MAP

በዸም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ከድርጅቱ አርማ አጠገብ ቆመው በዸም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ከድርጅቱ አርማ አጠገብ ቆመው   (Johannes P. Christo)

ካሪታስ ‘የዕዳ ጫና በማደግ ላይ ያሉ አገሮችን እድገት እያሽቆለቆለ ነው’ ማለቱ ተነገረ

የቫቲካን ባለስልጣናት፣ የበጎ አድራጎት ሰራተኞች እና ዸም አቀፍ እውቅና ያላቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ዸም አቀፉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት ካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ በዌቢናር ባዘጋጀው የዕዳ ማሻሻያ ውይይት ላይ ተሳትፈው በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦችን ማንሳታቸው ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

3.3 ቢሊዮን ሰዎች ወይም የዓለማችን ግማሽ ያህል የሚጠጋ ህዝብ ለጤና አጠባበቅ ይልቅ ዸም አቀፍ እዳቸውን ለመክፈል ብዙ ገንዘብ በሚያወጡ አገሮች ውስጥ እንደሚኖሩ ይፋ የተደረገ ሲሆን፥ ይሄ አስደንጋጭ መረጃ የወጣው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የበጎ አድራጎት ተቋም በሆነው ካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ አዘጋጅነት ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደ የዌቢናር ውይይት እንደሆነ ተገልጿል።

ረቡዕ ዕለት የተካሄደው ዌቢናር ከ 200 በላይ ግለሰቦችን አንድ ላይ ያሰባሰበ ሲሆን፥ በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች፣ ዸም አቀፍ እውቅና ያላቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች እና ከፍተኛ የቫቲካን ባለስልጣናት ስለ ዸም አቀፍ ዕዳ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት አንስተው ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

“ዕዳን ወደ ተስፋ መቀየር”
የካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አላስታይር ዱተን ውይይቱን በማስተዋወቅ ያስጀመሩ ሲሆን፥ ሃላፊው እንደጠቆሙት በርካታ ሃገራት ከጤና አጠባበቅ እና ከትምህርት ይልቅ በርካታ ገንዘብ የዸም አቀፍ ዕዳቸውን ለመክፈል ሲሉ ወጪ ማድረጋቸው፥ በዛሬው ኢኮኖሚ ውስጥ የሰው ልጅ ከ ‘ኢኮኖሚያዊ ጥቅም’ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የመሆኑን እውነታ ያሳያል ብለዋል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ አቶ ዱተን እንደተናገሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስለ ዕዳ ማሻሻያ ርዕሰ ጉዳይን ማንሳት የጀመሩት ተመርጠው ሳምንት እንኳን ሳይሞላቸው እንደሆነ ጠቁመው፥ ከዚህም ባሻገር ይሄንን ርዕሰ ጉዳይ የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በ 2016 ዓ.ም. በሃገራት መካከል የሚደረጉ የብድር ስምምነቶችን ለመቆጣጠር ሁሌም ደካማው ሃገር የሚሸነፍበትን አካሄድ በመተው ሁለገብ የሆነ ዘዴ እንደሚያስፈልግ አንስተው እንደነበር አስታውሰዋል።

የካሪታስ ዋና ሃላፊው አክለውም ካሪታስ ኢፍትሃዊ ለሆነ የብድር ስምምነት የዕዳ ስረዛ እንዲደረግ ጥሪ የሚያቀርብ ‘ዕዳን ወደ ተስፋ መቀየር’ የሚል ዘመቻ መጀመሩን ገልጸዋል።

የካሪታስ ሰራተኛ የሆኑት አልፎንሶ አፒሴላ እንዳብራሩት የዘመቻው ዋና ዓላማ፣ በተለይም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀጣይነት ያለው 2025 የኢዮቤልዩ ዓመትን ከግምት ውስጥ በማስገባት፥ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ የእዳ አሰራር ዙሪያ ህዝባዊ ጫና መፍጠር እንደሆነ ገልጸው፥ “በዸም ላይ 1.4 ቢሊዮን ካቶሊኮች አሉ፥ ስለእነሱ የሚሟገት ኤጀንሲ እንዳለ ማሳየት እንፈልጋለን” ብለዋል።

የዕዳ ስርዓት ተጽእኖ
በዝግጅቱ ላይ ከተሳተፉት ሌሎች ተናጋሪዎች መካከል የቀድሞ የአርጀንቲና የኢኮኖሚ ሚኒስትር የነበሩት የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ማርቲን ጉዝማን ይገኙበታል።

ፕሮፌሰር ጉዝማን የዸም የዕዳ ስርዓት በዸም ላይ በጣም ደሃ በሆኑ ሀገራት ላይ የሚያደርሰውን አስከፊ ውጤት ጎላ አድርገው በመግለጽ፤ እነዚህ የብድር ስምምነቶች ከበለጸጉ ሃገራት የበለጠ የወለድ ክፍያ እንደሚጠይቁ ጠቁመዋል።

የኖቤል ሽልማት አሸናፊው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ጆሴፍ ስቲግሊትዝ የሚመራው እና በዓለማችን ደቡብ ንፍቀ ክበብ ስላለው የእዳ እና የልማት ቀውሶች ሪፖርት በማዘጋጀት ላይ የሚገኘው ‘የቫቲካን የኢዮቤልዩ የባለሙያዎች ኮሚሽን’ እየሰራቸው በሚገኙ ሥራዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የቅድስት መንበር የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጸሃፊ የሆኑት ሲስተር አሌሳንድራ ስሜሪሊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የበለጸጉ ሃገራት ለድሃ አገሮች የሚከፍሉትን ‘የሥነ-ምህዳር ዕዳ’ ጽንሰ-ሐሳብ አጽንኦት ሰጥተው በማንሳት፥ በአየር ንብረት ቀውስ ምክንያት እየተሰቃዩ ስላሉት ደሃ ሃገራት እና ይህ ቀውስ እንዲፈጠር ብዙ አስተዋጽኦ ስላበረከቱት አበዳሪ ሃገራት አንስተዋል።

በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ገብርኤሌ ካቺያ በበኩላቸው የስነ ምህዳር ዕዳ ጽንሰ-ሀሳብን በመጥቀስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ለኢዮቤልዩ ዓመት ማስጀመሪያ ያደረጉትን ንግግር አጽንዖት ሰጥተውበታል።

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ የዕዳ ሥርዓቱ በድሃ አገሮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በግልፅ ማሳወቅ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበው “ይህ የምጣኔ ሃብት ቴክኒካዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፥ ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት ግልጽ እንቅፋት ነው” ብለዋል።
 

29 May 2025, 16:45