የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በቫቲካን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት የዘርዓ ክህነት እጩ ተማሪዎች የሕንጸት ትምሕርቶችን የተመለከቱ ጉዳዮችን መመሪያ በማውጣት ለተግባራዊነቱ የቅድስት መንበርን ይሁንታ መጠየቅ እና ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ የተሰጠው ተልዕኮ ነው። በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ መንፈሳዊ ጥሪን በተመለከተ የእረኝነት አገልግሎት እንዲሰጥ እና የዘርዓ ክህነት ተማሪዎች በጠንካራ ሰዋዊ፣ መንፈሳዊ፣ አእምሮዋዊ እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ሕንጸት ቀጣይነት ያላቸው ትህምርቶች በበቂ ሁኔታ እንዲሰጡ የሀገረ ስብከት ጳጳሳትን ይረዳል። በቫቲካን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል ላዛሮ ዩ ሄንግ ሲክ ሲሆኑ ጸሐፊያቸው ደግሞ የእኔታ አባ አንድሬስ ገብርኤል ፌራዳ ሞሬራ ናቸው።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች እና ዳራዎች
የዚህ ጉባኤ ታሪክ (በላቲን ቋንቋ፣ 'Sacra Congregatio Cardinalium Concilii Tridentini interpretum, instituted" በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም (በትረንት ከተማ በተካሄደው የተቀደሰ የካርዲናሎች ጉባኤ፣ ምክር ቤት ተርጓሚዎች የተቋቋመ) ወደ እዚያው ዘመን የሚወስደን ሲሆን በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 224ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ነበሩት በፒየስ አራተኛ በላቲን ቋንቋ " Alias Nos" በአማርኛ በግርድፉ ሲተረጎም (ሌላኛው እኛ) በተሰኘውና እ.አ.አ በነሐሴ 2 ቀን 1564 ዓ.ም ይፋ በሆነው ሐዋርያዊ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የተቋቋመው ትክክለኛ ትርጓሜ እና በትሬንት ጉባኤ የወጡትን ደንቦች ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው። ይህ ተቋም እ.አ.አ እስከ ታኅሣሥ 31 ቀን 1967 ዓ.ም ድረስ “ማኅበረ ካህናት” የሚል ስያሜ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ “የቅዱሳት ማኅበራት ጉባኤ" የሚለውን ታሪካዊ ስሙን ይዞ ቆይቷል። በላቲን ቋንቋ "praedicate Evangelium" በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም (ወንጌል ስበኩ) በሚል አርእስት የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሮማን ኩሪያ ተሐድሶ እንዲያደረግ ያወጁበት ሐዋርያዊ መተዳደሪያ ደንብ ይፋ በሆነበት ወቅት መጠሪያው "በቫቲካን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት" በመባል መጠራት ጀመረ።
ብቃት
በሮማን ኩሪያ (የሮማን ኩሪያ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የሚረዱ አካላት እና ባለሥልጣናት ያካተተ ነው። ለትክክለኛው ሥራው አስፈላጊውን አደረጃጀት የምያስተባብር እና የምያቀርብ የቅድስት መንበር አስተዳደር አካል ነው) በሐዋርያዊ መተዳደሪያ ደንብ ላይ አጽንዖት እንደተሰጠው፣ "በቫቲካን
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት አንድ ወሳኝ አካባቢ እንዲቆጣጠር ተሰይሟል። ጥረቱ እና ተግባሩ የማህበረሰቡ ሕይወት እና የዘርዓ ክህነት ተማሪዎች የሕንጸት ትምህርት የሚያገኙባቸውን ተቋማት ማስተዳደርና ከካህናት የህንጸት ትምህርት ሂደቶች መስፈርቶች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። በተጨማሪም የበላይ አለቆች እና አስተማሪዎች በተቻለ መጠን በአርአያነት እና በትክክለኛ አስተምህሮዎች ለወደፊቱ የተሾሙ አገልጋዮች ስብዕና እንዲመሰርቱ እና እንዲያበቁ ማድረግ አለበት።
የጽ/ቤቱ ቢሮዎች
