MAP

ካርዲናል ፓሮሊን ‘ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ይህን የቆሰለውን የሰው ልጅ ይባርኩ’ ማለታቸው ተገለጸ!

ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ 20ኛ ዓመት የሙት ዓመት ምክንያት በማድረግ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በስብከታቸው ቤተ ክርስቲያንንና ዓለምን በጥልቅ የቀረጹ ሊቀ ጳጳሳትን ውርስ ዘክረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የመጨረሻ ጊዜያት ላይ በማንፀባረቅ፣ ብፁዕ ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን፣ ጳጳሱ በመስቀል መንገድ ጸሎት ወቅት መስቀሉን ሲያቅፉ የሚያሳዩትን ኃይለኛ ገጽታ ያስታውሱት ካርዲና ፔትሮ ፓሮሊን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይን ከሚመለከቱት መስኮት በጸጥታ የሰጡት የትንሳኤ እሑድ ቡራኬ፣ እና እረኛቸውን ለመሰናበት የተሰበሰበውን ታላቅ ሕዝብ አስታውሰዋል።

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በመጋቢት 24/2017 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መስዋዕተ ቅዳሴን ባሳረጉበት ወቅት ቀሳውስት፣ ገዳማዊያን/ገዳማዊያት፣ ሊቃነ መናብርት እና ምእመናን በተገኙበት በምስጋና እና በደስታ መንፈስ ሟቹን ሊቀ ጳጳስ ለማሰብ ተገኝተው ነበር።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የዛሬ 20 አመት ገደማ በሞት ከተለዩ በኋላ “እርሳቸው ራሳቸውን መሃሪ በሆነው በእግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ስያስቀምጡ የዓለም ሕዝብ ደግሞ በወቅቱ ከእርሳቸው ጋር በጸሎት አንድ ሆኖ ይጠባበቅ ነበር" ብለዋል ካርዲናል ፓሮሊን።

ከዮሐንስ ወንጌል በመጥቀስ “ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው” (ዮሐ 5፡24) ይህ እምነት እና ውሳኔ፣ ሟቹን ሊቀ ጳጳስ በማያወላውል ተልእኮው አፅንቶዋቸዋል፣ ይህም ፈተናዎችን በሚገርም ድፍረት እና ታማኝነት እንዲጋፈጡ አድርጓቸዋል ሲሉ ካርዲናል ፓሮሊን በስብከታቸው ገልጸዋል።

በስብከታቸው ላይ በትውልድ ፖላንዳዊ በሆኑት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊን በእግዚአብሔር እይታ ስር የመኖር ጥልቅ ስሜትን አጉልተው ገልጸዋል፣ በዚህ አንጻር እርሳቸው የነበራቸውን ነጸብራቅ በመጥቀስ፣ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የገለጠላቸው “የመጀመሪያ ባለ ራእይ” ሲሉ ገልጿል። ካርዲናል ፓሮሊን ስብከታቸውን ሲቀጥሉ “በእግዚአብሔር ፊት ያሳዩትን ግልጽነት፣ ለእውነት የሰጡት ፍርሃት የለሽ ምሥክርነት፣ ለሰብዓዊ ክብር ሲሉ ያለመታከት ጥበቃና የወንጌል ማወጁ መሠረት ነው” ብለዋል።

"በእግዚአብሔር ፊት የነበረው የሕይወታቸው ግልጽነት፣ ለእውነት ያለ ፍርሃት የሰጡት ምስክርነት፣ የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር ይጠበቅ ዘንድ ያደረጉት ጥረት እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ መሥራታቸው የወንጌል ማወጁ መሠረት ነው ሲሉ ካርዲናል ፓሮሊን ተናግረዋል።

