በፖላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መካሄዱ ተነገረ
አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
የፖላንድ መራጮች የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶችን በሚወክሉ ሁለት ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች መካከል ድምጽ መስጠት የጀመሩ ሲሆን፥ ሰላሳ ስምንት በመቶ በሆነ ድምጽ እየመሩ የሚገኙት የሊበራል ፓርቲን ወክለው እየተወዳደሩ የሚገኙት የታዋቂው የጃዝ ሙዚቀኛ ልጅ፣ የ53 ዓመቱ ራፋል ትርዛስኮቭስኪ በርካታ ቋንቋ ተናጋሪ እና የፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶ ከንቲባ ሲሆኑ፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ ጋር የፖለቲካ ልዩነት ባለው የጥምር አስተዳደር ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም እየተነገረ ይገኛል።
ሆኖም እጩ ተወዳዳሪው ራፋል ናሽናሊስት ፓርቲን ወክለው እየተወዳደሩ ከሚገኙት የታሪክ ምሁሩ እና የቀድሞ አማተር ቦክሰኛ ካሮል ናውሮኪ ከባድ ፈተና እንደገጠማቸው የተነገረ ሲሆን፥ የ42 ዓመቱ ናውሮኪ እ.አ.አ. በ 2015 እና በ 2023 ዓ.ም. ፖላንድን ያስተዳደረው በህዝባዊ-ቀኝ ክንፍ ህግ እና ፍትህ ፓርቲ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተገልጿል።
ታዛቢዎች እንደሚሉት ናውሮኪ አሸንፈው ወደ ስልጣን ከወጡ ፖላንድ በጦርነት ውስጥ ለምትገኘው ጎረቤት ሃገር ዩክሬን ስታደርግ የነበረው የድጋፍ ደረጃ ይለወጣል እየተባለ ይገኛል።
እጩ ተወዳዳሪው በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው ውጥረት እና የከረረ ታሪካዊ ግንኙነት በመግለጽ፥ ዩክሬን የኔቶ ወታደራዊ ህብረት አባል መሆንዋን እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል።
ነገር ግን ናውሮኪ ከአንድ ትልቅ ሰው የመኖሪያ አፓርታማ ማግኘታቸውን ጨምሮ በወጣትነታቸው በ140 የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል በተካሄደው የተደራጀ ግጭት ላይ እንደተሳተፉ ማመናቸው የምርጫ ዘመቻቸው ውጤት ላይ ጥላ እንዳጠላበት እየተነገረ ይገኛል።
የምዕራቡ ደጋፊ የሆኑት ተቀናቃኛቸው ትርዛኮውስኪም ቢሆኑ እጩነታቸውን ለማስተዋወቅ ለኦንላይን ማስታወቂያ ከውጭ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘታቸው ተነስቶ ክስ ስለገጠማቸው ከውዝግብ ያመለጡ አልሆኑም ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ ታዋቂ ባልሆነው የቱስክ መንግስት እንደሚደገፉ እየታወቀ ከንክኪ ውጪ እንደሆኑ በሚገባ እራሳቸውን መከላከል እንደነበረባቸውም ተነግሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቱስክ እጩ ተወዳዳሪው ትርዛስኮውስኪ ቢያሸንፉ እንደሚመርጡ የተነገረ ሲሆን፥ ምንም እንኳን የፖላንድ ፕሬዚዳንትነት ሚና በዋናነት ስነ-ስርዓታዊ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንቱ በውጭ ሃገራት እና በመከላከያ ፖሊሲ ላይ የተወሰነ ተጽእኖ እንዳላቸው እንዲሁም አዲስ ህግን የመቃወም ወሳኝ ስልጣንም እንዳላቸው ይነገራል።
የማገጃ ድምጽ የሚሻረው አብላጫውን የፓርላማ ሶስት-አምስተኛ ድምጽ ሲያገኝ ሲሆን፥ ሆኖም አሁን ያለው መንግስት ይሄንን እንደማያሟላ ተገልጿል። ይህም በመሆኑ እሁድ ዕለት የተደረገው ምርጫ ወደ 39 ሚሊዮን ለሚጠጉ የምስራቅ አውሮፓ ትልቁ ኢኮኖሚ ባለቤት እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ካቶሊካዊያን ሀገር የወደፊት አቅጣጫ ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል።