ብጹዕ ካርዲናል ቸርኒ፥ ቤተ ክርስቲያን የባሕር ላይ ተጓዦችን እንድታስታውስ ጠየቁ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ መሠረት በማድረግ ባቀረቡት አስተንትኖአቸው፥ ማንኛውም እውነተኛ ሰብ ዓዊነት በክርስቲያኖች ልብ ውስጥ የሚያስተጋባ መሆኑን በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ብፁዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ አስረድተው፥ በባሕር ላይ የሚሠሩት ፍትህን፣ ሰብዓዊ ክብርን እና ደስታን አስመልክተው በሚያቀርቡት ጥያቄ ብቻቸውን እንዳልሆኑ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ዘወትር እንደምታስባቸው አረጋግጠዋል።
ስለ ዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ መጠይቅ
ብጹዕ ካርዲናል ቸርኒ ሐምሌ ወር በገባ በሁለተኛው እሑድ የሚከበረውን የባሕር ላይ መንገደኞች ቀን በማስታወስ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በየዓመቱ የሚከበረው ይህ ቀን ክርስቲያኖች ከሞት በተነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ የምሥራች ቃል፥ ሥር ነቀል በሆነ መልኩ ራሳቸውን ይበልጥ ለለውጥን እንዲጠይቁ የሚጋብዝ መሆኑን ተናግረዋል።
ብጹዕነታቸው በመቀጠልም፣ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በወደቦች እና በመርከቦች ላይ የሚሠሩት ሰዎች በምን ዓይነት መብት፣ በምን ዓይነት ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ዕርዳታ እንደሚሠሩ ለማሰብ የተጠራች መሆኗን ተናግረው፥ በተጨባጭ አነጋገር ካቶሊካዊ ምዕመናን ከኢኮኖሚው በስተጀርባ ስላለው ነገር፣ ብዙውን ጊዜ ምንም ጥቅም የማይሰጡ እና ራሳቸውን ለአድልዎ እና ለአደጋ በሚያጋልጡ ሰዎች ላይ ብርሃናቸውን እንዲያበሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የባሕር ላይ ተጓዦች ‘የተስፋ ናጋዲያን’ ናቸው
በመቀጠልም የባሕር ላይ ተጓዦችን እንደ ተስፋ ነጋዲያን እንዲታወቁ ለማድረግ ፍላጎት እናዳላቸው ገልጸው፥ የእያንዳንዱን ሰው ፍላጎት መሠረት በማድረግ በሥራ፣ በመጋራት እና እርስ በርስ በመገናኘት በክብር ለመኖር የተጠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ብጹዕ ካርዲናል ቸርኒ ስለ ተስፋ ምንነት ሲገልጹ፥ ያለ መዳረሻ የምንጓዝ ሳንሆን ነገር ግን ማንም ክብራችንን ሊሰርዝ የማይችል ሰዎች በመሆናችን ግባችንን ልናስታውስ እንደሚገባ አሳስበው፥ ሁላችንም ከአንድ ቤት የምንመጣ እና የምንመለስ በመሆናችን፥ በራሳችን እና ሕይወት ባላቸው ፍጥረታት መካከል ያለው አንድነት የበለጠ ጠንካራ እና ሕያው ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።
ባሕር ለለውጥ ይጠራናል!
ብጹዕ ካርዲናል ቸርኒ፥ መርከበኞች እና የሥራ ባልደረቦቻቸው፥ ሃይማኖታቸው ሆነ ባሕላቸው ምንም ይሁን ምን የተስፋ ምእመናን በመሆናቸው ካመሰገኑ በኋላ፣ በጦርነት ውስጥ በሚገኙ አገሮች መካከል ድልድይ እና የሰላም ነቢያት እንዲሆኑ ጋብዘዋቸዋል።
እንደዚሁም ቤተ ክኅነት በተለይም በባሕሮች፣ በወንዞች እና በሐይቆች የሚዋሰኑ ሀገረ ስብከቶች እነዚህን ቦታዎች ለለውጥ የሚጠሩ መንፈሳዊ አካባቢዎች እንዲሆኑ በማድረግ ትኩረት እንዲሰጡባቸው አደራ ብለዋል።