MAP

እ.አ.አ 325 ዓ.ም በኒቂያ ተካሂዶ የነበረው የክርስቲያናዊ ሕበረት ጉባኤ እ.አ.አ 325 ዓ.ም በኒቂያ ተካሂዶ የነበረው የክርስቲያናዊ ሕበረት ጉባኤ  

የኒቂያው ጸሎተ ሐይማኖት የክርስቲያን ማንነት መግለጫ ነው!

የአለም አቀፉ የስነ-መለኮት ኮሚሽን “ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አዳኝ፡ 1700ኛው የኒቂያ የክርስቲያኖች ሕብረት ጉባኤ (325-2025)”፣ በሚል አርእስት የመጀመሪያውን አለም አቀፍ በጸሎተ ሐይማኖት (የሐይማኖት መግለጫ) ላይ የተንተራሰና በኢየሱስ ክርስቶስ የመዳን ኃይል፣ በአንድ አምላክ፣ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እምነት በግልጽ ያወጀውን ጉባኤ በተመለከተ መጽሐፍ ማሳተሙ ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እ.አ.አ በመጪው በግንቦት 20/2025 ዓ.ም መላው የክርስቲያን ማሕበረሰብ እ.አ.አ በ325 ዓ.ም በኒቂያ የተካሄደው የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ሕብረት ጉባኤ የተከፈተበትን 1700ኛ ዓመት ያከብራል፣ ይህም በጸሎተ ሐይማኖት (የሐይማኖት መግለጫ) ምክንያት በታሪክ ውስጥ የተመዘገበው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በአንድ አምላክ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ላይ ያለውን የመዳን እምነት አንድ ላይ የሚያሰባስብ፣ የሚገልጽ እና የሚያውጅ ነው። በኋላ እ.አ.አ በ381 ዓ.ም በቁስጥንጥንያ ጉባኤ የተጠናቀቀ፣ የኒቂያው ጸሎተ ሐይማኖት ወይም የሃይማኖት መግለጫ  በተግባር የተረጋገጠ የቤተ ክርስቲያን እምነት መታወቂያ ሆነ። በዚህ ምክንያት፣ ዓለም አቀፉ የነገረ መለኮት ኮሚሽን (ITC) በትንሿ እስያ ንጉሠ ነገሥት ቆስጠንጢኖስ የጠራው ሰባ ገጽ የሚጠጋ ሰነድ ለጉባኤው እንዲሰጥ ወስኗል። አዲሱ ሰነድ የኒቂያ አመታዊ በዓል በተስፋ ኢዮቤልዩ ወቅት የሚከበረው ፋሲካ በሁሉም ክርስቲያኖች በተመሳሳይ ቀን በሚከበርበት አመት በመሆኑ ልዩ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

“ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አዳኝ - የኒቂያ የክርስትያናዊ ሕብረት ጉባኤ 1700ኛ ዓመት (325-2025)” - ይህ በመጋቢት 25/2017 ዓ.ም የወጣው የሰነዱ ርዕስ ሲሆን - ስለዚህ በቀላሉ የአለም አቀፉ የስነ-መለኮት ኮሚሽን ሥራ ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን በእምነት እና በክርስቲያናዊው ማህበረሰብ ውስጥ የሚመሰክረው ጥልቅ ግንዛቤን ለማግኘት የሚያስችል ውህደት ሆኖ ቀርቧል።

በመጨረሻም ኒቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ የቤተክርስቲያኗ አንድነት እና ተልእኮ በአለም አቀፍ ደረጃ (ስለዚህም “ኢኩሜኒካል” (ክርስቲያናዊ ሕብረት) ወይም “ዓለም አቀፋዊ” የሚል ስያሜ) በሲኖዶሳዊ መልክ ሲገለጽ ነበር። ስለዚህም የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅት እያካሄደች ላለው ሲኖዶሳዊ ጉዞ እንደ ማመሳከሪያ እና መነሳሳት ሊታይ ይችላል።

