‘ላ ቺቪሊታ ካቶሊካ’ የተመሰረተበትን 175ኛ ዓመት አከበረ!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ይህ ወቅታዊ እትም 'ላ ሲቪልታ ካቶሊካ' የተመሰረተበትን 175ኛ ዓመት በአሁኑ ወቅት እያከበረ ይገኛል፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እና የጣሊያን ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በተገኙበት ይህ 175ኛ አመት የምስረታ በዓል ሥነ ሥርዓት ተከብሯል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በበዓሉ ላይ ባይሳተፉም በበዓሉ ላይ በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልእክት “የሁሉንም ድምፅ የሚያዳምጥ እና ለልብ መልካም የሚያደርግ የዋህነትን የሚያንጸባርቅ ጥሩ ጋዜጠኝነትን” አወድሰዋል።
175 ዓመታት እንደ "ወዳጃዊ መገኘት፣ የዓለምን ክስተቶች በእምነት ብርሃን ለመተርጎም ጠቃሚ መረጃዎችን በመጠቆም የሥራ ነው" ሲሉ በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ለ175 ዓመታት “ለቅድስት መንበር እና ለቤተ ክርስቲያን የማሰብ ችሎታ ያለው አገልግሎት፣ ለእውነት ጠንካራ አክብሮት በመስጠት “ለመገናኘትና ለመነጋገር” ቦታ በመስጠት 'ላ ቺቪልታ ካቶሊካ' በትጋት ሰርቷል ሲሉ ቅዱስነታቸው አወድሰዋል።
የቅድስት መንበር ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እና የጣሊያኑ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በተገኙበት 175ኛው የ“ላ ቺቪልታ ካቶሊካ” የምስረታ በዓል ማክሰኞ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም ሲከበር የበዓሉ ሥነ ሥርዓት የተከፈተው በዚህ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልእክት ነበር።
'ላ ቺቪልታ ካቶሊካ' እ.ኤ.አ. በመጋቢት ሚያዝያ 6 ቀን 1850 ዓ.ም በብፁዕ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዩስ ዘጠነኛ ትእዛዝ የተመሰረተ ሲሆን እጅግ ጥንታዊ ከሆኑ መጽሔቶች አንዱ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከሊቃነ ጳጳሳት እና ከቅድስት መንበር አቋሞች ጋር በመተባበር ታሪክን፣ ፖለቲካን፣ ባህልን፣ ሳይንስንና ጥበብን ከክርስትና እምነት አንፃር የማንበብ እና የመተርጎምያ መሣሪያ ሆኗል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላኩት መልእክት ይፋ የሆነው በአራት ሺኛው የ'ላ ቺቪልታ ካቶሊካ' መጽሔት እትም በተለቀቀበት ወቅት ላይ እንደጻፉት "በዓይነቱ ልዩ" የሚል ጽሑፍ አስፍረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ሰራተኞቻቸው ይህንን ተግባር እንዲቀጥሉ በደስታ እና በጥሩ ጋዜጠኝነት “የሁሉንም ድምጽ በሚያዳምጥ እና ለልብ መልካም የሚያደርግ የዋህነትን በማሳየት” የሚል ጽሑፍ አስፍረዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከቫቲካን ዜና ጋር ቆይታ ያደረጉት ለመጽሔቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረከቱት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑት ካህን አባ ዊልያም ማኮርሚክ እንዳሉት ቀኑ "ያለፈውን ታሪካችንን የምናከብርበት ብቻ ሳይሆን ዛሬ ዓለምን እንድናገለግል የተጠራንበትን መንገድ የምንቀበልበት ወቅት ነው" ብለዋል።
የሰላም ቁርጠኝነት
ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በበኩላቸው መጽሔቱን "አገራት ክርስቲያናዊ ራዕይን እንዲያዳብሩ ይረዳል" በማለት አወድሰዋል። ይህን ያደረገው ለሁለት ምዕተ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ነው ያሉት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በተለይም ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ በሆኑ ወቅቶች ለምሳሌ በቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ የተጀመረው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጾ መጽሔቱ ማበርከቱን ገልጸዋል።
“ውድ ኢየሱሳውያን፣ ከብፁዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ ዘጠነኛ ጀምሮ ሁል ጊዜም በድፍረት አብረዋችሁ የሚሄዱትን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን እና የቀድሞ አባቶቻችሁን ቃል ከፍ አድርጋችሁ መመልከታችሁን ቀጥሉ” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን "175 ኛውን የምስረታ በዓል ለማክበር የኢየሱሳዊያንን ማህበር ባህላዊ እና ትምህርታዊ ቁርጠኝነት በአመስጋኝነት በማስታወስ ነው" በማለት መጽሔቱ "በዲጂታል አለም ውስጥ መገኘቱ" ልዩ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
የሕትመቱ “ብቁ እና ለጋስ ቁርጠኝነት” “በማንኛውም ሁኔታ ለሰው ልጅ ክብር መከበር” እና ቅድስት መንበር ብቻ ልትቀበለው ከሚችለው “ሰላም ማስፈን” ጋር አብሮ የሚሄድ ነው" ያሉት ካርዲናል ፓሮሊን “አዳዲስ መንገዶችን ለመክፈት ድፈሩ፣ በዓለማችን ውስጥ የተስፋ ምልክቶችን ለማሳወቅ" ትጉ ብለው የመጽሔቱን ሰራተኞች ካወደሱ እና ካመሰገኑ በኋላ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ንግግራቸውን ደምድመዋል።