አዲስ የቤተክርስቲያን አኃዛዊ መረጃዎች የሚያሳዩት የካቶሊክ ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነው!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የቫቲካን ማተሚያ ቤት (LEV) እ.አ.አ የ2025 ዓ.ም የጳጳሳዊ ዓመታዊ መጽሐፍ እና በላቲን ቋንቋ "Annuarium Statisticum Ecclesiae" እ.አ.አ 2023ን (የ2023 የቤተክርስቲያኗ ዓመታዊ መጽሐፍ) አሳትሟል፤ ይህም የቫቲካን አካል በሆነው የቤተክርስቲያን ስታቲስቲክስ ማእከላዊ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት ይፋ የሆነ ነው።
በጳጳሳዊ ዓመታዊ መጽሐፉ ላይ የተዘገበው መረጃ እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ ስለምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት በተመለከተ መረጃ ይሰጣል። እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም አንድ የቤተ ክርስቲያን መንበር ተቋቁሟል። ሦስት የኤጲስ ቆጶስ መንበር ወደ ሜትሮፖሊታን (በዋና ከተማ የሚገኝ የመጀመርያ አገረ ስብከት) ደረጃ ከፍ ብለዋል፤ ሰባት አዳዲስ አገረ ስብከቶች ተቋቁመዋል፣ አንድ የኤጲስ ቆጶስ መንበር ወደ ሊቀ ጳጳስ መንበርነት ከፍ ብሏል፣ ሐዋርያዊ አስተዳደር ደግሞ ወደ ሀገረ ስብከት ደረጃ ከፍ ብሏል።
በላቲን ቋንቋ "Annuarium Statisticum Ecclesiae የ2022–2023" (እ.አ.አ የ2022-2023 ዓ.ም) አመታዊው የቤተክርስቲያን ስታቲስቲካዊ ግንዛቤን ጨምሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የሐዋርያዊ አገልግሎት ሰጪ እንቅስቃሴን በሚመለከቱ ዋና ዋና የቁጥር ክስተቶች ቅጽበታዊ እይታ ያቀርባል።
ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር
እ.አ.አ በ2022 እና 2023 ዓ.ም መካከል ያለው የአለም ካቶሊክ ምዕመናን ህዝብ ቁጥር በ1.15 በመቶ ጨምሯል፣ ከ1.39 ቢሊዮን ወደ 1.406 ቢሊዮን ገደማ ከፍ ብሏል፣ ይህም በመቶኛ ሲሰላ ካለፉት ሁለት አመታት ጋር ተመሳሳይ ነው። የተጠመቁ ካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር ስርጭት በተለያዩ ጂኦግራፊያዊ (መልክዓ ምዳርዊ) አካባቢዎች ይለያያል፣ በእያንዳንዱ አህጉር የተለያዩ የስነ-ሕዝብ መረጃዎች መሰረት ማለት ነው።
አፍሪካ ከመላው በፕላኔታችን ላይ ከሚኖሩ የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር ውስጥ 20% ያህሉን ይይዛል፣ እናም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጣም ተለዋዋጭ በሆነ የስርጭት ሁኔታ ይገለጻል። የካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር እ.አ.አ በ 2022 ዓ.ም ከነበረበት ከ 272 ሚሊዮን ወደ 281 ሚሊዮን እ.አ.አ በ 2023 ጨምሯል፣ በአንፃራዊነት በ 3.31% የጭማሪ ልዩነት አሳይቷል። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተጠመቁ የካቶሊክ ምዕመናን የቁጥር ብዛት የመጀመሪያ ቦታ መያዟን አረጋግጣለች፣ ወደ 55 ሚሊዮን የሚጠጉ ምዕመናን በአገሪቷ ውስጥ ይኖራሉ፣ናይጄሪያ በ 35 ሚሊዮን ይከተላል፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኬንያም ጉልህ የሆኑ አኃዞችን አስመዝግበዋል።
እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም በ0.9% እድገት በማስመዝገብ፣ አሜሪካ 47.8% የአለም ካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙባት አህጉር በመሆን አቋሟን አጠናክራለች። ከእነዚህ ውስጥ 27.4% የሚሆኑት በደቡብ አሜሪካ ይኖራሉ (ብራዚል 182 ሚሊዮን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የሚገኙባት አገር ስትሆን አጠቃላይ በአለም ደረጃ 13% የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ይወክላል እና ከፍተኛ የካቶሊልክ ምዕመናን ሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ሆና ቀጥላለች)፣ 6.6% በሰሜን አሜሪካ እና የተቀረው 13.8% በመካከለኛው አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር ከጠቅላላው የህዝብ ብዛት ጋር ሲነጻጸር አርጀንቲና፣ ኮሎምቢያ እና ፓራጓይ ተለይተው ይታወቃሉ፥ በእነዚህ 3 አገራት ውስጥ የሚገኙት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር ከአጠቃላይ የሕዝብ ቁጥራቸው ውስጥ ከ90% በላይ ነው።
የእስያ አህጉር የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር የ0.6 በመቶ እድገት በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበ ሲሆን እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም ይህ አኃዝ ከአለም የካቶሊክ ምዕመናን የህዝብ ቁጥር አንጻር ሲታይ 11% አካባቢ ነው። እ.ኤ.አ. በ 2023 ዓ.ም 76.7% የደቡብ ምስራቅ እስያ ካቶሊክ ምዕመናን አኃዝ ቁጥር ውስጥ በፊሊፒንስ ከሚገኙት 93 ሚሊዮን ካቶሊካዊያን ምዕመናንን ጨምሮ በህንድ 23 ሚሊዮን የካቶሊክ ምዕመናን ይገኛሉ።
አውሮፓ፣ 20.4% የዓለምን የካቶሊክ ማህበረሰብን የምታስተናግድ አህጉር ስትሆን እራሷን እንደ ትንሿ የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር የሚገኝባት ተለዋዋጭ አካባቢ አድርጋ አረጋግጣለች፣ ይህም የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር በ 0.2% ብቻ ጨምሯል። ይህ ልዩነት በሌላ በኩል፣ ከሞላ ጎደል የቆመ የስነ-ሕዝብ ተለዋዋጭነት ቁጥር አንፃር፣ በግዛት መገኘት ላይ መጠነኛ መሻሻልን ያመጣል፣ ይህም እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም ወደ 39.6% ይደርሳል። ጣሊያን፣ ፖላንድ እና ስፔን የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር ከሦስቱ አገራት ከነዋሪው ህዝብ ቁጥር አንጻር በመቶኛ ሲሰላ ከ90% በላይ የሚሆነውን ሕዝብ ይወክላል።
የኦሺያኒያ አህጉር የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር በ2023 ዓ.ም ከ11 ሚሊዮን በላይ ነበር፣ ይህም ከ2022 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር የ1.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
የጳጳሳት ቁጥር እያደገ መጥቷል
በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአሁኑ ወቅት የሚገኙት ጳጳሳት ቁጥር ከባለፈው ወቅት አንጻር ሲታይ 1.4% እድገት አሳይቷል፣ እ.አ.አ በ2022 ዓ.ም 5,353 ጳጳሳት ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም ወደ 5,430 ከፍ ብሏል፣ በዚህ መሰረት 77 የሚሆኑ ጳጳሳት በቁጥር ጨምረዋል። ይህ የእድገት አዝማሚያ በሁሉም አህጉራት ይታያል ፣ ከኦሺያኒያ በስተቀር ፣ የጳጳሳት ቁጥር በባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ ምንም የቁጥር ልዩነት አላስመዘገበም።