የነገረ መለኮት ሊቃውንት

ይህ ሰነድ 124 አንቀጾች ያሉት ሰነድ ሲሆን ሰነዱ በኮሚሽኑ በየአምስት አመቱ አስጠንቶ አሥረኛው ዓመት ጊዜ የኒቂያ ቀኖናዊ ጠቀሜታ ላይ የጠለቀ ጥናት ለመጀመር የአለም አቀፉ የስነ-መለኮት ኮሚሽን (ITC) ውሳኔ ውጤት ነው። ሥራው የተካሄደው በፈረንሳዊው ቄስ አባ ፊሊፕ ቫሊን የሚመራ እና በብጹዕን ጳጳሳት አንቶኒዮ ሉዊዝ ካቴላን ፌሬራ እና ኢቲየን ቬቶ በተባሉት ንዑስ ኮሚቴ ነው። አባ ማርዮ አንጌል ፍሎሬስ ራሞስ፣ ጋቢ አልፍሬድ ሃኬም እና ካርል-ሄይንዝ መንኬ፥ እና ፕሮፌሰር ማሪያን ሽሎሰር እና ፕሮፌሰር ሮቢን ዳርሊንግ ያንግ ይገኙበታል። ጽሑፉ ልዩ በሆነ መልኩ እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተመርጦ ጸድቋል እና ኮሚሽኑ ለተቋቋመበት የሐይማኖት ጉዳዮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው እና የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ዋና ፕሬዝዳንት ለሆኑት ለካዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ ቀርቧል። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ  ይሁንታን ካገኙ በኋላ፣ ካርዲናል ፈርናንዴዝ እ.አ.አ በታኅሣሥ 16 እንዲታተም ፈቀዱ።

ሰነዱ "ዶክስሎጂ (ለእግዚአብሔር የምስጋና ሥነ ሥርዓት የሚቀርብበት መንፈሳዊ ስነ-ሥርዓትን ያመለክታል)፣  ሥነ-መለኮት እና አዋጅ (ቅዱስ ወንጌልን ማወጅ ይመለከታል" የሚል የመግቢያ ርዕስ ይዟል፣ አራት የነገረ መለኮት አስተንትኖ የያዙ ምዕራፎች፣ እና በወቅታዊው “ኢየሱስ መዳኛችን” ለሁሉም ወንዶች እና ሴቶች በተነገረው አዋጅ ላይ የመደምደሚያ ወይም የማጠቃለያ ጽሑፍ አካቷል።

የምልክቱ ዶክስሎጂያዊ ንባብ (ለእግዚአብሔር የምስጋና ሥነ ሥርዓት የሚቀርብበት መንፈሳዊ ስነ-ሥርዓትን ያመለክታል)

የመጀመሪያው ምዕራፍ፣ “የመዳን ምልክት፡ ዶክስሎጂ እና የኒቂያ ዶግማ ሥነ-መለኮት” (ቁጥር 7-47) በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ በጣም ጠቃሚ እሴቶችን አስፍሯል።  “ወደ ክርስቲያናዊ አንድነት በሚደረገው ጉዞ ላይ አዲስ መነሳሳትን” ለመስጠት በማሰብ “ሥነ-ሥርዓተ-ትምህርታዊ እና ስለዚህ ክርስቶሳዊ፣ ሥላሴያዊ እና አንትሮፖሎጂካል (ሥነ-ስብዓዊ) ሀብቶቹን ለማጉላት የምያስችሉ ምልክቶችን በማካተት ዶክስሎጂያዊ ንባብ ያቀርባል።

የኒቂያን ጉባኤ የሐይማኖት መግለጫ (ጸሎተ ሐይማኖት) የክርስቲያናዊ ሕብረት ጠቀሜታ በማመልከት ጽሑፉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ራሳቸው ደጋግመው የጠየቁትን የትንሳኤ በዓል በጋራ የሚከበርበትን ቀን ተስፋ እና ስምምነትን ይገልፃል። አንቀጽ 43 ላይ እንደ ተጠቀሰው እ.አ.አ በ2025 ዓ.ም ሁሉንም ክርስቲያኖች እንደሚወክል ይናገራል፡- “በጋራ ያለው ነገር ከሚከፋፍለን እጅግ የላቀ መሆኑን ለማጉላት ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው፡- በቤተክርስቲያን ውስጥ በተነበበው ቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እና በመንፈስ ቅዱስ ተነሳሽነት በትንሣኤና በጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ መዳን አንድ ላይ ሆነን፣ በትንሣኤና በዘላለም ሕይወት እናምናለን" የሚል አንቀጽ ተካቶበታል።