በቫቲካን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት በአራት ቢሮዎች የተዋቀረ ነው፤ አጠቃላይ የካህናትን ጉዳይ የሚከታተል ቢሮ፣ ካህናትን ከክህነት አገልግሎቶቻቸው የሚፈታ (ነጻ የምያደርግ) ቢሮ፣ የቤተ ክርስቲያን ንብረቶችን የምያስተዳድር ቢሮ፣ የመጀመሪያ እና ቀጣይነት ያለው የሕንጸት ትምህርቶችን የሚመለከቱ ቢሮዎች ናቸው። እነዚህ መሥሪያ ቤቶች የባለሥልጣኖቹን ሥራ የሚቆጣጠሩ እና በአደራ የተሰጣቸውን ጉዳይ በሚመለከት ከሊቃውንት ጋር የሚተባበሩ አራት ኃላፊዎች ወይም አለቆች የማስተባበር አደራ ተሰጥቷቸዋል።
እ.አ.አ ከ 2022 ዓ.ም ጀምሮ በቫቲካን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን እና የዝግጅት አገልግሎትን ተግባራዊ ለማድረግ ፕሮጀክት በማዘጋጀት አዲስ የግንኙነት ስልቶችን በመቅረጽ ከተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት ጋር የድጋፍ እና ሐሳብ የመለዋወጥ አውታረ መረብን ለማስተዋወቅ ያለመ እንዲሆን ተደርጎ ተቀርጿል።
በተጨማሪም የካህናትን እና የሕንጸት ጉዳዮችን የሚመለከቱ ጽ/ቤቶች ለቅዱስነታቸው እና ለካህናት (የሀገረ ስብከቱ ካህናትና ዲያቆናት) የዕውቀትና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎችን ይሰበስባሉ፣ ይጠቁማሉ፣ ያስተዋውቃሉ።
የሕንጸት ትምህርቶች የሚሰጡበት ተቋማትን የሚቆጣጠረው የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት በስተቀር ለሁሉም ሴሚኔሪዎች ወይም የዐብይ ዘርዓ ክህነት ተማሪዎች እና የትምሕርት ተቋማት ኃላፊነት አለበት።
የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ልዩ የኃላፊነት ቦታ የሕዝብ ህጋዊ አካላት ንብረት የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ንብረት አደረጃጀት እና አስተዳደርን ይመለከታል።
ካህናትን ከክህነት ማዕረጋቸው እና መንፈሳዊ ግዴታቸው እንዲፈቱ ወይም ነጻ እንዲሆኑ ሕጋዊ አካሄዶችን የምያከናውነው ቢሮ የላቲን አብያተ ክርስቲያናትን እና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት የሀገረ ስብከት እና ገዳማዊያን ካህናትን፣ ቅዱስ ከሆነው የክህነት እና የድቁና ማዕረጋቸው የተነሳ ከተሰጣቸው ግዴታዎች በህጉ መሰረት የማስተናገድ እና ከተሰጣቸው ግዴታዎች ነጻ የማድረግ ኃላፊነት አለበት።
በደጉ ሳምራዊ እና በኩሬ ዲ አርስ ፈለግ
የክህነት የሕንጸት ትምህርት መንገድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ህይወት የተለያዩ ገጽታዎችን ያጠቃልላል። በቫቲካን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ዋናው ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል፣ በአእምሮ እና በክንዶቿ እንድትነቃነቅ በአለም ውስጥ በሁሉም ቦታ የደጉ ሳምራዊ ምስል እንዲፈጠር ማድረግ ነው። የእግዚአብሔርን ምሕረት፣ የወንጌል ፍቅር፣ ብርሃን የማድረጉ ጉዳይ ነው።
የካህናት ጠባቂ ቅዱስ ዮሐንስ ማርያ ቪያኒ የክህነት አገልግሎት በተመለከተ “ካህን በምድር ላይ ምን እንደሆነ በሚገባ ከተረዳን፣ በፍርሃት ሳይሆን በፍቅር እንሞታለን" ሲል ተናግሮ ነበር።
ብፁዕ ካርዲናል ላዛሮ ዩ ሄንግ ሲክ እንዳሉት፣ ቅዱስ ኩሬ ዲ አርስ ("Cure of Ars" የቅዱስ ዮሐንስ ማርያ ቪያኒ ቅፅል ስም ነው፣ ፈረንሳዊው ቄስ በጥልቅ መንፈሣዊነቱ እና ነፍሳትን በፈውስ አገልግሎት በተለይም በምስጢረ ንስሐ አማካኝነት እንዲያገኙ በመደገፍ ይታወቃል። አብዛኛውን የክህነት ህይወቱን ያሳለፈው በአንዲት ትንሽ መንደር በፈረንሳይ እና ከዚያም ባሻገር ለሆኑ አማኞች የማጣቀሻ ነጥብ በሆነችው ትንሽ መንደር ነው) ቅድስና “በጸሎት፣ በቅዱስ ቁርባን እና መስጢረ ንስሐ የሚገኝ እንጂ ከክብር የሚመጣ” የቅድስና ዓይነት ወይም ምሳሌ የለም ነበር፣ ይህም ቅድስና “በእረኛው ልብ” ሰዎችን በማዳመጥ፣ በመውደድ እና በመምራት የተፈጠረ ነው።
ዛሬ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ፣ ለሁሉም ካህናት አርአያ ሆኖ ቆይቷል።