አንጻራዊው ልዩነት ለአፍሪካ እና እስያ በተወሰነ ደረጃ ጎልቶ የሚታይ ሲሆን አውሮፓ እና አሜሪካ ከአለም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት አማካይ አኃዝ በታች ነው። በአሜሪካ እና በአውሮፓ ከፍተኛ መጠን ያለው የጳጳሳት ስብስብ ከእያንዳንዱ አህጉራዊ እውነታዎች አንጻራዊ ጠቀሜታ አንጻር የእያንዳንዱ አህጉር አንጻራዊ ክብደት በጊዜው ሳይለወጥ እንደሚቀር ልብ ሊባል ይችላል። በአፍሪካ የጳጳሳት ድርሻ እ.አ.አ በ2022 ከነበረበት 13.8% እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም ወደ 14.2% ከፍ ብሏል።
እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም በተናጥል አኃዝ የአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ቁጥር ከአህጉር ወደ አህጉር በእጅጉ ይለያያል። የአለም አማካኝ አኃዝ የምያሳየው በተናጥል በአንድ ጳጳስ ሥር 259,000 የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንደሚገኙ መረጃዎች የምያሳዩ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ 365,000 እና 334,000 መጠን ያለው አኃዝ በቀድም ተከተል በአፍሪካ እና አሜሪካ አህጉራት ተመዝግቧል። በተለይም ኦሺያኒያ ውስጥ ያለው ሁኔታ በጣም ጥሩ ነው፣ እያንዳንዱ ጳጳስ ለ 87,000 የካቶሊክ ምዕመናን ኃላፊ ወይም ተጠያቂ ነው፣ ይህም ከዚህ አንጻር ሲታይ ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነፃፀር ትንሽ የበዛ የጳጳሳትን ቁጥር እንዳለ ያመለክታል።
ጥቂት ካህናት
እ.ኤ.አ. በ 2023 ዓ.ም መገባደጃ ላይ የካቶሊክ ምዕመናን በዓለም ውስጥ ከሚገኙ በ 3,041 የቤተ ክህነት ተቋማት ውስጥ 406,996 ካህናት ነበሩ፣ እ.አ.አ ከ 2022 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር በ734 በቁጥር ቀንሷል ፣ ማለትም -በመቶኛ አኃዝ ሲሰላ 0.2% ቀንሷል። በጂኦግራፊያዊ አካባቢ ወይም በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ መሰረት የተደረገው ትንታኔ በአፍሪካ (+2.7%) እና በእስያ (+1.6%) ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በአውሮፓ (-1.6%)፣ በኦሽንያ (-1.0%) እና በአሜሪካ (-0.7%) ቅነሳ መኖሩን ያሳያል።
ከአህጉራቱ በተጨማሪ በሀገረ ስብከቶች እና በማሕበራት፣ ገድማዊያን ካህናት መካከል ያለውን ልዩነት ስናነፃፅር በእስያ እና በአፍሪካ የካህናት አጠቃላይ ጭማሪ በሀገረ ስብከት እና በማሕበራት፣ ገድማዊያን ካህናት መካከል ያለው ልዩነት የተለዋዋጭነቱ ምክንያት ነው ።
በአፍሪካ በተለይም የካህናት አጠቃላይ ጭማሪ በሀገረ ስብከት ካህናት በግምት 3.3% እና በማሕበራት፣ ገድማዊያን ካህናት ደግሞ 1.4% ጭማሪ ምክንያት ነው። በአሜሪካ አህጉራት ላይ የሀገረ ስብከት ቀሳውስት በባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ የቁጥር ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በመካከለኛው እና በላቲን አሜሪካ ጭማሪው ጎልቶ ይታያል። በአውሮፓ ውስጥ ግን የ 1.6% ቅነሳ በአጠቃላይ በእያንዳንዱ አካላት ማለትም በሀገረ ስብከት እና በማሕበራት፣ ገድማዊያን ካህናት) ውስጥ ይታያል፣ ተመሳሳይ ንድፍ ምንም እንኳን ትንሽ ማሽቆልቆል (-1.0%), ቢታይም በኦሽንያ አህጉር ውስጥ ተመዝግቧል።
