MAP

ሲኖዶስ በሲኖዶሳዊነት ላይ በሚል ባለፈው ዓመት የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ሲኖዶስ በሲኖዶሳዊነት ላይ በሚል ባለፈው ዓመት የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ   ( foto Agência Ecclesia)

የሲኖዶስ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ መመረጥን በደስታ ተቀበለ

የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አዲስ ለተመረጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጻፈው ደብዳቤ፥ ብጹእነታቸው “ቤተክርስቲያኒቷ ለሁሉም ክፍት የሆነች የእግዚአብሔር ቤት እና ቤተሰብ” ሆና እንድታድግ የሚረዱትን መመሪያዎች “በድፍረት እንደሚመለከቱ” ያለውን ተስፋ ገልጿል።

አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አዲስ ከተመረጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር “በአንድነት ለመጓዝ የተሰማውን ደስታ” በመግለጽ፥ ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ያላቸውን አገልግሎት ለመደገፍ ቃል ገብቷል።

እንደ ሚሲዮናዊ ቤተክርስቲያን ማደግ
ጽህፈት ቤቱ ‘እጅግ የተባረኩ አባት’ በሚል ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በላከው የደስታ መግለጫ ደብዳቤ ላይ ሲኖዶሱ “በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ የቤተ ክርስቲያን ጉዞ መሆኑን፣ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጦታ መሆኑን፣ እንደ ሚሲዮናውያን ቤተክርስቲያን እንድናድግ የሚረዳን፣ እንዲሁም ወንጌልን በትኩረት በማዳመጥ የማያቋርጥ ለውጥ የምናደርግበት” መሆኑን አስታውሷል።

ደብዳቤው በማከልም እንደገለጸው ባለፈው ዓመት በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የመጨረሻ ሰነድ ላይ የተካተቱት ሃሳቦች “ቀድሞ የተደረገው እና ወደፊት ምን መደረግ እንዳለበት የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና በአብያተ ክርስቲያናት ቡድኖች ውስጥ ሊተገበሩ ይችላሉ” ያለ ሲሆን፥ ይህም ሲሆን ለሚሲዮናዊት ሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን የሚስማማው ዘይቤ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የተሳካ እና የዳበረ ይሆናል ብሏል።

ጽሕፈት ቤቱ በቅርብ ጊዜያት መላውን ቤተ ክርስቲያን የሚያካትት ውሳኔዎችን ለሚወስኑት ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሚቀርበውን በቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የተቋቋሙትን የጥናት ቡድኖች ሥራዎችንም አንስቷል።

ለሁሉም ክፍት መሆን
“አሁን የ[ሲኖዶሱ] ጉዞ በቅዱስነትዎ መመሪያ ወደፊት ይቀጥላል” የሚለው መልዕክቱ፥ ቤተክርስቲያናችን ማህበረሰብን በትኩረት ለማዳመጥ የምትችል ቤተክርስቲያን ሆና እንድታድግ ለመርዳት፣ ለእያንዳንዱ ሰው ቅርብ እንድትሆን፣ ትክክለኛ እና የእንግዳ ተቀባይነት ግንኙነት እንዲኖር፣ ለሁሉም ክፍት የሆነ የእግዚአብሔር ቤት እና ቤተሰብ እንድትሆን ብሎም የሚስዮናውያን ሲኖዶሳዊ ቤተክርስቲያን እንድትሆን ብጹእነታቸው የሚያስተላልፉትን አቅጣጫዎች በልበ ሙሉነት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

ቀጣዩ ምዕራፍ
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሲኖዶሱ በሲኖዶሳዊነት ላይ ያካሄደውን ውጤት ለማስፈጸም ከሶስት ዓመታት ሂደት በኋላ በቫቲካን የሚካሄደውን “ልዩ ድኅረ ሲኖዶሳዊ ጉባኤ” እንዲካሄድ በማጽደቅ የሚቀጥለውን የቤተክርስቲያኒቷን ሲኖዶሳዊ ጉዞ ምዕራፍ ማስጀመራቸው የሚታወቅ ነው።

የሲኖዶሱ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች ይሄን አስመልክተው ውሳኔውን ይፋ ባደረጉበት ደብዳቤ ላይ ጉባኤው አዲስ ሲኖዶስ ሳይሆን የሲኖዶስ ማጠቃለያ ላይ የቤተክርስቲያን የ “አቀባበል” ተግባራት አካል መሆኑን አስረድተዋል።
 

14 May 2025, 14:08