የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ውርስ በአዲሱ ትውልድ ዘንድ እንደሚቀጥ ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
በዛይድ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ሽልማት ሰጭ፣ በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ የርክሌይ የሃይማኖት፣ የሰላም እና የዸም አቀፍ ጉዳዮች ማዕከል አስተባባሪነት ለሁለተኛ ጊዜ የሚቀርበው የሰብዓዊ ወንድማማችነት ኅብረት ፕሮግራም ዝግጅት መጠናቀቁ ታውቋል።
በበጋ ወራት የሚቀርብ ተከታታይ ምናባዊ ዝግጅት እና በኢንዶኔዥያ መዲና ጃካርታ ውስጥ በይነ-መረብ አማካይነት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የጥናት ጉብኝት ፕሮግራሙ በዸም ዙሪያ ካሉ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ አሥር የተማሪዎች መሪዎችን ያሰባሰበ ሲሆን፥ ዋና ግቡ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2019 ዓ. ም. በአቡ ዳቢ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና በአል-አዝሃር ታላቁ ኢማም አል ጣይብ መካከል የተፈረመውን የሰብዓዊ ወንድማማችነት ሠነድ ውርስ ለማስቀጠል እንደ ሆነ ታውቋል።
ወጣት ተማሪዎችን ለወደፊት ጊዜ ማዘጋጀት
በጃካርታው ጉብኝት ወቅት ተማሪዎቹ በሃይማኖቶች እና በባሕሎች መካከል የሚደረጉ ውይይቶችን በማዳበር እና ክህሎታቸውን ለማሻሻል በሚረዱ የላቁ የውይይት አውደ-ጥናቶች እና የተግባር ስልጠናዎች ላይ ተሳትፈዋል።
የተማሪ መሪዎች ቡድን የጃካርታ ሊቀ ጳጳስ ከሆኑት ከብፁዕ ካርዲናል ኢግናሽቲየስ ሱሃርዮ እና የኢንዶኔዥያ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ የዛይድ ሽልማት የሰብዓዊ ወንድማማችነት ዳኞች ኮሚቴ አባል ከነበሩት መሐመድ ዩሱፍ ካላን ከመሳሰሉ ግብረሰናይ፣ ዲፕሎማቶች እና የሕዝብ ተወካዮች ጋር ተገናኝቷል።ለአንድ ሳምንት በቆየው ጉብኝት ወቅት የተማሪ መሪዎች ቡድን በመሐመድያህ እና በዳርማ ባኪቲ የቻይና ቤተ መቅደስ የሚተዳደር ሆስፒታልን ጨምሮ የሰው ልጆች ወንድማማችነትን ያካተቱ የመስክ ቦታዎችን ጎብኝቷል።
በሁለት ሕዝባዊ ዝግጅቶች የተጠናቀቀው ፕሮግራሙ፥ አንደኛው በጃካርታ በሚገኘው በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ የውጭ አገልግሎት እስያ-ፓሲፊክ ሥፍራ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ውርስ እና በሰብዓዊ ወንድማማችነት ሠነድ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ሁለተኛው በጃካርታ ከሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምባሲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የእራት ግብዣ እንደ ነበር ታውቋል።
አዲሱን ትውልድ ማበረታታት
በዝግጅቱ ማጠናቀቂያ ላይ የዛይድ ሽልማት ለሰብዓዊ ወንድማማችነት መርሃ ግብር ዋና ጸሐፊ ዳኛ መሐመድ አብደልሰላም፥ ልምዱ የዸምን ችግሮች ለመፍታት እና አንድነትን የሚያጎለብት አዲስ ወጣት መሪዎችን በማዘጋጀት ግብ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ዳኛ መሐመድ አብደልሰላም ለዝግጅቱ ተሳታፊዎች ባደረጉት ንግግር፥ “እነዚህ ወጣቶች የውይይት ተነሳሽነት መሪዎች እንዲሆኑ፣ በባሕሎች እና በሃይማኖቶች መካከል ድልድይ ፈጣሪ እና አርአያ እንዲሆኑ በማበረታታት ኩራት ይሰማናል” ሲሉ ተናግረዋል።
የዸም አቀፍ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የበርክሌይ የሃይማኖት፣ የሰላም እና የዸም ጉዳዮች ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ቶማስ ባንቾፍ በበኩላቸው፥ በዩኒቨርሲቲው እና በኅብረቱ መካከል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸው፥ “ይህ ቁርጠኝነት የቀጣዩ ትውልድ መሪዎችን በባህል እና በሃይማኖታዊ ልዩነቶች ውስጥ እንዲሳተፉ ለማዘጋጀት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
ከጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ የመጡት አቶ ሻሃን ሻፊ፥ የጃካርታው ስብሰባ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ታላቁ ኢማም አል-ታይብ ለሰው ልጆች ወንድማማችነት ያቀረቡትን ጥሪ ወደ ፊት ለማራመድ የማበረታቻ ስሜት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።
ከኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የመጡት አቶ አሩሺ ፕራሳድም፥ ፕሮግራሙ በኢንዶኔዥያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በመንፈሳዊ እና ሃይማኖታዊ መልክዓ ምድር ውስጥ ያሉ በርካታ እንግዶች እንዲገናኙ መብት እንደሰጣቸው በማብራራት፥ በሃይማኖቶች መካከል ያሉ እሴቶች በኢንዶኔዥያ አውድ ውስጥ እንዴት እንደሚስማሙ ገልጸዋል።
በአንዋር ጋርጋሽ የዲፕሎማሲ አካዳሚ ባልደረባ የሆኑት አምና አል ባስካቲ በፕሮግራሙ ላይ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ኩራት ገልጸው፥ እንደ ኤሚሬትስ ወጣት ተሳፊነታቸው ይህን ውርስ ማስከበር እና ለትውልድ የተሻለ የወደፊት ሁኔታን ለመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት የትውልዳቸው ሃላፊነት መሆኑን በፅኑ እንደሚያምኑ ገልጸዋል።