 “በመሆኑም” ይላል የአለም አቀፉ የስነ-መለኮት ኮሚሽን ሰነድ በአንቀጽ 45 ላይ “በእነሱ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነውን በዓል አስመልክቶ የክርስቲያኖች መለያየት በማኅበረሰቦች መካከል የሐዋርያዊ እንክብካቤ ምቾት ማጣት እስከ ቤተሰብ መከፋፈል ድረስ ይፈጥራል እናም ክርስቲያን ባልሆኑ ሰዎች መካከል መጥፎ ምሳሌ መሆን ለወንጌል የተሰጠውን ምስክርነት ይጎዳል" ሲል ገልጿል።

' ስናጠምቅ እናምናለን፣ እኛም እንደምናምን እንጸልያለን"

ነገር ግን ከአሥራ ሰባት መቶ ዓመታት በኋላ የኒቂያን ብልጽግና መቀበል የኒቂያ ጉባኤ እንዴት የክርስትናን ሕልውና መመገቡን እና መምራትን እንደቀጠለ ለመረዳት ያስችላል። ሁለተኛው ምዕራፍ፣ “በአማኞች ሕይወት ውስጥ የኒቂያ ምልክት” (ቁጥር 48-69) ስለዚህ፣ ከኒቂያ ጀምሮ ሥርዓተ አምልኮ እና ጸሎት በቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደበለፀጉ ይዳስሳል፣ ይህም በክርስትና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች አስተምህሮ ላይ የተመሰረተው ሰነዱ፣ “ስናጠምቅ እናምናለን፣ እናም ባመንን ጊዜ እንጸልያለን” በማለት ያስታውሳል። ክርስቲያኖች ዛሬም እና ሁልጊዜም የክርስትናን አስተምህሮ ለመመስረት ወሳኝ ከሆነው “የሕይወት ውሃ ምንጭ” እንዲቀዱ ይመክራል። ሰነዱ በሥርዓተ አምልኮ፣ በምስጢራት ልምምድ፣ በትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ በስብከት እና እንዲሁም በ 4 ኛው ክፍለ ዘመን ጸሎቶችና መዝሙራት ላይ ጸሎተ ሐይማኖት (የሃይማኖት መግለጫን) መቀበሉን የሚዳስሰው ከዚህ አንጻር ነው።

ሥነ-መለኮታዊ እና የቤተክርስቲያን ክስተት

ሦስተኛው ምእራፍ፣ “ኒቂያ እንደ ሥነ-መለኮታዊ እና የቤተ ክርስቲያን ክስተት” (ቁጥር 70-102) በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ሐሳቦችን የያዘ ሲሆን በመቀጠል ምልክቱ (መገለጫው) እና ጉባኤው “በታሪክ ውስጥ መግባቱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወደ አምላክ የመግባት እና የሰውን አስተሳሰብ መለወጥ የሚያስተዋውቅበትን የኢየሱስ ክርስቶስን ተመሳሳይ ክስተት እንዴት እንደሚመሰክሩ” ይዳስሳል።

ቤተ ክርስቲያኗ ራሷን ባዋቀረችበት እና ተልእኮዋን በምትፈጽምበት መንገድ ላይ አዲስ ነገርን ይወክላሉ። "በምሥራቃዊው የሮም ግዛት ውስጥ ባሉት አብያተ ክርስቲያናት እና በብዙ የምዕራቡ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ላይ የተከሰተውን አለመግባባት ለመፍታት በንጉሠ ነገሥቱ ተጠርቷል" ሲል ሰነዱ ገልጿል፣ "ከሁሉም የኦይኮሜኔ (“oikoumene” የሚለው ቃል (ከጥንታዊ ግሪክ οἰκουμένη፣ “የሚኖርበት ዓለም”) በመጀመሪያ የሚያመለክተው በጥንቷ ግሪክ ውስጥ የሚታወቀውን፣ የሚኖርበትን ዓለም ነው፣ እና የእንግሊዝኛው ቃል “ecumenica” ነው፥ ክርስቲያናዊ ሕበረት ይሚለውን ይገልጻል)) ይህም ኤጲስ ቆጶሳት ለመጀመሪያ ጊዜ በሲኖዶስ ተሰብስበው ነበር። የእምነት መገልጫዎች ቀኖናዊ ውሳኔዎች ለመላው ቤተ ክርስቲያን እንደ መመሪያ ሆነው ይታወጃሉ። በአዲስ መንገድ በዓለማቀፋዊ ወሰን መዋቅር፣ እና የክርስቶስን ምሥራች በታላቅነት ማወጅ ደግሞ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ የሥልጣን መሣሪያን ይቀበላል” (አንቀጽ 101) እንደ ተገለጸው።

