MAP

የወጣቶች ኢዩቤሊዩ የምሽት የጸሎት ጊዜ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የወጣቶች ኢዩቤሊዩ የምሽት የጸሎት ጊዜ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (@Vatican Media)

ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ፡ ጦርነት እኛን ከማጥፋቱ በፊት ጦርነትን ማቆም አለብን ማለታቸው ተገለጸ!

40,000 የሚሆኑ ወጣት ጣሊያናዊያን "አንተም ጴጥሮስ ነህ" በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም ምሽት ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተዘጋጀው የኢዮቤልዩ ዝግጅት ላይ የተሳተፉ ሲሆን ይህ ዝግጅት ሰላምን በዓለም ዙሪያ ለማስፈን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህ ዝግጅት በካርዲናል ዙፒ ቀጥተኛ ተሳትፎ እና በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓተ አምልኮ ፓትርያርክ ካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ከእየሩሳሌም ሆነው በቪዲዮ ባስተላለፉት የተመራ ዝግጅት ነበር።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"በዚህ ምሽት የህይወቶቻችሁን ትኩስነት እና ድንገተኛነት በደስታ፣ በአዘኔታ እና በመተማመን በሚመለከተው በመላው ቤተክርስቲያን አቀባበል እንደ ተደረገለችሁ ሆኖ ሊሰማችሁ ይገባል" ያሉት የጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ብፁዕ ካርዲናል ማትዮ ዙፒ ዛሬ ማምሻውን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የወጣቶች ኢዮቤልዩ አካል ከሆኑት 40,000 ወጣት ጣሊያናውያን ጋር የእምነት ሥነ ሥርዓቱን ሲመሩ የተናገሩት ነው።

ከ40ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ባቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ
ከ40ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ባቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (@Vatican Media)

ምሽቱ በመዝሙር፣ በቅዱሳት መጻህፍት ንባባት እና በእምነት ምስክሮች የተከናወነ ሲሆን በግጭት ቀጣና ውስጥ ለሚሰቃዩት መንፈሳዊ ቅርበት የታየበት ዝግጅት ነበር።

"የሰው ልጅ ጦርነትን ማቆም አለበት፣ አለበለዚያ ጦርነት የሰው ልጅን ያጠፋል" በማለት በስብከታቸው ወቅት፣ ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ የተናገሩ ሲሆን፣ ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ለጴጥሮስ መስጠቱን በሚያመለክተው ከማቴዎስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበው ቃል ላይ አስተንትኖ አድርገዋል።

የልባችንን ትጥቅ እንፍታ!

የጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንት የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ሐሳባቸውን ወደ "የሰው ልጆችን ለማጥፋት የጦር መሣሪያ በሚያመርቱ ሰዎች ወደተገነቡት እብድ የሆኑ አመለካከቶች" ያዞሩ ሲሆን ሆስፒታሎችን ጨምሮ ህይወት የሚሰጠውን ነገር ሁሉ አጠፋ፣ “ቤተክርስቲያኗ በመስቀሉ ሥር ትቆማለች፣ ዐይኖች በእንባ የተሞሉ እና በእንደዚህ ዓይነት ስቃይ የተጎዱ ልቦች ናቸው” ሲሉ በቁጭት ተናግሯል።

ዛሬ አሉ ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ሐሳባቸውን ለማጽናት በማሰብ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሞት፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጦርነቶች አሉ። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 12ኛ ከተመረጡ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የጦር መሣርያ  “አለመታጠቅ እና የታጠቀም ካለ ትጥቅ በመፍታት" ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ሁሉም እንዲያደርጉ ጥሪ ባቀረቡበት ወቅት የተናገሩትን አስታውሰዋል።

ይህንንም መሰረት በማድረግ ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ፡- "የልባችንን ትጥቅ እንፍታ፣ ዓመፀኛ የሆነውን ዓለም ልብ እና እጆችን እንፈታ - ቁስሉን ለመፈወስ እና አዲስ ግጭቶችን ለመከላከል!" እንሥራ ሲሉ ተናግረዋል።

ካርዲናል ዙፒ ሌሎችን እንደ ጠላት አድርጎ መቁጠር ወይም ያለ እነርሱ ሙሉ በሙሉ መኖር እንደማንችል ማሰብ የተለመደ በሆነበት ዓለም ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጿል። እኛንም የሚያስፈራውን፣ የማይታሰብ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ኃይል ላይ ያለውን የግድየለሽነት መንፈስ ነቅፏል።

የጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ብፁዕ ካርዲናል ማትዮ ዙፒ በቫቲካን
የጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ብፁዕ ካርዲናል ማትዮ ዙፒ በቫቲካን   (@Vatican Media)

ፒዛባላ፡- ከኔ እና ከማንም በላይ "እኛን የሚለውን" እንምረጥ

ብፁዕ ካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ከኢየሩሳሌም በተላለፈው የቪዲዮ መልእክት በአሁኑ ጊዜ በመላው ጋዛ እየተስፋፋ ያለውን ረሃብ አጉልተው የገለጹ ሲሆን በትክክል በእንደዚህ ዓይነት ጥፋት እና ጨለማ ውስጥ - "በማያልቅ ምሽት" - እምነት አስፈላጊ ነው ሲሉ የተናገሩ ሲሆን "ሕመሙ እውነት ነው፣ እናም ልንክደው አንችልም" ብለዋል ፓትርያርኩ። ነገር ግን እኛ በጎነትን እና ማጽናኛን ለማምጣት የተጠራነው በዚህ ህመም ውስጥ ነው ማለታቸውም ተገልጿል።

ካርዲናል  ፒዛባላ በጋዛ እና በእስራኤል ውስጥ "ብርሃን ተሸካሚዎች" የሆኑትን ብዙ ሰዎች እንዳሉ የገለጹ ሲሆን በቅድስት ሀገር እና ከዚያም በላይ ብዙዎች ለተስፋ መቁረጥ ለሽንፈት እጅ አይሰጡም እምቢ ይላሉ፣ ይልቁንም "ከእኔ እና ከማንም" ይልቅ "የእኛ አንድነት" የተሰኘውን መንገድ ይመርጣሉ ብለዋል።

ካርዲናሉ አፅንዖት ሰጥተው ሲናገሩ ብዙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ሃይማኖታዊ እና በጎ ፈቃደኞች—የሁሉም እምነት—አሁን ተስፋን ለመገንባት እየሰሩ ነው። እነዚህ ሰዎች በመካከለኛው ምሥራቅ ሩቅ የሚመስሉ የኢዮቤልዩ መንፈስ ምልክቶች ናቸው፣ ነገር ግን እንደ ብርሃን መብራቶች ያበራሉ ብሏል።

“የፈረሱ ሕንፃዎችን እንደገና መገንባትና የተበጣጠሰውን ማኅበራዊ መዋቅር ማስተካከል ያለብን ጊዜ ለማዘጋጀት ወደ እነርሱ ልንመለከት ይገባል” ብሏል።

ቤተክርስቲያኗ በእነዚህ ትግሎች ውስጥ፣ በውይይት፣ በጠንካራ እና አንዳንዴም ውጥረት በሚፈጥሩ ውይይቶች ጭምር፣ ልክ እንደ መጀመሪያዎቹ ሐዋርያት መገኘት እንዳለባት ለሁሉም ያሳሰቡ ሲሆን እንደ ጴጥሮስ፣ የሚያንጽ፣ አዲስ አድማስን የሚከፍት፣ የመተማመን እድሎችን የሚፈጥር ቃል እንድንናገር ተጠርተናል ብለዋል።

01 Aug 2025, 10:16