እ.ኤ.አ. በ 2023 ዓ.ም በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ስርጭቱ 38.1% የሚሆኑት በአውሮፓ ፣ 29.1% የአሜሪካ አህጉራት ሲሆኑ ፣ ሌሎች አህጉራዊ አካባቢዎች ደግሞ 18.2% በኤዥያ ፣ 13.5% በአፍሪካ እና 1.1% በኦሽንያ እንደሚገኙ ያሳያል ።
በሐዋርያዊ አገልግሎት ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለውን አለመመጣጠን ለማጉላት የካህናት መዋቅራዊ ትንተና የምያሳየው የካህናት ቁጥር ከካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ ሊጨመር ይችላል የሚል ትንበያን ያሳያል። በሐዋርያዊ አገልግሎት እንቅስቃሴ አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ፍጹም ሚዛን ሲኖር፣ የካህናቱ መቶኛ ስብጥር፣ ለእያንዳንዱ የግዛት ክልል ከካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር ጋር መመሳሰል አለበት። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ በካህናቱ እና በካቶሊክ ምዕመናን የቁጥር አኃዝ በመቶኛ ስብጥር መካከል ያለው ንጽጽር እንደሚያሳየው እ.አ.አ በ2023 ጉልህ ልዩነቶች ተመዝግበው ነበር።
በተለይም የካህናቱ ብዛት በአለም አቀፍ ደረጃ በመቶኛ ስብጥር ስንመለከት በሰሜን አሜሪካ 10.3% ካህናቶች የሚገኙ ሲሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር አሁንም ከአለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ በመቶኛ ሲሰላ 6.6% የካቶሊክ ምዕመናን በሰሜን አሜሪካ ይገኛል፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ጠቅላላ የካህናት ብዛት 38.1% ካህናት በአውሮፓ አህጉር ይገኛሉ፣ አሁንም ከአለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ በመቶኛ ሲሰላ 20.4% የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በአውሮፓ አህጉር ውስጥ ይገኛሉ፥ በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው አኃዝ አንጻር ሲታይ በኦሽንያ አህጉር የሚኖሩ የካህናት ብዛት 1.1% ሲሆን አሁንም በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የቁጥር አኃዝ አንጻር ሲታይ 0.8% የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በኦሻኒያ አህጉር ይኖራሉ። በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የካህናት የቁጥር አኃዝ አንጻር ሲገመገም በጣም ግልጽ የሆነው የካህናት እጥረት የሚታየው በደቡብ አሜሪካ ሲሆን ይህም 12.4% ነው፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር አንጻር ሲታይ ደግሞ በደብብ አሜሪክ አህጉር የሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ብዛት 27.4% ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኘው የቁጥር አኃዝ አንጻር በአፍሪካ አህጉር 13.5% ካህናት የሚገኙ ሲሆን አሁንም በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የቁጥር አኃዝ አኳያ 20.0% የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በአፍሪካ ይገኛሉ። በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የቁጥር አኃዝ አንጻር ሲታይ በመካከለኛው አሜሪካ ክልል 5.4% ካህናት የሚገኙ ሲሆን አሁንም በአለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ 11.6% የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በመካከለኛው አሜሪካ ክልል ይገኛሉ።
