MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የንስሐ አባቶች የምሕረት አገልጋዮች እንዲሆኑ ያበረታታሉ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምእመናን በእርቅ እና በመታደስ መንገዳቸው ላይ ሲጓዙ “የምሕረት አገልጋዮች” እንዲሆኑ ምስጢረ ንስሐ የምያስገቡ ካህናትን ጋብዘዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ፣ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም ባስተላለፉት መልእክት፣ በተለይ እ.አ.አ በ2025 የቅዱስ ዓመት የንስሐ አባቶች ልዩ ሚና ላይ አስተንትነዋል።

የማበረታቻ መልእክት ሐዋርያዊ ንስሐን በተመለከተ በተካሄደው 35ኛው የውስጥ መድረክ ላይ ለተሳተፉ ተሳታፊዎች የነበረ ሲሆን "ምህረትን ማክበር በተለይም የኢዮቤልዩ መንፈሳዊ ተጓዦችን ማክበር ትልቅ እድል ነው፡ እግዚአብሔር በፀጋው የምሕረት አገልጋዮች አድርጎናል፣ የምንቀበለው ስጦታ እኛ እራሳችን በመሆናችን የእርሱን ይቅርታ ለመቀዳጀት ነው" ብሏል።

ከመጋቢት 16-19/2017 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ክስተት፣ ለንስሐ አባቶች ከአገልግሎታቸው አስፈላጊነት አንፃር ቀጣይነት ያለው የሕነጻ ትምህርት ይሰጣል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ውድ ወንድሞች” ብለው መልእክታቸውን ሲጀምሩ ጸሎት የአገልግሎታቸው መሠረት በመሆኑ የጸሎት ሰዎች እንዲሆኑ አሳስቧቸዋል።

"በጸሎት የአገልግሎታችሁ መሰረት ተጥሏል፣ በዚህም የኢየሱስን ስራ የምታራዝሙበት፣ አሁንም እና ሁል ጊዜም የሚደገመው፡- እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም በኋላ ደግመሽ  ኃጢአት አትስሪ" (ዮሐንስ 8፡11) የሚለውን ቃል ደጋግመን መጠቀም ይኖርብናል ሲሉ በመልእክታቸው ገልጸዋል።

ቤተ ክርስቲያን የኢዮቤልዩ ዓመትን ስታከብር፣ ቅዱስ አባታችን እንደገለጹት “ይህ የጌታ የነጻነት ቃል በመላው ቤተ ክርስቲያን ይጮኻል (…) ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ የሚፈሱትን የልብ መታደስን የሚያመጣ እና ለአዲስ ወንድማማችነት ግንኙነት መንገድ የሚከፍት ይሁን" ሲሉ በመልእክታቸው አስፍረዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም በምሕረት እና በሰላም መካከል ያለውን ትስስር አጉልተው ገልጸው እውነተኛ ሰላም ከእግዚአብሔር ምሕረት የተወለደ እና የማያሳፍር ተስፋን እንደሚያመጣ አረጋግጠዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልእክታቸውን ሲያጠቃልሉ የንስሐ አባቶችን ለአገልግሎታቸው  ምስጋናቸውን ገልጸው ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አደራ ሰጥተዋል።

28 Mar 2025, 16:14