መለኮታዊ ጥበቃ

በምስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ካርዲናል ፓሮሊን ያደርጉት ስብከት ዋና ጭብጥ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በራሳቸው ሕይወት ውስጥ መለኮታዊ አገልግሎትን ማወቃቸው እንደ ነበረ ገልጸዋል። እ.ኤ.አ. በ1981 የተካሄደውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የጳጳሱን ቃል በማስታወስ፣ ካርዲናል ፓሮሊን፣ ካሮል ዎጅቲላ (ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሳይሆኑ በፊት የነበራቸው የመጠሪያ ስም ነው) የእርሳቸው  ህልውና እንደ የእግዚአብሔር ስጦታ እንዴት እንዳዩት፣ ቤተክርስቲያኗን ለማገልገል የነበራቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በመንፈሳዊነት በሰጡት ምስክርነት "የመለኮታዊ ጥበቃ አገልግሎት በተአምራዊ መንገድ ከሞት አዳነኝ። የሕይወትና የሞት ብቸኛ ጌታ የሆነው እርሱ ራሱ ሕይወቴን አራዘመልኝ፣ በሆነ መንገድ አዲስ አድርጎ መልሶ ሰጠኝ" ሲሉ ጽፈው እንደ ነበረ ካርዲናል ፓሮሊን አስታውሰዋል።  ይህ የተልእኮ ስሜት፣ ካርዲናል ፓሮሊን እንደተናገሩት ቤተክርስቲያንን ወደ ሦስተኛው ሺህ ዓመት የመምራት ሚናቸውን አስቀድሞ ባዩት በብፁዕ ካርዲናል ስቴፋን ዊስዚንስኪ ምክር ተቀርጾ ነበር ያሉ ሲሆን ይህ ትንቢታዊ መመሪያ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሊቀ ጳጳሱን የሚገልጸውን የዓላማ ግልጽነት እንደሰጣቸው ተናግሯል።

አትፍሩ

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፓሮሊን እ.አ.አ በ2000 ዓ.ም. ታላቁ ኢዮቤልዩ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያደረጉትን ታሪካዊ ሚና አንፀባርቀዋል።

“ለቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ፣ ክርስቶስ የታሪክ ማዕከል ነበር፣ እናም በቤዛዊው ብርሃን ትርጉሙን እንደገና እንዲያገኝ ዓለምን ጠሩ" ያሉት ካርዲናል ፓሮሊን ለቤተክርስቲያን ያቀረቡትን ግብዣ በማስታወስ “ወደ ጥልቁ ምራ ” (በላቲን ቋንቋ 'Duc in altum')፣ የሚለው ቃላቸው ዛሬም ማስተጋባቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል፣ ይህም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን “በተልእኮ ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን” የሚል ራዕይ አነሳስቷል። ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በላቲን ቋንቋ " Novo Millennio Ineunte (በአዲሱ ሚሊኒዬም መጀመሪያ ላይ) በተሰኘው መልእክታቸው ላይ እንደጻፉት “አትፍሩ፣ ለክርስቶስ በሮችን ክፈቱ!” ሲሉ መግለጻቸውን ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አክለው ገልጸዋል።

ጦርነት ሁሌም ሽንፈት ነው።

ለሰላምና ለሰብአዊ ክብር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ደጋፊ የነበሩት ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ድምፅ ለተጨቆኑት ሰዎች መከላከያ እና ጦርነትን በመቃወም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ነበር። ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፣ “ንግግሮቻቸው ሰሚ ባላገኙበት  ጊዜም እንኳን፣ ለሰላም የነበራቸው ቁርጠኝነት የማይናወጥ ሆኖ ነበር፣ ይህም የቤተክርስቲያኗን ትንቢታዊ ምስክርነት ይዟል" ያሉ ሲሆን “ጦርነት ለሰው ልጆች ምንጊዜም ሽንፈት ነው” ሲሉ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጦርነትን ለማስወገድ የተማጸኑበትን መንገድ አስታውሷል።

ካርዲናሉ ፓሮሊን  የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አማላጅነት በመማጸን ነበር ስብከታቸውን ያጠናቀቁት። የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በነዲክቶስ 16ኛ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከ20 ዓመታት በፊት ምእመናን ወደ እርሳቸው እንዲመለሱ በተጋበዙበት የቀብር ሥነ ሥርዓት ወቅት የተናገሩትን ቃል በማስተጋባት “ቅዱስ አባታችን ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ባርከን፣ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ፍቅር እንደገና መገንዘብ እንችል ዘንድ ይህችን የተስፋ ቤተ ክርስቲያን፣ ክብሩንና ጥሪውን በመፈለግ የቆሰለውን የሰው ልጅን ባርከው” በማለት ጸልየው እንደ ነበረ አውስተዋል።  

"ቅዱስ አባታችን ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሆይ ይባርኩን! የእግዚአብሔርን ምሕረትና ፍቅር እንደገና እንገነዘብ ዘንድ ይህን የተስፋ ቤተ ክርስቲያን፣ ክብሩንና ጥሪውን ፍለጋ የቆሰለውን የሰው ልጅ ባርኩ" ብለው የመማጸኛ ጸሎት ካደረጉ በኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

03 Apr 2025, 15:28