፥ “ይህ ሁሉ ምድርን እና ማህበረሰቦቿን መፈወስ እንዲሁም የአካባቢ ኢኮኖሚዎችን እና የእርሻ ገቢዎችን በማጠናከር ላይ ወሳኝ ሚና አለው” ብለዋል።

‘ይህ ከዘንባባ ዘይትነት በላይ ነው’
ብራዚል ከፋውንዴሽኑ ጋር ያላት አጋርነት ብዙ ጉዳዮችን እንደሚያካትት የተገለጸ ሲሆን፥ በአማዞን ውስጥ ፋውንዴሽኑ የላቲን አሜሪካ ትልቁ የመዋቢያ ዕቃዎች ማምረቻ ኩባንያ ከሆነው እና ‘ናቱራ’ በተሰኘ ተቋም የተሻሻለ የዘንባባ ዘይቶችን ከሚያመርተው ድርጅት ጋር፣ የአገሪቱ ብሔራዊ የግብርና ምርምር አካል ከሆነው ኤምብራፓ (Embrapa) እና ከ100 ዓመታት በፊት በጃፓን ስደተኞች ከተመሰረተው የህብረት ስራ ማህበር ከሆነው ‘ካምታ’ ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የስነ ምህዳር ውድመት ምልክት ከሆነው ከተለመደው የዘንባባ ዘይት በተለየ ሁኔታ ‘ሳፍ ዴንዴ’ ተብሎ የሚጠራው የተሻሻለ የዘንባባ ዘይት የማምረት ሂደት አፈርን በማደስ እና የአካባቢውን ማህበረሰቦች ህይወት በማሻሻል የዘንባባ ዘይት ምርትን 40 በመቶ ይጨምራል ተብሏል።

አቶ ዋልተር እንደ ካካዎ እና አሳይ ከመሳሰሉ ሰብሎች፣ ከተለያዩ ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች ጋር በብዝሃ-ሰብል ስርዓት ውስጥ ተቀናጅቶ ጠንካራ የሥነ ምህዳራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የመቋቋም አቅም እንደሚፈጥር ገልጸው፥ እየተሰራ ያለው ሥራ ከሚነገረው በላይ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ አቶ ዋልተር የ “እሴት መጨመር” አስፈላጊነትን አጽንዖት ሰጥተው በማንሳት፥ ይህም ማለት ገበሬዎች ምግብ እንዲያመርቱ መርዳት ብቻ ሳይሆን ከመዋቢያ ንጥረ ነገሮች ወደ ጽዳት እና የታሸጉ ምርቶች ደረጃ እንዲሸጋገሩ ማድረግ እንደሆነ እና በዚህም ለብራዚል ነፃ የምግብ ፕሮግራም ለትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች ማቅረብ እንደሚያስችል አስረድተዋል።

በአንዳንድ የብራዚል ደቡባዊ ግዛቶች የአግሮኢኮሎጂ ምርቶች መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ የትምህርት ቤት ምግቦች እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ነገር ግን በአማዞን አከባቢ ውስጥ ይህ ቁጥር ወደ 15 በመቶ ዝቅ እንደሚል ጠቁመው፥ ‘ዋናው ችግር የግብርና ምርት አቅርቦት ሳይሆን ምግቦቹን በማጽዳት፣ በመቁረጥ፣ በማሸግ እና በማቅረብ እሴት የመጨመር አቅም ማነስ እንደሆነ አስረድተዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ እንዲረዳ የፋውንዴሽኑ አጋሮች ከብራዚል መንግስት እና ከሌሎች የሃገሪቱ እና ዸም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር በብራዚል እና በሌሎች ሀገራት የተለያዩ አይነት ስልጠናዎችን ለመስጠት ‘ግሎባል አካዳሚ’ የተሰኘ መርሃ ግብር በማስጀመር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የተነገረ ሲሆን፥ አቶ ዋልተር አካዳሚውን አስመልክተው እንደተናገሩት የመማር እና የፈጠራ ቦታ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ በጣም አስፈላጊ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ተግዳሮቶች እና እድሎች የሚፈታበት ተጨባጭ የሆነ የተግባር ቦታ መሆኑን አስረድተዋል።

በዓለማችን ውስጥ ከ600 ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑት አነስተኛ ገበሬዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ለህልውና የሚታገሉ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን፥ ከእነዚህም መካከል በአፈር መራቆት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መሬታቸውን ለቀው በህዝብ ብዛት ወደተጨናነቁ ከተሞች ለመፈናቀል እንደተገደዱ እና አግሮኢኮሎጂ ለእነዚህ ሁሉ ተግዳሮቶች መልስ እንደሚሰጥ ይታመናል ተብሏል።

