MAP

በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት 

በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት

በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ከአይሁድ እምነት በስተቀር ክርስቲያናዊ ካልሆኑ የሃይማኖት ተቋማት አባላት እና ቡድኖች ጋር ያለውን ግንኙነት ያስተዋውቃል እና ይቆጣጠራል። በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የተቋቋመውን የውይይት ዘዴ እና መስፈርት በመከተል እ.አ.አ በ 2019 ዓ.ም የሰብአዊ ወንድማማችነት ሰነድ የተፈረመበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ተልእኮ ከአይሁድ እምነት በስተቀር በካቶሊኮች እና በሌሎች ክርስቲያን ባልሆኑ የሃይማኖት ተቋማት መካከል ሃይማኖታዊ ወጎች መካከል መከባበርን፣ መግባባትን እና ትብብርን ማሳደግ ነው፣ ለዚህም የክርስቲያን አንድነትን የሚያበረታታ ጽ/ቤት ነው።

ከ60 ዓመታት በፊት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የተጀመረው ይህ ተግባር፣ እ.አ.አ በየካቲት 4 ቀን 2019 ዓ.ም በአቡ ዳቢ ታሪካዊውን “የሰው ልጅ ወንድማማችነት ሰነድ” በመፈረም በቀድሞ ነፍስኄር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አማካይነት ታላቅ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ካርዲናል ጆርጅ ጃኮብ ኮቫካድ በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ ሲሆን እ.አ.አ ከጥር 21 ቀን 2025 ዓ.ም ጀምሮ በፕሬዚዳንትነት መርተዋል። ጸሐፊያቸው የእኔታ ኢንዱኒል ጃናካራትኔ ኮዲቱዋኩ ካንካንማላጌ ናቸው።

ታሪካዊ ዳራ

በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት መነሻውን ያገኘው በግንቦት 19 ቀን 1964 ዓ.ም በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ በነበሩት ጳውሎስ 6ኛ በተቋቋመው፣ በላቲን ቋንቋ "Progrediente Concilio" (እየተሻሻለ የሚሄደው ምክር ቤት) በተሰኘው አጭር ሰነድ እና በተጨማሪም በላቲን ቋንቋ "Nostra Aetate" (በእኛ እድሜ) በተሰኘው ከአጭር የአስታራቂ መግለጫ ኖስትራ አቴቴት (እ.አ.አ 1965 ዓ.ም) በተሰኘው አዋጅ እና የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መዝጊያ በፊት፣ ክርስቲያን ላልሆኑ የሐይማኖት ተቋማት የተቋቋመ ጽሕፈት ቤት ነው።

እ.ኤ.አ. በ 1974 ዓ.ም ከሙስሊሞች ጋር ሐይማኖታዊ ውይይት ለማድረግ ይቻል ዘንድ አንድ ኮምሽን በዚህ ጽ/ቤት ሥር ተቋቋመ።

እ.ኤ.አ. በ1988 ዓ.ም ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በላቲን ቋንቋ "Pastor Bonus" (መልካም እረኛ) በሚል አርዕስት ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ ሕገ ደንብ መሰረት በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት የበለጠ አካታች ተፈጥሮውን በማንፀባረቅ ወደ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ደረጃ ከፍ በማለት ክርስቲያን ካልሆኑ የሐይማኖት ተቋማት ጋር የሚደርገውን ውይይት አጠናክሮ ቀጥሏል። እ.ኤ.አ. በ 2022 ዓ.ም በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት በቀድሞ ነፍስኄር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ ሕገ ደንብ መሰረት አሁን ያለውን የመጠሪያ ስሙን ለማግኘት ችሏል።

ብቃት እና የሥራ ድርሻ

በሕገ ደንቡ መሰረት በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ከሌሎች ሃይማኖቶች ተከታዮች ጋር በተገቢው መንገድ ውይይት በመደማመጥ፣ በአብሮነትና በአክብሮት እንዲካሄድ ይሠራል።

"በሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ ውይይት በድርጊት፣ በሥነ-መለኮት ሐሳቦች ልውውጥ እና በመንፈሳዊ ልምድ እንደሚካሄድ በመገንዘብ፣ በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት በሁሉም ሰዎች መካከል እግዚአብሔርን መፈለግን ያበረታታል" (አንቀጽ 149፣ ቁ. 1)።

ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጳጳሳት ጋር በተለይም በሃይማኖታዊ ውይይት ኤጲስ ቆጶስ ኮሚሽኖች አማካይነት ቤተክርስቲያንን ሰፊ በሆነው የውይይት ተልእኮ ያገለግላል።

በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ከሌሎች ሃይማኖቶች ተከታዮች ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ በክርስቲያኖች መካከል ውይይትን ያበረታታል፣ እና ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት የሃይማኖቶች ውይይት ቢሮ ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነት እንዲኖር እና በምርምር እና በውይይት ማስተዋወቅ ተነሳሽነት ይተባበራል።

ከሌሎች ሃይማኖታዊ ባህሎች ከሚወክሉ የተለያዩ ቡድኖች ጋር የውይይት መንፈስ እና ወንድማማችነትን የሚያጎለብቱ ግንኙነቶችን እና ዝግጅቶችን ይደግፋል፣ እንዲሁም በክርስቲያኖች መካከል የሃይማኖት ጥናትን የሚያበረታታ እና የሌላ እምነት ተከታዮች የክርስትና ትምህርታቸውን እንዲያጠናክሩ ይጋብዛል።

በእውቀት እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በውይይት ውስጥ የተሳተፉትን መመስረትን ያበረታታል።

በተለይም በቀድሞ ነፍስኄር በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሥር፣ በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ተልእኮ ከቤተክርስቲያን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ሆኗል፣ በዓለም አቀፍ ጉዞዎች፣ ከአቡ ዳቢ እ.ኤ.አ. በየካቲት 2019 ዓ.ም ወደ ኢራቅ፣  እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2024 ዓ.ም ወደ እስያ እና ኦሺኒያ እስከ የመጨረሻ እና ረጅሙ ጉዞው ድረስ የቀጠለ ሲሆን በዚህ ወቅት ለምሳሌ በኢንዶኔዢያ ዋና ከተማ ጃካርታ የሚገኘውን መስጊድ፣ ኢንዶኔዥያ ካቴድራል ጋር የሚያገናኘውን “የጓደኝነት ዋሻ” ባርኳል።

በቫቲካን በተለዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ቅዱስ በሆኑት ቀናት ውስጥ ወደ ተለያዩ ሃይማኖታዊ ወጎች ለምሳሌ ለረመዳን ወር ለሙስሊሞች መልእክት የመላክ ባህል አለው፣ ለቡዲስቶች ለቬሳክ ወይም ሃናማትሱሪ በዓል፣ ለሂንዱ እምነት ተከታዮች ለዲፓቫሊ በዓል፣ ለጃይን ማህበረሰቦች ለማሂቫር ጃያንት በዓል፣ ለሲክ ማሕበረሰቦች ደግሞ ፓራካሽ ዳዊስ በአል የእንኳን አደረሳችው መልዕክት የመላክ ኃላፊነት አለበት።

በሊቃነ ጳጳሳት የቀረበው መነሳሳት በእርግጠኝነት አልጎደለም። ለምሳሌ ያህል እ.አ.አ በ1986 ዓ.ም በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በአሲዚ የተጀመረው የሰላም የጸሎት ቀን፣ 50 የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ተወካዮችና 60 የሌሎች ሃይማኖቶች ተወካዮች ያሉት ሲሆን ይህም በሃይማኖታዊ ውይይቶች ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ቀን መጥቀስ ይቻላል። እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም 25 ኛው የምስረታ በዓል ላይ 180 የሚጠጉ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተወካዮች በተገኙበት በአዚዚ በተካሄደው ሁለተኛው ስብሰባ በቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ተጀመረ።

ኖስትራ አቴቴት ፋውንዴሽን

እ.ኤ.አ. በ1990 ዓ.ም የተመሰረተው ኖስትራ አኤቴት ፋውንዴሽን በሮም በሚገኘው ጳጳሳዊ የትምህርት ተቋም የሌላ እምነት ተከታይ ለሆኑ እና በውጪ ሀገር ለሚኖሩ የሌላ እምነት ተከታይ ወጣቶች የነጻ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ይሰጣል።

እነዚህ ወጣቶች ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ስለ ክርስትና እምነት ጠለቅ ያለ ግንዛቤ አግኝተው ከሃይማኖታዊ ውይይት ጋር በተያያዙ እንቅስቃሴዎች ወደ አገራቸው ይመለሳሉ።

ፋውንዴሽኑ በሃይማኖቶች መካከል ውይይትን ለማስፋፋት የታለሙ የአካባቢ ተነሳሽነቶችን ለመደገፍ እርዳታ ይሰጣል።

የኖስትራ አቴቴ ፋውንዴሽን በገንዘብ ራሱን የቻለ እና በራሱ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ነው።

 

31 Jul 2025, 10:40