ብዙ የቋሚ ዲያቆናት ስብስብ
ቋሚ ዲያቆናት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ያለውን የካህናት ቡድን ያግዛሉ። እ.ኤ.አ. በ 2023 ቁጥራቸው በ2022 ዓ.ም ከተመዘገበው 50,150 ጋር ሲነፃፀር 51,433 ደርሷል ፣ በ 2.6% ጭማሪ አሳይቷል።
ይህ ጭማሪ ከአህጉር አህጉር ልዩነት ጎልቶ ይታይባቸዋል፡ በኦሽንያ (+10.8%) እና በአሜሪካ (+3.8%) ከፍተኛ የእድገት ደረጃዎች ተስተውለዋል፣ በአፍሪካ እና በአውሮፓ ደግሞ መጠነኛ ቅናሽ ተመዝግቧል። በአውሮፓ አንጻራዊ በሆነ መልኩ የዲያቆናት ብዛት ከመቀነሱ እና የአሜሪካው ከመጨመሩ በስተቀር በዋነኛነት በሰሜን አሜሪካ ከሚታየው ከፍተኛ እድገት ሳቢያ ካልሆነ በስተቀር በአለም አቀፍ የዲያቆናት ስርጭት ላይ ጉልህ ለውጦች አልተስተዋሉም። ይህ የሐዋርያዊ አገልግሎት ምድብ በተለይ በአሜሪካ (በተለይ በሰሜን አሜሪካ ከዓለም ዙሪያ 39 በመቶውን የዲያቆናት ድርሻ ይይዛል) እና እንዲሁም በአውሮፓ (31%) ቋሚ ዲያቆናት ይገኛሉ።
እነዚህ የሐዋርያዊ አገልግሎት ሰጪዎች ከካህናት ጋር በመሆን በእረኝነት ተግባር ውስጥ የሚኖራቸውን የድጋፍ ሚና ለማጉላት፣ የቋሚ ዲያቆናት ብዛት በየአካባቢው ካሉት ካህናት ብዛት ጋር ያለውን ጥምርታ ግምት ውስጥ ማስገባት ይቻላል። በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው የዲያቆናት ስርጭት እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም ለአንድ መቶ ቄስ13 ቋሚ ዲያቆናት ምጥንጥን የምያሳይ ሲሆን ይህም በእስያ በትንሹ ከ0.5 እስከ 29 በአሜሪካ አህጉር ይደርሳል። በአውሮፓ አህጉር አኃዙ ወደ 10 አካባቢ ሲሆን በአፍሪካ ግን አንድ ቋሚ ዲያቆን ብቻ ከመቶ ቄሶች ጋር ያገለግላል።
የዚህ ቁጥር አኃዝ መጠን ምንም እንኳን አድናቆት ቢኖረውም ቋሚ ዲያቆናት በአህጉራት ውስጥ ላሉ ካቶሊኮች ያላቸው የአገልግሎት ፍላጎት እና አቅርቦትን በማመጣጠን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዲኖራቸው አሁንም በጣም ትክክለኛ ሥራ ሊሰራ ይገባል። ነገር ግን፣ በዝግመተ ለውጥ አገላለጽ፣ ቋሚ ዲያቆናት ለክህነት እጩዎች ቁጥራቸው ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ይታወቃል።
የደናግላን እና የወንድሞች (ካህናት ያልሆኑ) ቁጥር ቀርፋፋ የመቀነስ መጠን
በጊዜ ሂደት የተከሰተው የሁለቱም ማለትም የደናግላን እና ካህናት ያልሆኑ ወንድሞች አኃዝ እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም በትንሹም ቢሆን ዘገምተኛ የሆነ የቁጥር ቅነሳ አሳይቷል።
በተለይም እ.አ.አ በ2022 እና 2023 ዓ.ም መካከል በአፍሪካ ጭማሪ የተመዘገበ ቢሆንም፣ ሁሉም ሌሎች አህጉራት ካህን ያልሆኑ ወንድሞችን በተመለከተ ግን መጨመሩን ልብ ሊባል ይገባል። በደቡብ አሜሪካ ያለው ቅነሳ ካለፈው ጊዜ አማካይ ዓመታዊ ቅናሽ ጋር ሲነፃፀር መቀነሱ እና በመካከለኛው አሜሪካ እንኳን የመረጋጋት ሁኔታ እንደሚታይ አጽንኦት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች ካህናት ያልሆኑ ወንድሞች ያላቸው አንጻራዊ ቁጥር በጊዜ ሂደት ሲታሰብ እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም እየቀነሰ የመጣውን የአውሮፓን አኃዝ ያረጋግጣል።