ተቃውሞን ማሸነፍ
በእርግጥ እንደማንኛውም የፍትህ እንቅስቃሴ የአግሮኤኮሎጂ እንቅስቃሴም ከተፈጥሮ ሳይሆን ከሃገራት ፖሊሲዎች ተቃውሞ እንደሚገጥመው የሚነገር ሲሆን፥ ለዚህም ማሳያ አብዛኛው በዓለማችን ላይ የሚገኙ በኬሚካል የታገዙ የግብርና ሥራዎች ከፍተኛ ድጎማ እንደሚደረግላቸው፥ ነገር ግን ለዚህ ዘርፍ እምብዛም ድጋፍ እንደማይደረግለት ይገለፃል።

በአንዳንድ አጋጣሚዎች የምዕራባውያን አገሮች በራሳቸው ድንበር ውስጥ የተከለከሉ ፀረ ተባይ መድኃኒቶችን ወደ ደቡቡ የዓለማችን ክፍል እንደሚልኩ የሚታወቅ ሲሆን፥ የህንድ መንግስት ለኬሚካል የእርሻ ማሳዎች 27 ቢሊዮን ዶላር ድጎማ እንደሚያደርግ እና የናዎ ፋውንዴሽን የሚተገብራቸው የአግሮኤኮሎጂ ዘዴዎች የግብርና ገቢን እና የማህበራዊ-ስነ-ምህዳር ሁኔታዎችን በማሻሻል ይህንን የመንግስት የድጎማ ጫና ለመቀነስ እንደሚረዳ ተገልጿል።

በእነዚህም ተግዳሮቶች ምክንያት የናዎ ፋውንዴሽን አጋሮች በአህጉሮች እና በተለያዩ ዘርፎች መካከል ጥምረት እየፈጠሩ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፥ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማለትም ከመንግስታት፣ ከገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት፣ ከፋይናንስ ተቋማት፣ ከኩባንያዎች፣ ከሲቪክ ማህበራት እና ከሀይማኖት ማህበረሰቦች ጋር አብረው እንደሚሰሩ ተገልጿል።

የእምነት ማህበረሰቦች በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ውስጥ ባሉ አብዛኞቹ ገጠራማ አካባቢዎች በብዛት እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ዋልተር፥ በዚህም ሥፍራ በታማኝነት እደሚኖሩ፣ ፍጥረትን እና መላውን የሰው ልጅ አካል እና ነፍስን ለማገልገል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ፥ ከእንደዚህ አይነት ቁርጠኝነት እና ብቃት ካላቸው አጋሮች ጋር ለሚያደርጉት ትብብር አመስጋኝ እንደሆኑ ገልጸዋል።

ይህ ሁሉን አቀፍ እይታ ሙያዊ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዋልተር፥ ይህ ሥራ ከምግብ ዋስትናም ባለፈ ስለ ሕይወት እንደሆነ ማስታወስ እንደሚገባ ገልጸው፥ “ምድራችንን የምንንከባከብበት መንገድ እርስ በእርሳችንን እንዴት እንደምንንከባከብ ይገልፃል” በማለት አስረድተዋል።

ብራዚል የኮፕ-30 ጉባኤን ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፥ ለግብርና ምርምር ያላት ቁርጠኝነት በዸም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን ያደረጋት ሲሆን፥ የብራዚል የግብርና ልማት እና የቤተሰብ እርሻ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ፓውሎ ከናዎ ፋውንዴሽን አጋሮች ጋር ያለው ትብብር በብራዚል ውስጥ የተሻሻሉ የእርሻ አሰራሮችን ብቻ ሳይሆን በሃገራት መካከል ‘እምቅ የሆኑ የልምድ ልውውጦችን’ እንደሚጨምር ጠቁመው፥ “የምናስተምረው ብቻ ሳይሆን በርካታ የምንማረው ነገር አለ” ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በብራዚል፣ ህንድ፣ ዛምቢያ እና ስሪላንካ ያሉ ዘረፈ ብዙ ባለድርሻ አካላት በመተግበር ላይ ያሉት ፕሮግራሞች የልውውጥ እና የትብብር ምሳሌ እንደሆኑ እና ነፍስኄር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሃዋሪያዊ ደብዳቤዎቻቸው በሆኑት ላውዳቶ ሲ' እና በፍራቴሊ ቱቲ ላይ ለህይወታችን እና ለዓለማችን የበለጠ ፍትሃዊ፣ ሰብአዊ እና የትብብር አቀራረብ እንዲኖር ያቀረቡትን ጥያቄ ወደ ተግባር በማምጣት ረገድ በርካታ ሥራ እንደተሰራ ገልጸዋል።

ከዚህ አንፃር አግሮኢኮሎጂ የአሰራር ዘዴ ብቻ ሳይሆን ንቅናቄ መሆኑም ጭምር የተገለጸ ሲሆን፥ የማሻሻያ ሥራዎችን በልምምድ ሃገራዊ፣ በሲኖዶሳዊነት ደግሞ ዸም አቀፋዊ መሆን እንዳለበት እንድንገነዘብ የሚያደርገን እና ከእግራችን በታች ያለው አፈር ምድራችንን እና ቤታችንን የሚሸፍነውን አፈር እንዴት መርገጥ እንዳለብን ሊያስተምረን ይችላል ተብሏል።

03 Sep 2025, 14:52