ለሁሉም ተደራሽ የሆነ እምነት

በአራተኛውና በመጨረሻው ምዕራፍ “ለእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የሚስማማውን እምነት መጠበቅ” (ከአንቀጽ 103-120) “በኒቂያ የሐይማኖት መገለጫ እመንት ተዓማኒነት ያለው ሁኔታ በቤተክርስቲያን ተፈጥሮ እና ማንነት ላይ ብርሃን በሚፈነጥቅበት መሠረታዊ የነገረ መለኮት መድረክ ላይ ጎልቶ ቀርቧል፣ እርሷ የእውነተኛው የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ተርጓሚ፣ የአማኞች ጠባቂ በተለይም የትናንሾች እና የተጋለጮች ጠባቂ" ተደርጋ ቤተክርስቲያን ተገልጻለች።

በኢየሱስ የተሰበከው እምነት ቀላል እምነት አይደለም፣ ይላል ዓለም አቀፉ የነገረ መለኮት ኮሚሽን (ITC)።ክርስትና እራሱን ለጀማሪዎች ልሂቃን ብቻ የተገደበ እንደ ሆነ አድርጎ ራሱን አቅርቦ አያውቅም። በተቃራኒው ኒቂያ ምንም እንኳን በንጉሠ ነገሥት ቆስጠንጢኖስ ተነሳሽነት የመጣ ቢሆንም - “ወደ ቤተ ክርስቲያን ነጻነት በሚደረገው ረጅም ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው ፣ ይህም በየትኛውም ቦታ በፖለቲካ ሥልጣን ውስጥ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች እምነት ጥበቃ ዋስትና ነው።

እ.አ.አ. በ325 ዓ.ም የራዕይ የጋራ ጥቅም በእውነት ለሁሉም ምእመናን “ይገኛል” ተብሎ ነበር፣ ይህም የካቶሊክ አስተምህሮ የተጠመቁት “በእምነት መግለጫ” አለመሳሳት ነው። ጳጳሳት እምነትን በመግለጽ ረገድ የተለየ ሚና ቢኖራቸውም በመላ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሕብረት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሳይገኙ ሊወስዱት አይችሉም፣ ይህ ጽንሰ-ሐሳብ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ብዙ ጊዜ ጎልቶ ይታያል።

የኒቂያ የቋሚ ዘላቂ ጠቀሜታ

ሰነዱ የሚደመደመው በኒቂያ ከተገለጸው እምነት ጀምሮ በብዙ ትርጉሞች “ኢየሱስ ዛሬም የሁላችን አዳኝ እንደ ሆነ" እንድንሰብክ አስቸኳይ ግብዣ በማቅረብ ነው።

በመጀመሪያ ፣ የዚያ ጉባኤ እና ከእሱ የመነጨው ምሳሌያዊ ጠቀሜታ ራሳችንን “ሁሉም ይደንቁ ዘንድ በክርስቶስ ታላቅነት መገረም” እና “ለእርሱ ያለንን የፍቅር እሳት ለማነቃቃት” መፍቀድን መቀጠል ነው፣ ምክንያቱም “በኢየሱስ 'ሆሞኡሲዮስ' (ኮንሰብስተንሻል ... በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎ ከክርስቶስ ጋር አንድ ባህሪይ ያለን መሆኑን ያሳያል) ከአብ ጋር ጭምር... እግዚአብሔር ራሱ ከሰብዓዊነታችን ጋር ራሱን ለዘላለም አቆራኝቷል።