እ.ኤ.አ. በ2023 ዓ.ም የደናግላን እህቶች ቁጥር ማሽቆልቆሉ ቀጥሏል። በአለም አቀፍ ደረጃ፣ ቁጥራቸው እ.አ.አ በ2022 ዓ.ም ከ599,228 ወደ 589,423 በ2023 ቀንሷል፣ በአንፃራዊ ልዩነት -1.6% በ2023 ዓ.ም ቅነሳ መልክዓ ምድራዊ ወይም ጂኦግራፊያዊ ስርጭታቸውን በተመለከተ ከአለም አቀፉ የቁጥር አኃዝ አኳያ በመቶኛ ሲሰላ፣ ወደ 32% የሚጠጋው በአውሮፓ፣ በመቀጠል እስያ በ30%፣ አሜሪካ በ23 በመቶ (በሁለቱ ንፍቀ ክበብ እኩል የተከፋፈለ)፣ አፍሪካ 14%፣ እና ኦሺኒያ በ1% አህጉራት ውስጥ ይኖራሉ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ መሐላ ያደረጉ የደናግላን እህቶች ቁጥር ማሽቆልቆሉ በዋነኝነት የሚጠቀሰው የሞቱት ሰዎች መብዛት ነው፣ ይህም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አረጋውያን የመሐላ ያደረጉ ደናግላን እህቶች ሲሆኑ፣ የገዳም ሕይወታቸውን የሚተውት ግን ከሁለት ዓመት በኋላ ግን ጉልህ በሆነ መልኩ መታየት ጀምሯል።
እ.ኤ.አ. በ2022 እና 2023 ዓ.ም መካከል አፍሪካ በ2.2 በመቶ ከፍተኛ እድገት አስመዝግባለች ፣ ደቡብ ምስራቅ እስያ በ +0.1% ይከተላል። በሌላ በኩል ሰሜን አሜሪካ የ -3.6% ቅናሽ አሳይቷል። ደቡብ አሜሪካ ከ -3% ቅነሳ በማሳየት በቅርበት ተከትላለች፣ በመካከለኛው የአሜሪካ አህጉር እና በማዕከላዊ የካሬቢያን ግዛቶች ውስጥ የተመዘገበው ቅነሳ ግን የበለጠ መካከለኛ ነበር። አውሮፓ ከምንጊዜም የበለጠ አሉታዊ አኃዝ አሳይቷል፣ ይህም በመቶኛ ሲሰላ ልዩነቱ -3.8% ነው።
እነዚህ እንቅስቃሴዎች መሐላ ያደረጉ ደናግላን እህቶች አጠቃላይ ቁጥር በአህጉራዊ ምጣኔ ለውጥ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እ.አ.አ በ2022-2023 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መሐላ ያደረጉ እህቶች በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ እህቶች ቁጥር ቀንሷል። በተለይም እ.ኤ.አ. በ2022 ዓ.ም በአውሮፓ እና በአሜሪካ ያሉ መሐላ ያደረጉ ደናግላን እህቶች አጠቃላይ ቁጥር 55.8% ከአለም አጠቃላይ ድርሻ ሲይዝ ፣ እ.አ.አ. በ2023 ዓ.ም ይህ በመቶኛ ወደ 54.8% ዝቅ ብሏል ። በወቅቱ ከፍተኛ ጉልህ ለውጦች በደቡብ ምስራቅ እስያ (ከ 28.7% ወደ 29.2%) እና በአፍሪካ (ከ 13.9% ወደ 14.5%) ማደጉ ተስተውሏል።
ምንም እንኳን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው ቅናሽ እና በአንዳንድ አህጉራዊ ክልሎች መሐላ ያደረጉ ደናግላን እህቶች አሁንም ተጨባጭ እውነታ አላቸው። የደናግላን እህቶች ቁጥር ከካህናት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በ45% ይበልጣል። በአገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ ያላቸው ስታቲስቲካዊ ወይም አኃዛዊ ሚና ባለፉት ዓመታት ባጠቃላይ እየቀነሰ ቢመጣም ለክርስቲያን ማኅበረሰብ ሕይወት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አሁንም አስፈላጊ ነው።
የሴሚናሪስቶች ቁጥር መቀነስ ቀጥሏል
በአለም አቀፍ ደረጃ በዋና ዋና የዘርዐ ክህነት ትምህርት መስጫዎች ውስጥ የሚታየው ጊዜያዊ አዝማሚያ እ.አ.አ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የተመዘገበውን ያልተቋረጠ ቅነሳ ያመለክታል።
