MAP

ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ በአባ ቤንዚ ልደት መቶኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ በአባ ቤንዚ ልደት መቶኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ  (ANSA)

ቅድስት መንበር፥ የኒውክሌር ጦር መሣሪያን በግንባር ቀደምነት እንደምትቃወም ተገለጸ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን “እውነተኛ የእርስ በእርስ ግንኝነት እና የአብሮነት መንገዶች ግንባታ” በሚል ርዕሥ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። ብጹዕነታቸው በስብሰባው ለተካፈሉት ባሰሙት ንግግር፥ ቅድስት መንበር የኒውክሌር ጦር መሣሪያን ግንባታ በግንባር ቀደምነት እንደምትቃወመው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በእስራኤል እና በኢራን መካከል ስለተቀሰቀሰው አዲስ ጦርነት የተጠየቁት ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ የጦር መሣሪያ ትጥቅ የማስፈታት፣ የመነጋገር እና የመደራደር አስፈላጊነትን በድጋሚ ገልጸው፥ በጣሊያን በሕክምና እገዛ የሰውን ነፍስ ወደፍጻሜ ማድረስን አስመልክተው ሲናገሩ፥ እያንዳንዱ አስተያየት ወይም ውሳኔ ሰብዓዊ ክብርን የሚያስጠብቅ መሆን እንዳለበት ጠይቀዋል።

“ቅድስት መንበር፥ ኒውክሌር የጦር መሣሪያ መጠቀምን በግንባር ቀደምነት እንደምትቃወም እና ይህም ተፈጻሚ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፥ በቅርቡ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት አዲስ የጦር ግንባር እንደሆነ ተናግረዋል።

“እውነተኛ የእርስ በእርስ ግንኝነት እና የአብሮነት መንገዶች ግንባታ” በሚል ርዕሥ በሮም ማክሰኞ ሰኔ 10/0217 ዓ. ም. ጠዋት የተካሄደውን ስብሰባ የጣሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አንቶኒዮ ታጃኒም ተካፍለዋል።

በዕለቱ “አንሳ” ከተሰኘ የጣሊያን የዜና ወኪል ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ የሰጡት ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፥ የቅድስት መንበርን ትጥቅ የማስፈታት ቁርጠኝነት በድጋሚ ገልጸው፥ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ትጥቅን ማስፈታት በሰላማዊ መንገድ በውይይት እና በድርድር መከናወን አለበት ብለዋል።

በሕክምና እገዛ ነፍስን ማጥፋት

ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፥ ከ “አንሳ” የጣሊያን የዜና ወኪል፥ ነፍስን በሕክምና እገዛ መንጠቅ አስመልክቶ ለተጠየቁት ሲመልሱ፥ በጣሊያን ውስጥ በቀረበው የቅርብ ጊዜ የጥናት ውጤት አንፃር፥ ሙሉ በሙሉ ራሷን መቆጣጠር የማትችል ሴት የሚገድል መድኃኒት ሐኪሟ እንዲልክላት የጠየቀችበትን ሁኔታ በማስታወስ እና የጉዳዩን አሳሳቢነትን በመግለጽ፥ “ሕገ መንግሥታቸው ለሰው ልጅ ሕይወት ተስማሚ መሆኑ በሁሉም መንገድ መረጋገጥ አለበት” ብለዋል። አክለውም “በሕይወት ፍጻሜ ላይ ያለውን ችግር ለመቆጣጠር ብዙ ሃሳቦች አስተያየቶች መኖራቸውን ተናግረው፥ “ነገር ግን ማንኛውም ሃሳብ እና ውሳኔ ሰብዓዊ ክብርን ለማስጠበቅ የሚመለከታቸውን ሊረዳ እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

አባ ቤንዚ፥ የእርስ በእርስ ግንኝነት እና የአብሮነት መንገድ ገንቢ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፥ የዮሐንስ 23ኛ ማኅበረሰብ መሥራች የአባ ቤንዚ ልደት መቶኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር፥ “አባ ቤንዚ በጣሊያን እና በዓለም ውስጥ የቤተ ክርስቲያኗን ሕይወት ያበለጸገ የእውነታ መሥራች እና አንቀሳቃሽ ነበር” ብለው፥ የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ፥ ‘አባ ቤንዚ ትሑት እና ምስኪን የኢየሱስ ክርስቶስ ካኅን፣ ታላቅ እና አርአያነት ያለው፣ ለተናቁትም ቅርብ ነው” በማለት መግለጻቸውን አስታውሰል።

የዮሐንስ 23ኛ ማኅበረሰብ ፍሬዎች

ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፥ በዮሐንስ 23ኛ ማኅበረሰብ ውስጥ የብዙ ሰው ሕይወት ማበቡን በማስታወስ፥ ይህም በማያቆም ድህነት ውስጥ ለተዘፈቁት ጠቃሚ እንደ ነበር አስረድተዋል። “ቅዱስ ወንጌል፥ ‘ዛፍ በፍሬው ይታወቃል’ ብሎ ያስተምረናል” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፥ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1968 ዓ. ም. በአባ ቤንዚ የተቋቋመው የዮሐንስ 23ኛ ማኅበረሰብ በዚህ መርህ በመመራት መቆሚያ በሌለው ድህነትን ውስጥ የወደቁትን ለመርዳት ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል ብለዋል። ብጹዕነታቸው በማከልም “ማኅበረሰቡ ሕይወቱን ከድሆች እና ከተጨቆኑ ጋር በማድረግ፣ ከእነርሱ ጋር እንደ እውነተኛ ቤተሰብ አብሮ በመኖር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለውን ግንኙነት ያሳድጋል” ብለዋል። “ከፍተኛው መከራ ከእግዚአብሔር መራቅ ነው” የሚለውን የአባ ኦሬስቴ አስተምህሮ እና ምስክርነት ያስታወሱት ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፥ ይህም “ለሕጻናት፣ ለድሆች፣ ለተገለሉት እና ለተናቁት በሙሉ ጥልቅ የፍቅር ምልክት ነበር” ሲሉ አስረድተዋል።

 

18 Jun 2025, 17:14