የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ተግባራት እና የሥርዓተ አምልኮ ትግበራ፥ በሮማን ኩሪያ እና በዓለም ላይ ላለው ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው አገልግሎት፣ እ.አ.አ በመጋቢት 19 ቀን 2022 የታወጀ።
አንቀጽ 88
የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በተካሄደው ማሻሻያ መሠረት የተቀደሰ ሥርዓተ አምልኮን ያበረታታል። የጽ/ቤቱ የሥራ ዘርፎች የቅዱሳን ሥርዓተ አምልኮ ሥርዓትን እና ንቃትን በተመለከተ በቅድስት መንበር በሕግ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት በታማኝነት በሁሉም ቦታ እንዲከበሩ ለማድረግ በሕግ የሚመለከታቸውን ጉዳዮችን ሁሉ ያጠቃልላል።
አንቀጽ 89
1. የተለመዱ የሥርዓተ አምልኮ መጻሕፍት እትሞችን መልሶ መመርመር ወይም ለማሻሻል እና እንደ ወቅታዊ ጊዜ ሁኔታ ማብቃት የዚህ ጽ/ቤት ዋና ተግባር ነው።
2. በየአገራቱ የኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤዎች በኩል ሕጋዊ በሆነ መልኩ የሥርዓተ አምልኮ መጻሕፍትን መተርጎም፣ የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ተግባር ሲሆን ወቅታዊ በሆኑና አሁን ባሉ ቋንቋዎች መተርጎሙን ያረጋግጣል፣ እነዚህን ከአካባቢው ባሕሎች ጋር በማስማማት ዕውቅና ይሰጣል። እንዲሁም ለተወሰኑ የቤተ ክርስቲያን የሥርዓተ አምልኮ የቀን መቁጠሪያዎችን፣ የሥርዓተ ቅዳሴ ሁኔታዎች፣ የአብያተ ክርስቲያናት፣ የተቀደሰ ህይወት እና ሐዋርያዊ ሕይወት የሚኖሩ ማኅበራት የሰዓታት ጸሎቶችን በአንፃራዊው ባለስልጣን ተቀባይነት እንዲያገኙ እውቅና ይሰጣል።
3. የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የየሀገራቱን አገረ ስብከት ጳጳሳት እና ኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤዎች ውጤታማ እና ተስማሚ እርምጃዎችን በማድረግ ሥርዓተ አምልኮን በተለይም የቅዱሳት ምስጢራት አከባበርን፣ ሌሎች ምሥጢራትንና ሥርዓተ ቅዳሴን በማስተዋወቅ ለምእመናን የበለጠ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ይረዳል። ከኤጲስ ቆጶስ ጉባኤዎች ጋር፣ የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ሥርዓተ አምልኮን የተመለከቱ ጉዳዮች ከባሕል ጋር ተስማምተው እና ተሰላስለው ይሄዱ ዘንድ ሊፈጥሩ በሚችሉ ቅርጾች ላይ ማሰላሰልን ያበረታታል እና ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተስማምተው እንዲሄዱ ያግዛል።
አንቀጽ 90
1. የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የእምነት አስተምህሮ ብቃቱን ሳይጎዳ የቅዱሳት ምስጢራትን እና የህግ ጉዳዮችን እንዲሁም ቅዱሳት ምስጢራት በአግባቡ በሥርዓቱ እና በደንቡ መሰረት መፈጸማቸውን ይቆጣጠራል።
2. ከየሀገረ ስብከት ብፁዓን ጳጳሳት አቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮችን በመመርመር የድጋፍ ጥያቄዎችን ያቀርባል።
አንቀጽ 91
የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የአለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ወቅታዊ አከባበርን ያስተዋውቃል፣ ያደራጃል፣ በብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ አከባበር ላይ በመተባበር ይሠራል።
አንቀጽ 92
የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የሥርዓተ አምልኮ ሕይወትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያለው ኃላፊነት ...
1. የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የአምልኮ ሥርዓቶችን በተለያዩ ደረጃዎች በማስተዋወቅ እንዲሁም በአጉረ ስብከት ደረጃ ስብሰባዎችን ማዘጋጀት . . .
2. የሥርዓተ አምልኮ ሐዋርያዊ አከባበር፣ ውዳሴ፣ ዝማሬ እና ቅዱስ የሆኑትን ጥበቦችን ለማስተዋወቅ የተፈጠሩ ባለድርሻ አካላትን ወይም ተቋማትን በመደገፍ . . .
3. ለእነዚህ ዓላማዎች ዓለም አቀፍ ማህበራትን በማቋቋም ወይም ህጎቻቸውን በማፅደቅና መደገፍ ...
አንቀጽ 93
የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩትን የሥርዓተ አምልኮ መጻሕፍት አጠቃቀምን በተመለከተ የቅዱስ ሥርዓተ አምልኮ ሥርዓትን እና አከባበራቸውን የመከታተል ኃላፊነት አለበት።
አንቀጽ 94
የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የቅዱሳት ንዋየ ቅድሳትን ቅርጾችን ማክበር፣ ቅዱሳንን የበላይ ጠባቅ አድርጎ መሾም እና ለአነስተኛ ባዚሊካዎች ማዕረግ የመስጠት ኃላፊነት አለበት።
አንቀጽ 95
የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የሀገረ ስብከቱ ጳጳሳት የሕዝባዊ አገልግሎት ዓይነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከቤተ ክርስቲያኗ ደንቦች ጋር እንዲጣጣሙ እና ከቅዱሱ ሥርዓተ አምልኮ ጋር እንዲጣጣሙ፣ መርሆቹን በማረጋገጥ እና በልዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ፍሬያማ አፈጻጸም እንዲኖራቸው መመሪያ በመስጠት ይረዳል።
አንቀጽ 96
ሊቃነ ጳጳሳት ሊያደርሱ የሚችሉ በደሎችን ለመከላከልና ለማስወገድ በአደራ የተሰጣቸውን የቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ የሥርዓተ አምልኮ ሕይወታቸውን መምራት፣ ማስተዋወቅ እና ጠባቂ በመሆን ተገቢውን የሥርዓት አገልግሎት እንዲያከናውኑ የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ጳጳሳትን ይረዳል።
አንቀጽ 97
የአምልኮ እና የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አከባበር ሥነ-ሥረዓት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት ከአባላቱና ከአማካሪዎቹ በተጨማሪ ከተለያዩ የኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤዎች የሥርዓተ አምልኮ ኮሚሽኖች እና ከዓለም አቀፍ ኮሚቴዎች ጋር የሥርዓተ አምልኮ መጻሕፍትን ወደ ዋና ቋንቋዎች እንዲተረጎም ትብብር እና የወቅታዊ መረጃዎችን ልውውጥ ማድረግ ይችላል። በከፍተኛ የቤተ ክህነት ጥናት ተቋማት በሥርዓተ አምልኮ ዙሪያ ያበረከቱትን አስተዋፅኦም ይከታተላል።