ከጠቅላላ አኃዝ አንፃር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለክህነት ማዕረግ እጩዎች እ.ኤ.አ. በ2022 ከ108,481 ወደ 106,495 እ.አ.አ በ2023 ቀንሰዋል፣ በ -1.8% የቅነሳ ልዩነት ያሳያል። በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው መቀነስ ከአፍሪካ በስተቀር በሁሉም አህጉራት ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል፣ ሴሚናሪስቶች ወይም የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች በ1.1% (ከ 34,541 ወደ 34,924) በቁጥር ጨምረዋል። በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአሜሪካ፥ ነገር ግን በተለይም በአንድ አንድ አህጉራት ቅነሳው በጣም ከፍተኛ ነው (-4.9% በአውሮፓ፣ -4.2% በእስያ እና -1.3% በአሜሪካ)። በኦሻኒያ አህጉር ውስጥ፣ አዝማሚያው አሉታዊ ቢሆንም መጠኑ አነስተኛ ነው።
የዋና ዋና ሴሚኔሪዎች ወይም የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች በአህጉር ደረጃ በመቶኛ ስርጭት በሁለት አመት ውስጥ መጠነኛ ለውጦችን ያሳያል። እ.ኤ.አ. በ2022 ዓ.ም አፍሪካ እና እስያ 61.0% ለአለምን አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሲሆን ይህም በ2023 ወደ 61.4% ከፍ ብሏል። በኦሺኒያ ካለው ትንሽ አሉታዊ ማስተካከያ በተጨማሪ አሜሪካ እና አውሮፓ በጋራ ድርሻቸው ቀንሷል። እ.ኤ.አ. በ 2022 የአሜሪካ እና የአውሮፓ አህጉር የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ወይም ሴሚናሪስቶች በድምሩ 41,199 ሲሆን በጠቅላላው 38% የሚሆነውን በአለም አቀፍ ደረጃ ይወክላሉ ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ግን ወደ 37.7% ዝቅ ብለዋል ።
በክልል ደረጃ ያለውን የመንፈሳዊ ጥሪ ህዳግ አወንታዊ እና አሉታዊ ገጽታውን ለማጉላት የሴሚናሪስቶች መቶኛ የእድገት ስርጭት ከተዛማጁ የካቶሊኮች ምዕመናን የቁጥር እድገት ስርጭት ጋር ማነፃፀር ጠቃሚ ነው። እ.አ.አ በ2023 ጉልህ ልዩነቶች ተመዝግበዋል።
በአለም ደረጃ የሴሚናሪስቶች ቁጥር በመቶኛ አኃዝ በቁጥር ሲሰላ በአፍሪካ ካሉት ካቶሊኮች ይበልጣል፣ አፍሪካ በአለም አቀፍ ደረጃ 32.8% ሴሚናሪስቶችን ስታበረክት፣ አሁንም አፍሪካ 20% የካቶሊክ ምዕመናን በአለም አቀፍ ደረጃ ታበረክታለች። በአለም አቀፍ ደረጃ እስያ 28.6% ሴሚናሪስቶችን የምያበረክት አህጉር ሲሆን የእሲያ አህጉር በአለም አቀፍ ደረጃ 11% የካቶሊክ ምዕመናን በአህጉሪቷ ውስጥ ይኖራሉ። ስለዚህ እነዚህ አህጉራት የአካባቢያቸውን ሐዋርያነት በራስ ገዝ የመደገፍን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ያሟሉ ናቸው።
በአውሮፓ እና አሜሪካ አህጉራት ውስጥ ግን የሴሚናሪስቶች ወይም የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ቁጥር ከአለማቀፉ አኃዝ አኳያ በመቶኛ ሲታይ አሁንም በአለም አቀፍ ደረጃ ከምያበረክቱት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን አኳያ ሲታይ በቁጥር ያነሰ ነው፣ ከአለማቀፉ አኃዝ አኳያ አውሮፓ ለአለም የምታበረክተው የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች በመቶኛ 12.0% ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ 20.4% የካቶሊክ ምዕመናን የአውሮፓ አህጉር ለአለም ያበረክታል፣ የአሜሪካ አህጉር ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ 25.7% የዘረዐ ክህነት ተማሪዎችን ለአለም የምያበረክት ሲሆን የአሜሪካ አህጉር በአለም አቀፍ ደረጃ 47.8% የካቶሊክ ቤተክርስቲያም ምዕመናንን ያበረክታል። በነዚህ ሁለት አህጉራት ለካቶሊክ ህዝብ ፍላጎት በተለይም በክህነት ውስጥ ካለው የትውልድ ለውጥ አንፃር በበቂ ሁኔታ ምላሽ መስጠት በጣም ከባድ ነው።