ካርዲናል ፓሮሊን፡- የግል ፍላጎቶች ለጋዛ ችግሮች መፍትሄ እንዳይሰጥ እየከለከሉ ይገኛሉ ማለታቸው ተገለጸ።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በሮም ካምፖ ማርዚዮ በሚገኘው የቅዱስ አውጉስጢኖስ ባዚሊካ በተከበረው የቅድስት ሞኒካ አመታዊ መታሰቢያ መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በመካከለኛው ምሥራቅ ስላለው ቀውስ የቅድስት መንበር አቋም በመግለጽ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ተማጽኖ እና በቅድስት አገር የሚኖሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን መግለጫ በማስታወስ የጋዛ ሕዝብ ከመፈናቀል ማስቆም ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።
የጋዛን ህዝብ መፈናቀል ማስቆም
ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን "በጋዛ ስላለው ሁኔታ የቅድስት መንበርን አስተሳሰብ የሚያንፀባርቀውን በነሐሴ 21/2017 ረፋዱ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለተገኙ ምዕመናን ካደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስትምህሮ በመቀጠል ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ያቀረቡትን ለማስታወስ እወዳለሁ" ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከግሪክ ኦርቶዶክስ እና የላቲን ፓትርያርኮች ጋር “ጦርነቱ እንዲቆም” ጥሪ እንዳቀረቡ እና “የጋዛን ሕዝብ መፈናቀል” በመቃወም እንዴት እንደተናገሩ አስታውሰዋል።
ብዙ የግል ፍላጎቶች ችግሩ እንዳይፈታ እንቅፋት ሆነዋል
ካርዲናሉ “ይህን ሁኔታ በእውነት ሊያስወግዱ የሚችሉ ብዙ መፍትሄዎች፣ አሉ” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፣ ነገር ግን “ለዚህ አደጋ ሰብአዊ ርህራሄ ለመስጠት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን” የምያግዱ የተለያዩ “ፖለቲካዊ” “ኢኮኖሚያዊ” “ከስልጣን ጋር የተገናኙ” እና “አንድ አገር ሌላውን ለመቆጣጠር የምያደርገው ጥረት” ጋር የተያያዙ የፍላጎቶችን ክብደት አውግዘዋል።
መቆየት፣ የድፍረት ተግባር
በጋዛ የሚገኙትን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ የእርዳታ ተቋማት ሠራተኞችንና ምእመናን ጥበቃን በተመለከተ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን “የእስራኤል መንግሥት ባወጣው ትእዛዝ መሠረት ጋዛን ለቆ የመሄድ ነፃነት ተሰጥቷል” ብለዋል። የኢየሩሳሌም የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ሳልሳዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን “ጋዛን ለቀው እንዲወጡ” መጠየቃቸውን መናገራቸውን አስታውሰዋል። “እያንዳንዱ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት እራሱ ይወስናል” ብለዋል ካርዲናል፣ “መቆየት መምረጥ ድፍረት የተሞላው ተጋባር ነው” ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም “ይህ ጋዛን ለቆ የመውጣት ትእዛዝ ካለ ይህ እንዴት ሊከናወን እንደሚችል” እና “በመሬቱ ላይ ፣ የግዛቱን አጠቃላይ ቁጥጥር” ማን እንደ ሚረከብ አላውቅም ብለዋል ።
የዲፕሎማሲ ምልክቶች
በዲፕሎማሲው በኩል የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ብጽዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እንዳሉት ከሆነ ቀጣይነት ያለው "ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር በኤምባሲው በኩል የሚደረጉ ግንኙነቶችን" አረጋግጠዋል እና የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ጌዲዮን ሳአር በዋሽንግተን በምያደርጉት ጉብኝት ወቅት የሚደረጉት ዓለም አቀፍ ንግግሮች ተጨባጭ ውጤቶችን እንደሚያስገኙ ተስፋቸውን ገልጸዋል፦ "ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጠየቁትን እጠብቃለሁ: የተኩስ ማቆም፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የሰብአዊ ርዳታ ተደራሽ ማድረግ፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግን ማክበር - አላስፈላጊ የሆኑትን የጅምላ ቅጣት ማስወገድ ይቻላል" ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
የእስራኤል መንግሥት አቋም
በመጨረሻም ካርዲናል ፓሮሊን የጋዛን ህዝብ በግዳጅ የማፈናቀል አደጋ በተመለከተ እስካሁን የእስራኤል መንግስት "ከዚህ አቋም በፍጹም ንቅንቅ የማለት ፍላጎት እንደሌለው" እና "ምናልባት ትንሽ ተስፋ እንዳለው" የገለጹ ሲሆን ምንም እንኳን ቅድስት መንበር ይህንን ሐሳብ ለማስለወጥ በመገፋፋት ላይ ብትሆንም ቅሉ ችግሩ እስካሁን እንዳልተፈታ አምነዋል።