MAP

ቅድስት መንበር ‘በሄይቲ የጠፋውን ሰላም ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ ትደግፋለች’! ቅድስት መንበር ‘በሄይቲ የጠፋውን ሰላም ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ ትደግፋለች’! 

ቅድስት መንበር ‘በሄይቲ የጠፋውን ሰላም ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ ትደግፋለች’!

ቅድስት መንበር ቤተክርስቲያኗ ከሄይቲ ህዝብ ጋር ያላትን ቅርበት በድጋሚ የገለጸች ሲሆን በሁከት በተሞላች ሀገር ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት የማያቋርጥ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጣለች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የአሜሪካ መንግስታት ድርጅት (OAS) (የአሜሪካ መንግስታት ድርጅት በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ውይይት፣ የፖሊሲ ትንተና እና ውሳኔ አሰጣጥ ዋና ክልላዊ መድረክ ነው። በመላው አሜሪካ ከሚገኙ ብሔራት የተውጣጡ መሪዎችን በአንድ ላይ ያሰባስባል፣ ንፍቀ ክበባዊ ጉዳዮችን እና እድሎችን ለመፍታት ይሰራል። በጋራ በመሆን በክልሎች መካከል ትብብርን ለመፍጠር እና በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ በሰብአዊ መብቶች፣ በባለብዙ ገፅታ ደህንነት እና በዘላቂ ልማት ላይ የጋራ ክልላዊ አጀንዳን ለማራመድ የሚሰራ ድርጅት ነው)፥ ይህ የአሜሪካ መንግሥታት ድርጅት በዋሽንግተን ዲሲ በነሀሴ 14/2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ፍኖተ ካርታ ላይ ሄይቲ ከአራት አመታት በላይ የማያቋርጠውን የቡድኖች ጥቃት ተቋቁማለች ማለታቸው ተገልጿል።

እ.ኤ.አ. በሐምሌ 7/2021 ዓ.ም ፕሬዝዳንት ጆቨኔል ሞይስ በፖርት ኦ-ፕሪንስ መኖሪያ ቤታቸው ተገደሉ፣ እናም በአገሪቱ የሚገኙ ኃያላን ቡድኖች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ ላይ ውድመት ያደረሱ ሲሆን አንዳንዴም ከ85 በመቶ በላይ ዋና ከተማውን ተቆጣጥረው ነበር።

እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም ብቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ ከ5,000 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

የአሜሪካ መንግስታት ድርጅት (OAS) ዋና ጸሃፊ አልበርት ራምዲን "ወደ ሄይቲ ወደሚመራው ፍኖተ ካርታ ላይ ለመረጋጋት እና ሰላም ከክልላዊ እና አለምአቀፍ ድጋፍ" በሚል ርዕስ ረቡዕ ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም የተዘጋጀውን ሰነድ አቅርበዋል።

ፍኖተ ካርታው ከሄይቲ አመራር ጋር በመተባበር አፋጣኝ መረጋጋትን ከረዥም ጊዜ መዋቅራዊ ማሻሻያ ጋር በማገናኘት ለአሜሪካ መንግስታት ሄቲንን የሚደግፉበትን መንገድ ያቀርባል ሲል የአሜሪካ መንግስታት ድርጅት  ድረ-ገጽ ዘግቧል።

በአሜሪካ መንግስታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት የእኔታ አባ ሁዋን አንቶኒዮ ክሩዝ ሴራኖ በቀረበው ገለጻ ላይ ተንተርሰው እንዳሉት ቅድስት መንበር “በዛች የካሪቢያን አገር ያለውን ከባድ የጸጥታና ተቋማዊ ቀውስ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ ገልጿል።

ፍኖተ ካርታው “ሄይቲ እያጋጠማት ላለው ጥልቅ እና አስቃቂ ሁኔታ፣ ማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ጉዳዮች፣ በተለይም ቀጣይነት ባለው የጸጥታ ማጣት፣ ሥር የሰደደ ድህነት እና በታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ተለይቶ የሚታወቅ አደጋን ለመቋቋም ይችል ዘንድ” ምላሽ ለመስጠት ይፈልጋል ብለዋል።

የእኔታ አባ ክሩዝ እ.አ.አ በነሀሴ 10/2025 የሄይቲ ህዝብ የግድያ፣ የአመፅ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የግዳጅ ግዞት እና አፈና ዛቻ ለሚደርስባቸው ሰዎች ሁሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ሰላም እንዲሰፍን ያቀረቡትን ጥሪ አስታውሷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ታጋቾቹን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠያቂ ለሆኑት ሁሉ አስቸኳይ ጥሪ አቀርባለሁ እና የሄይቲ ሕዝቦች በሰላም እንዲኖሩ የሚያስችላቸውን ማህበራዊ እና ተቋማዊ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተጨባጭ ድጋፍ እንዲደረግላቸው እጠይቃለሁ" ማለታቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ ጊዜ የእኔታ አባ ክሩዝ የሄይቲ ጳጳሳት እ.አ.አ በሐምሌ 23/2025 ዓ.ም መግለጫ ማውጣታቸውን አስታውሰው፣ የሄይቲን ማህበረሰብ መፍረስ አስመልክቶ የማስጠንቀቂያ ደወል በማሰማት የሰውን ክብር የሚያዋርዱ ድርጊቶችን ሁሉ አውግዘዋል።

“የህብረተሰቡን መፈራረስ እና የሚደግፉትን ተቋማት ማውደም እያየን ነው” ያሉት የሄይቲ ጳጳሳት መንግስት ከአሁን በኋላ “ደህንነትን፣ ፍትህን አልፎ ተርፎም ለህዝቡ የሚያስፈልጉትን መሰረታዊ ነገሮች ለማቅረብ በእጅጉ ይቸገራል" ማለታቸው ይታወሳል።

በአሜሪካ መንግስታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት የእኔታ አባ ሁዋን አንቶኒዮ ክሩዝ ሴራኖ ለሄይቲ ህዝብ የሰላም መንገድ ለመፈለግ በማንኛውም መንገድ ለመተባበር የቅድስት መንበር ፈቃደኝነትን አረጋግጧል።

“ቅድስት መንበር ለሄይቲ ህዝብ ያላትን ቅርበት እና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ያላትን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጣለሁ" ብለዋል።

 

22 Aug 2025, 15:32