MAP

ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድርዜይ ዱዳ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድርዜይ ዱዳ   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የፖላንድ ፕሬዝዳንትን ተቀብለው አነጋገሩ!

ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድርዜይ ዱዳ እና አጃቢዎቻቸውን በቫቲካን ተቀብለዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሕልፈት 20ኛ ዓመት እና የፖላንድ የመጀመሪያው ንጉሥ የንግሥና ሺህ ዓመት የሚከበርበት ወቅት ምክንያት በማድረግ ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የፖላንድ ፕሬዝደንት አንድርዜይ ዱዳ አርብ ጠዋት መጋቢት 19/2017 ዓ.ም በቫቲካን ከብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት መግለጫ እንዳስታወቀው “ስብሰባው የተደረገው የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 20ኛ የሙት አመት ዋዜማ እና የፖላንድ የመጀመሪያው ንጉስ ቦለስላው ክሮብሪ የንግስ በዓል በሚከበርበት በሚሊኒየም ዝግጅት ላይ ነው" ሲል መግለጫው አትቷል።

በርካታ የጋራ ጉዳዮች ተዳሰዋል። ውይይቱ በኋላ ወደ ወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች በተለይም በዩክሬን ጦርነት እንዲሁም በአውሮፓ ደህንነት እና ሰላም ላይ ትኩረት አድርጓል።

ፕረዚደንት ዱዳ ከሐሙስ ጀምሮ በቫቲካን ይገኛሉ፣ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ቅዱስ በር የኢዮቤልዩ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ከዚያም ከቀዳማዊት እመቤት አጋታ ኮርንሃውዘር-ዱዳ ጋር በካሮል ዎዮቲላ መቃብር ላይ ጸሎት አድርገዋል፣ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

28 Mar 2025, 16:17