MAP

አቡነ ተስፋዬ ታደሰ ገብረሥላሴ፣ የአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ረዳት አቡነ ተስፋዬ ታደሰ ገብረሥላሴ፣ የአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ረዳት  

ቫቲካን ለተቀደሰ ሕይወት ተቋሟ እና ለሐዋርያዊ ሕይወት ማኅበራት ጽ/ቤት አዲስ ሹመት መስጠቷ ተገለጸ!

ቫቲካን ለተቀደሰ ሕይወት ተቋሟ እና ለሐዋርያዊ ሕይወት ማኅበራት ጽ/ቤት አዲስ ሹመት መስጠቷ ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን ለተቀደሰ ሕይወት እና ለሐዋርያዊ ሕይወት ማኅበራት ጽ/ቤት ኃላፊዎችን መሾሟቸው የተገለጸ ሲሆን ብፁዕ ካርዲናል፡- አርተር ሮቼ፣ የመንፈሳዊ አምልኮ እና የቅዱሳን ምስጢራት ሥነ-ሥርዓተ አከባበርን የሚቆጣጠረው ጽ/ቤት አላፊ አድርገው ሾሟቸዋል። ሊቀ ጳጳስ ክሪስቶባል ሎፔዝ ሮሜሮ፣ የራባት (ሞሮኮ) ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቀ ጳጳስ ጆርጅ ማሬንጎ የኡላንባታር (ሞንጎሊያ) ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ፣ ሊቀ ጳጳስ ፒዬርባቲስታ ፒዛቤላ የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ (እስራኤል) የላቲን ሥርዓተ አምልኮ ፓትርያርክ፣ ጃይሜ ስፔንገር የፖርቶ አሌግሬ (ብራዚል) ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቀ ጳጳስ ጁዴ ታዴዎስ ሩዋኢቺ የዳር-ኤስ-ሰላም ታንዛኒያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብጹዕ አቡነ ጄርዚ ማኩሌቪች የኡዝቤኪስታን ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ፣ ጁሊዮ ቼዛር በሜክሲኮ የታላክስካላ ጳጳስ፣ ቱላኒ ቪክቶር ምቡዪሳ የኮክስታድ ጳጳስ፣ ደቡብ አፍሪካ መሆናቸው ተገልጿል።

በሴ/ር ሲሞና ብራምቢላ በሚመራው የቫቲካን የተቀደሰ ሕይወት የሚመለከተው እና ለሐዋርያዊ ሕይወት የሚኖሩ ማኅበራት ጽ/ቤት አዲስ ሹመት የመሰጠቱ የተገለጸ ሲሆን በዚህ መሰረ ክቡር አቡነ ተስፋዬ ታደሰ ገብረሥላሴ፣ የአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ረዳት እና አባ ስታንሊ ሉቡንጎ፣ የዛምቢያ ተወላጅ የአፍሪካ ሚስዮናውያን ማኅበር የበላይ ጄኔራል እንደሚገኙበት ተገልጿል።

 

26 Jun 2025, 15:28