የቅድመ ግጭት ይቅርታ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
"እውነተኛ ይቅርታ ንስሐን መጠበቅ እንደሌለበት ያውቃል፣ ነገር ግን ተቀባይነት ከማግኘቱ በፊት እንኳን አስቀድሞ እራሱን እንደ ነፃ ስጦታ አድርጎ ያቀርባል" በማለት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ቃል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፣ ኢየሱስ አሳልፎ ለሰጠው ለይሁዳ እንኳ እንጀራ ቆርሶ እንደ ሰጠው በሚገልጸው የዮሐንስ ወንጌል ክፍል ላይ አስተንትኖ አድርገዋል። እሱ መለኮታዊ አመክንዮ ነው፣ " እንደፈለጋችሁ አድርጉ" ከሚለው ከሰው ልጅ አመክንዮ የራቀ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኢየሱስ፣ እየሆነ ያለውን ነገር በሚገባ እንደ ሚያውቅ፣ ነገር ግን በትክክል ስለሚመለከት፣ “የሌላውን ነፃነት፣ በክፋት ቢጠፋም፣ አሁንም በየዋህነት የእጅ ምልክት ሊደረስበት እንደሚችል ያውቃል” በማለት ገልጿል።
ይህ የቅድመ ግጭት ይቅርታ የምያሳፍር ተግባር ሊሆን ይችላል፣ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሳያስፈልገው ከምህረት እቅፍ ጋር በቅድሚያ የሚመጣው ይቅርታ ግን በጣም አስፈላጊ ነው። ይህም ልክ በቀራጩ ዘኬዎስ ላይ እንደደረሰው ነው፣ በኢየሱስ ስለ ተጠራና ስለተቀበለው ንስሐ የገባው፣ ራሱን ወደ ዘኬዎስ ቤት የጋበዘው፣ በናዝሬት እንዲህ ያለውን ወግ እና ማኅበራዊ ስምምነቶች መቋረጥ ሲመለከት ሁሉም ሰው ተደናግጦ ነበር።
ሕይወታችን እና ግንኙነታችን ምን ያህል እንደዚህ ዓይነት ይቅርታ ይፈልጋሉ። ዓለማችን ምን ያህል ይቅርታ ትፈልጋለች - “የመርሳት” ወይም “የደካማነት” ባሕርይ አይደለም። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.አ.አ በመስከረም 11/2001 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እ.አ.አ በ2002 ዓ.ም ለዓለም የሰላም ቀን ይፋ ባደረጉት መልእክት ትንቢታዊ ቃላት ወደ አእምሯቸው ይመጣሉ። ሁሉም ሰው ስለ "መከላከያ" ጦርነት ሲናገሩ፣ ለጥቃቱ ግዙፍ ምላሽ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ ይፋ ባደርጉት መልእክት "ያለ ፍትህ ሰላም የለም፣ ያለ ይቅርታ ፍትህ የለም" በማለት ማረጋገጫ ሰጥተው ነበር።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዲህ ብለው ነበር፡- “የዚህ ዓይነት አሰቃቂ ጥቃት የደረስንባቸውን ሥነ ምግባራዊና ማኅበራዊ ሥርዓት እንዴት እናስመልሳለን የሚለውን የማያቋርጥ ጥያቄ ላይ ለማሰላሰል ብዙ ጊዜ ወሰድኩኝ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ የተረጋገጠው በእኔ ምክንያት የፈረሰው ሥርዓት ፍትህን ከይቅርታ ጋር በማጣመር ምላሽ ካልሰጠ በስተቀር ሙሉ በሙሉ መመለስ እንደማይቻል ነው" በማለት ጽፈው ነበር።
ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ፣ “ቤተሰቦች፣ ቡድኖች፣ ማኅበራት፣ መንግሥታትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ራሱ የተቋረጠውን ግንኙነታቸውን ለማደስ፣ የጋራ ውግዘት ከሚያስከትሉ ሁኔታዎች በዘለለ እና ሌሎችን ያለይግባኝ የመድልዎን ፈተና ለማሸነፍ ይቅርታ ያስፈልጋቸዋል። ይቅር የማለት ችሎታም በፍትህና በአብሮነት የተረጋገጠ የወደፊት ኅብረተሰብ ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ነው።
በሌላ በኩል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዳብራሩት፣ ይቅርታ አለማድረግ በተለይም ቀጣይ ግጭቶችን በሚያባብስበት ጊዜ፣ “በሰው ልጅ ልማት ረገድ እጅግ ውድ ነው፣ ሀብት ለልማት፣ ለሰላምና ለፍትህ ሳይሆን ለጦር መሣሪያ ይውላል፣ በሰው ልጅ ላይ የሚደርሰው መከራና ስቃይ፣ እርቅ ባለመኖሩ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰው መከራ፣ ይቅር ባለማለታችን እድገታችንን እናዘገያለን! ሰላም ለዕድገት አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን በይቅርታ ብቻ የሚረጋገጥ ሰላም አስፈላጊ ነው” በማለት አክለው መግለጻቸው ይታወሳል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ይቅርታ ከሌለ ሰላም እንደማይኖር በማስረዳት ረቡዕ ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀዋል። አርብ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም ለሁሉም ሰው የጸሎትና የጾም ቀን እንዲሆን በመጋበዝ የሰላም ንግሥት የሆነችውን የማርያምን አማላጅነት ለመለመን እና በጦርነት ለተሰበረ ዓለም ሰላምና ፍትህ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ይቻል ዘንድ አማላጅነቷን የምንማጸንበት ቀን እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ይህንንም የምናደርገው ለዓለማችን የግጭት ቅድመ ይቅርታ በጥብቅ ያስፈልጋታልና በ|ጸሎት ልንተጋ ይገባል።