በሮም የሚገኘው አሌፖ ካህን 'የብዙ ሶርያውያንን ህልም እየኖርን ነው' ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
"ወደ አሌፖ ብዙ ተስፋዎችን ይዤ እንደምመለስ ተስፋ አደርጋለሁ"
እነዚህ ቀላል ቃላት ሊሆኑ ይችላሉ፣ ያሉት የፍራንችስካዊያን ማሕበር አባል የሆኑ ወንድም ጆርጅ ጃሎፍ ጥንካሬን እና እምነትን ይዘው ወደ አሌፖ እንደ ሚመለሱ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ለዲጂታል ሚሲዮናውያን እና የካቶሊክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ኢዩቤሊዩ ላይ ለመሳተፍ “የዲያስፖራ ልጆች” ተብለው ከሚጠሩት ከተወሰኑ ወጣቶች ጋር ወደ ሮም መምጣታቸውን የተናገሩት ወንድም ጆርጅ ጃሎፍ “በሶሪያ ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች አሁንም ሊኖሩ የማይችሉትን ህልም እየተገነዘብን ነው” ብለዋል።
በሶሪያ ያሉ ወጣቶች ሻማ እንዲያበሩላቸው መጠየቃቸው
እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት ሳቢያ በአውሮፓ ያሉ ስደተኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወጣቶች አሁን በጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ ቤልጂየም እና ስዊድን ይኖራሉ ።
ወንድም ጆርጅ “በአሁኑ ጊዜ ሶሪያውያን በቪዛ ችግር ምክንያት በቀላሉ መጓዝ አይችሉም” ብሏል።
ቢሆንም በግላቸው የአካባቢውን የክርስቲያን ማህበረሰብ ፍላጎት ሁሉ በመወከል “ሻማ እንዳበራላቸውና በቅዱስ በር መስቀል ተሸክሜ እንዳልፍ ጠይቀውኛል" ጥያቄውንም ፈጽምያለሁ ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን “እነሱም ከሩቅ ቢሆኑም እንኳ እዚያ በመንፈስ እንደነበሩ መስክረዋል” ብለዋል።
በአሌፖ ውስጥ ያሉ ችግሮች እና "ዕለታዊ ተአምራት"
ምንም ይሁን ምን በሶሪያ ያለው እውነታ አሁንም አስቸጋሪ ነው ያሉት ወንድም ጆርጅ "በአሌፖ ሁኔታው በአንጻራዊ ሁኔታ የተረጋጋ ነው" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን "በቅርብ ጊዜ በደማስቆ ከተከሰቱ ጥቃቶች በኋላ፣ ፍርሃት ወደ ምእመናን ልብ ተመልሷል። የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት በሚካሄድበት ጊዜ እንኳን የደህንነት ጥበቃውን ከፍ አድርገን ማሳደግ ነበረብን፣ ወደ ጸሎት የሚመጡትን ለመጠበቅ ሰዎች በቤተክርስቲያኗ ደጃፍ ላይ ይቆማሉ" ሲሉ የሁኔታውን አስቸጋሪነት ተናግረዋል።
ሁሉም ነገር ቢሆንም የክርስቲያኑ ማኅበረሰብ በጽናት ይቀጥላል። በቁጥር አናሳ—1,200 ያህል ምዕመናን አሉን ነገር ግን ህያው እና ንቁ ሆነ የሚገኙ ናቸው ብለዋል።
“ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድረስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ይሰጣል” ሲሉ ተናግሯል፣ “ይህ ጸጋ ነው፣ የዕለት ተዕለት ተአምር ነው" ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
ወደ ሶርያ ሲመለሱ፣ ወንድም ጆርጅ እንደተናገሩት ከሆነ የሮም ከተማ ፊቶች፣ ቃላቶች እና በረከቶች እና እንዲሁም በእርግጠኝነት፣ “ጌታ ከኛ ጋር ነው፣ ተስፋ አያሳፍርም። እናም እኛ ለምናገኛቸው ሰዎች በየቀኑ ተስፋ እንድንሆን ተጠርተናል" የሚለውን አስተሳሰብ በምዕመኑ አእምሮ እና ልብ ውስጥ ለማስረጽ እንደሚሰሩ ተንግረዋል።
ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለመጸለይ ከሶሪያ ተነስተን መተናል
"እዚህ ብቻ መሆን እና ሶርያን መወከል በራሱ የኩራት ምንጭ ነው" በማለት በሮም ለወጣቶች ኢዮቤልዩ ከነበሩት ሶርያውያን ወጣቶች መካከል አንዱ ሐሳቡን ያጋራ ሲሆን "ይህ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ስሜት ነው። በእውነት ደስተኞች ነን። እናም አንድ ቀን በሁሉም የአለም ሀገራት ሰላም እንዲሰፍን እንጸልያለን" ብለዋል።
እሱን በማስተጋባት የእነርሱ መኖር ለሶሪያ ብቻ ሳይሆን ለመላው መካከለኛው ምስራቅ ምን ያህል ትርጉም እንዳለው የሚያስረዳ አብሮነት ጉዞ ነው ያለው ወጣቱ “በጣም ጥሩ እምነት ያላቸው በጣም ብዙ ወጣት ክርስቲያኖች እዚያ አሉ፣ ልክ እንደ ወንድም ጆርጅ" በማለት የተናገረ ሲሆን፣ ወጣቶቹ “በእነሱ ስም፣ በስማቸው እዚህ እንጸልያለን” በማለት የእኩዮቻቸው የጸሎትና የሕልም መልእክተኞች ሆነዋል።
በተለይም በሮም የመሆን እና በኢዮቤልዩ የመሳተፍ እድል የሚወክለውን ስጦታ በመገንዘብ “በተለይ ጌታ አንድ ቀን መጥተው ይህንን ልምድ እንዲኖሩ እድል እንዲሰጣቸው እንጸልያለን” ሲሉ ለቫቲካን ዜና ተናግረዋል።