MAP

ለንደን ለንደን  

በለንደን በሚካሄደው የአውሮፓ የብሮድካስቲንግ ጉባኤ ላይ የቫቲካን ሬዲዮ እንደሚሳተፍ ተገለጸ

በለንደን የሚገኘው የቢቢሲ ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱን 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስመልከት 94ኛውን የአውሮፓ ብሮድካስቲንግ ህብረት (EBU) ጠቅላላ ጉባኤ ከሰኔ 25 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚያስተናግድ ሲሆን፥ የህብረቱ መስራች አባል የሆነውን የቫቲካን ሬዲዮን በመወከል የቫቲካን መገናኛ ብዙሃን ምክትል ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር አሌሳንድሮ ጊሶቲ በጉባኤው ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በለንደን በሚካሄደው የአውሮፓ ብሮድካስቲንግ ህብረት (EBU) 94 ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በርካታ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ይህ ማህበር በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ የህዝብ አገልግሎት ሚዲያ ድርጅቶች ውስጥ ግንባር ቀደም ማህበር እንደሆነ እና ዝግጅቱ የሚካሄደው በብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ቢቢሲ) ዋና መስሪያ ቤት እንደሆነ እና የቫቲካን ሬዲዮን ወክለው የቫቲካን መገናኛ ብዙሃን ምክትል ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር አሌሳንድሮ ጊሶቲን ጨምሮ ከዸም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዋና ዋና ሰዎች በዝግጅቱ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የኢ.ቢ.ዩ. 75ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ የተደረገ ጉባኤ
የአውሮፓ ብሮድካስቲንግ ህብረት (EBU) የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት በማስመልከት በሚካሄደው የዘንድሮው የህብረቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በርካታ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት ሲሆን፥ ለሕዝብ አገልግሎት ማሰራጫዎች መድረክ ሆኖ እንዲያገለግል ተብሎ በተመሠረተው በዚህ ማህበር በአሁኑ ወቅት ከአውሮፓ ብቻ ሳይሆን የሜዲትራኒያን ሃገራትን ጨምሮ ሰሜን አፍሪካን እና መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የተካተቱበት ከ50 በላይ አገሮች የተውጣጡ 112 ድርጅቶችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ቢቢሲን ጨምሮ፣ የጣሊያን ብሔራዊ የህዝብ ብሮድካስቲንግ ኩባንያ የሆነው RAI፣ የፈረንሳይ ቴሌቭዥን እና የቫቲካን ሬዲዮን የመሳሰሉ መስራች አባላት በድርጅቱ ውስጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ የተነገረ ሲሆን፥ የቫቲካን ሬዲዮን ወክለው የአቶ ጊሶቲ በለንደን መገኘት ጣቢያው ለዸም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ውይይት ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ያረጋግጣል ተብሏል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ስብሰባ ላይ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች በዘመናዊው የመገናኛ ሥርዓት ላይ የሚገጥሟቸውን በጣም አንገብጋቢ ፈተናዎችን አንስተው እንደሚወያዩ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ከእነዚህም አጀንዳዎች ውስጥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተፅእኖን፣ የፕሬስ ነፃነት ጥበቃ፣ የሀሰት መረጃን መከላከል ስለሚቻልባቸው መንገዶች እና የማሰራጫ ቴክኖሎጂዎች የወደፊት ሁኔታን በተመለከተ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

ኢ.ቢ.ዩ፡ የህዝብ አገልግሎት እና ፈጠራ ምሰሶ
የአውሮፓ ብሮድካስቲንግ ህብረት (ኢቢዩ) ለ 75 ዓመታት የህዝብ አገልግሎት ሚዲያዎችን ዋና እሴቶች ለማስተዋወቅ እና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለጋራ ጥቅም ለማሳደግ በቁርጠኝነት ሲሰራ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፥ በጣም ከሚታወቁት ተነሳሽነቶቹ መካከል ‘ዩሮ-ቪዥን’ የተሰኘው የሙዚቃ ውድድር እና በአባል ብሮድካስተሮች መካከል የዜና ይዘትን ለማጋራት ታስቦ የተመሰረተው የዩሮ-ቪዥን የዜና ልውውጥ መድረክ ይገኙበታል።

ከዚህም በተጨማሪ በለንደኑ ጉባኤ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የህዝብ ሚዲያ ዘላቂነት፣ የተሳሳቱ መረጃዎችን መከላከል እንዲሁም እየጨመረ በመጣው የጽንፈኝነት ዸም ውስጥ ማህበራዊ ትስስርን ለማጎልበት የብሮድካስተሮች ሚና የሚሉ ጭብጦች እንደሚዳሰሱ ተብራርቷል።

የቫቲካን ረዲዮ ሚሲዮናዊያን ድምፅ
ኢ.ቢ.ዩ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የቫቲካን ረዲዮ ተሳትፎ የቤተክርስቲያኒቱን ሁለንተናዊ መልዕክት በዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች የማስተላለፍ ተልእኮውን ያሳያል የተባለ ሲሆን፥ በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በሳንታ ማሪያ ዲ ጋለሪያ በሚገኘው የቫቲካን ረዲዮ የስርጭት ማዕከል ያደረጉት ጉብኝት ይሄንን ሃሳብ ያረጋግጣል ተብሏል።

ቅዱስ አባታችን በወቅቱ ባደረጉት ንግግር በላቲን አሜሪካ እና በአፍሪካ በሚስዮናዊነት ሲያገለግሉ በነበረበት ወቅት የቫቲካን ረዲዮ የአጭር ሞገድ ሥርጭት እጅግ ጠቃሚ የሆነ የግንኙነት ምንጭ እንደነበር አስታውሰው፥ ስርጭቱ ሌሎች የዜና ማሰራጫዎች ሊደርሱባቸው በማይችሉበት ቦታዎች ሁሉ ተደራሽ እንደነበር እና በዸም ዳርቻ ላይ ተስፋን እና እውነትን ለማምጣት ሚሲዮናዊ የመገናኛ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

02 Jul 2025, 14:33