በሁለተኛ ደረጃ “እውነታውን” ችላ ማለት ወይም “ዓለምን ከሚያሰቃዩ እና ሁሉንም ተስፋዎች የሚያበላሹ ከሚመስሉ መከራዎች እና ውጣ ውረዶች መራቅ” እና በተመሳሳይ ጊዜ ባህል እና ባህሎችን ማዳመጥ ማለት ነው።

በሦስተኛ ደረጃ፣ እራሳችንን “በተለይ በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን መካከል ላሉ ታናናሾች ትኩረት መስጠት” ማለት ነው፤ ምክንያቱም በታሪክ “የተሰቀሉት”፣ “ተስፋና ጸጋ የሚያስፈልጋቸው” ሁሉ “ከእኛ መካከል የሚኖሩ ክርስቶሶች” ናቸው። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የተሰቀለውን ኢየሱስን መከራ በመረዳት፣ በተራቸው፣ “ሐዋርያት፣ አስተማሪዎች፣ የባለጠጎችና የሐብታሞች ወንጌላውያን” ሊሆኑ ይችላሉ።

በመጨረሻም አዋጅ “አንዲት፣ ቅድስት፣ ካቶሊካዊት እና ሐዋርያዊት” እና “ዓለምአቀፋዊ የድኅንነት ምስጢር” የሆነችበትን አስደናቂ ነገር ለዓለም በማሳየት “እንደ ቤተ ክርስቲያን” ወይም ይልቁንም “በወንድማማችነት ምስክርነት” መከናወን አለበት። በተመሳሳይ ጊዜ ምልክቱ የሚተረጉመውን የቅዱሳት መጻሕፍት ውድ ሀብት ያሰራጫል-የፀሎትን፣ የሥርዓተ አምልኮን እና የምስጢራትን ብልጽግና በኒቂያ ከተነገረው ጥምቀት እና ከየቤተክርስቲያን አስተምህሮ ብርሃን፥ ሁልጊዜ የሚያተኩረው በሞትና በኃጢአት ላይ ድል ባደረገው ክርስቶስ ላይ ነው እንጂ በተቃዋሚዎች ላይ አይደለም፤ ምክንያቱም በፋሲካ ምስጢር ውስጥ ተሸናፊዎች ስለሌሉበት፣ ከፍጻሜው ተሸናፊ ሰይጣን፣ ከፋፋይ መንፈስ ከሆነው በቀር።

ባለፈው ህዳር 28 አለም አቀፍ የስነ-መለኮት ኮሚሽን አባላት በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሥራቸውን በማመስገን “በኒቂያ ስለተነገረው የእምነት መገለጫ ወቅታዊነት ላይ ብርሃን ለመስጠት ታስቦ” እና “የምእመናንን እምነት ለመንከባከብ እና ለማጥለቅ (ለማስረጽ) እንዲሁም የኢየሱስን አምሳያ መሰረት በማድረግ ለአዲሱ የክርስቶስ ባሕላዊ ግንዛቤን፣ ነጸብራቆችን እና ጠቃሚ ምክሮችን ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ሰነድ ያለውን ጠቀሜታ በማጉላት ስራቸውን ያመሰገኑት በአጋጣሚ አይደለም።

የጥናት ቀን

“የእግዚአብሔር ልጅ፣ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ 1700ኛ ዓመት የምስረታ በዓል (325-2025)” በሚል መሪ ቃል በጳጳሳዊ ኡርባኒያና ዩኒቨርሲቲ  በመጪው ግንቦት 20/2025 ዓ.ም ቀን ከቀኑ 9፡00 እስከ ቀኑ 7፡30 የሥነ-መለኮት ሊቃውንት እና ሌሎች የሰነድ ባለሙያዎችን በማሳተፍ የጥናት ቀን ይካሄዳል።

የእግዚአብሔር ልጅ አዳኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ ቃል - የኒቂያ የክርስቲያናዊ ሕብረት ጉባኤ (325-2025) 1700ኛ ዓመት የምስረታ በዓል፣ ክንውን በጣሊያንኛ ቋንቋ በአለም አቀፉ የስነ-መለኮት ኮሚሽን ድህረ ገጽ ላይ ይገኛል።

 

04 Apr 2025, 15:10