MAP

ነሃሴ 13 የተከበረው የሰብዓዊነት ቀን ነሃሴ 13 የተከበረው የሰብዓዊነት ቀን   (AFP or licensors)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.አ.አ. በ 2024 ዓ.ም. የሞቱ የእርዳታ ሰራተኞችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.አ.አ. ከ 2024 ዓ.ም. መጀመሪያ ጀምሮ ቢያንስ 383 የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ሰራተኞች በዸም አቀፍ ደረጃ መገደላቸውን ገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.አ.አ. በ 2024 ዓ.ም. መጀመሪያ ጀምሮ በዸም አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 383 የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ሰራተኞች መገደላቸውን ገልጿል።

የዸም የሰብአዊ ቀንን አስመልክቶ ማክሰኞ ዕለት በተለቀቀው አሃዛዊ መረጃ መሰረት እ.አ.አ. በ 2024 ዓ.ም. የተከሰተው የሞት መጠን ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ 31 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ የተነገረ ሲሆን፥ ከሟቾች መካከል ግማሽ ያህሉ ወይም 181 የሚሆኑት ሰዎች የሞቱት በጋዛ ውስጥ እንደሆነ እና በሰርጡ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግጭት በሰብአዊ ተግባራት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተነግሯል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት ውስጥ 265 የእርዳታ ሰራተኞች ተግባራቸውን ሲያከናውኑ በቀጥታ ጥቃት እንደደረሰባቸው እና ከተገደሉት መካከል አብዛኞቹ በሥራ ላይ እያሉ ብቻ ሳይሆን በቤታቸው ውስጥ ኢላማ የተደረገባቸው የአካባቢው ሰራተኞች ጭምር እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ከሟቾች በተጨማሪ 308 የእርዳታ ሰራተኞች እንደቆሰሉ፣ 125 እንደታገቱ 45 ደግሞ መታሰራቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ ቶም ፍሌቸር በአንድ የሰብአዊ ሥራ ባልደረባ ላይ የሚደርስ አንድ ጥቃት በሁሉም የእርዳታ ሰራተኞች እና በሚያገለግሉት ሰዎች ላይ የተፈፀመ ጥቃት መሆኑን በመግለጽ ግጭቱን አውግዘዋል።

ምክትል ዋና ጸሃፊው በጣም ዘግናኝ ከሆኑት ክስተቶች መካከል በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የእስራኤል ወታደሮች በግልጽ ምልክት በተደረገባቸው የድንገተኛ አደጋ ተሽከርካሪዎች ላይ ተኩስ ከፍተው 15 የህክምና ባለሙያዎችን እና ምላሽ ሰጪ ሰራተኞችን የገደሉበት ጥቃት መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን፥ ከዚህም በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ምንጮች እንዳሳዩት በኋላ ላይ ተሽከርካሪዎቹ እና አስከሬኖቹ በቡልዶዘር ተደርገው በጅምላ የተቀበሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሰል ጥቃቶች ዸም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋትን የሚጥሱ መሆኑን ጠቅሶ፥ የእርዳታ ሰራተኞችን ለመጠበቅ እና ወንጀለኞችን ተጠያቂ ለማድረግ የተጠናከረ ዸም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል።

የዘንድሮው የዸም የሰብአዊነት ቀን እ.አ.አ. በ 2003 ዓ.ም. ባግዳድ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፅህፈት ቤት ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ሃላፊ ሰርጂዮ ቪየራ ዴ ሜሎን ጨምሮ የ22 የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ህይወት ያለፈበት ቀንን በማስታወስ ተከብሯል።

21 Aug 2025, 12:57