ቅድስት መንበር፡- ጦርነቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች አፍሪካን የበለጠ ደካማ ያደርጓታል አለች!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የሳህል የዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ፋውንዴሽን ወይም ድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ በዚህ ሳምንት ለ43ኛ ጊዜ በዳካር ሴኔጋል እየተሰበሰበ ነው።
በሳህል ውስጥ በድርቅ የተጎዱ ህዝቦችን መደገፍ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.አ.አ በ1980 ዓ.ም ወደ አፍሪካ ያደረጉትን የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉዞ ተከትሎ እ.አ.አ በ1984 ዓ.ም የቅድስት መንበር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከአካባቢው ቤተ ክርስቲያን እና ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር የቅድስት መንበር ድጋፍ ለማድረግ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ከአለም ድሃ ከሆኑ አገራት መካከል አንዱ በሆነው በሳህል ቀጠና አገራት ቡርኪናፋሶ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ማሊ፣ ሞሪታኒያ፣ ኒጀር፣ ሴኔጋል፣ ቻድ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋም ድርጅት ነው።
ፋውንዴሽኑ የአስተዳደር አደራውን ለአካባቢው ጳጳሳት የተሰጠ እና በአሁኑ ጊዜ የቫቲካን የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማትን ለማበረታታት የተቋቋመው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት አካል የሆነው፣ በረሃማነትን በመዋጋት፣ የድርቅ ተጎጂዎችን በመርዳት እና በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና፣ በውሃ አያያዝ እና በታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ዘላቂ ልማትን በማስተዋወቅ ላይ ያተኩራል።
የሥራው ጉልህ ገጽታ ለማህበረሰባቸው ውጤታማ አስተዋጽዖ ሊያበረክቱ የሚችሉ ልዩ የቴክኒክ ባለሙያዎችን ማሰልጠን ያካትታል። በተጨማሪም በሃይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት ይደረግ ዘንድ ያበረታታል፣ የተለያየ እምነት ያላቸውን ሰዎችን በተቻለ መጠን በልማት ይደግፋል።
በጦር መሣሪያ የሚደረጉ ግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች አፍሪካን ደካማ ያደርጋታል።
ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 14/2017 ዓ.ም በዳካር የምካሄደው ስብሰባ ትኩረት፣ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን በሣህል ውስጥ እየጨመረ የሚሄደውን ተግዳሮቶች፣ የትጥቅ ግጭቶች፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የተፈጥሮ አደጋዎችን በሚጨምርበት ጊዜ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን እንዴት የበለጠ መደገፍ እና ከእዚህ ቀደም የሚያደርገውን ድጋፍ ማሳደግ እንደሚችል እየተወያየ ይገኛል።
ማክሰኞ የካቲት 11/2017 ዓ.ም ለተሳታፊዎች ንግግር ያደረጉ የቫቲካን ተወካይ የሆኑት የእኔታ ሮቤርቶ ካምፒሲ እንዳሉት፣ ፋውንዴሽኑ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ ተልእኮውን በብቃት ለመወጣት ከተፈለገ፣ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተቀመጡት መመሪያዎች ላይ በመመሥረት ውጥኖቹን በማዋቀር በሰው ልጆች ሁለንተናዊ ልማት ላይ ማተኮር ይኖርበታል ብለዋል።
የዳካር ሊቀ ጳጳስ ቤንጃሚን ንዲዬ ጉባኤውን ስላስተናገዱ ምስጋናቸውን ያቀረቡት የቫቲካን ምክትል ኃላፊ በአደራ በተሰጣቸው ጳጳሳት መካከል “የወንድማማችነት ትኩረት ምልክት” እና “ለማኅበረ ቅዱሳን ጠንካራ ምስክርነት” በማለት ገልጸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለተልዕኮው ቀጣይነት ያላቸውን ድጋፍ አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከምንም በላይ ውስጣዊ ለውጥ በማድረግ የተጀመረውን የሮማን ኩሪያ ማሻሻያ ጥሪ ተከትሎ ስብሰባው የቫቲካን መሰረታዊ ደንቦች በሚገዙት አዲስ ደንቦች ላይ በጋራ ለማሰላሰል እንደ እድል ሆኖ እንደሚያገለግል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ግጭቶችን ለመከላከል ድህነትን መዋጋት እና ልማትን ማስፋፋት
በተጨማሪም ማክሰኞ የካቲት 11/2017 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ ላይ የተናገሩት እህት አሌሳንድራ ስሜሪሊ የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማትን የሚያበረታታ የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ፀሃፊ ሲሆኑ በሳሄል ውስጥ ግጭቶችን እየፈጠሩ ያሉትን ኢፍትሃዊነት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን በማስተጋባት ድህነትን ለመዋጋት፣ የሰው ልጅን ሁለንተናዊ ልማት ለማስፋፋት እና ሰላማዊ አብሮ መኖርን ለመፍጠር የጋራ ጥረቶች እንዲደረጉ አሳስበዋል። የእርሳቸው አስተያየት የፋውንዴሽኑ ሥራ አፋጣኝ ዕርዳታ በመስጠት ላይ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ክብርን እና ማህበራዊ መግባባትን የሚደግፉ ዘላቂ መፍትሄዎችን መፈለግ እንዳለበት ሐሳባቸውን አጠናክረው አቅርበዋል።
እህት ስሜሪሊ በበኩላቸው የተሻለች አፍሪካን ለመገንባት ለሚደረገው ቀጣይ ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን ገልፀዋል—ወንድማማችነት ጥሩ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ እውነታ ነው ብለዋል።
በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ በጳጳሳዊ ተቋማት ደንቦች ላይ ባደረጉት ማሻሻያ ያስተዋወቁትን አዳዲስ አመለካከቶች በማንፀባረቅ፣ እህት ስሜሪሊ የተከናወኑት ውጥኖች “የፍትህ፣ የአብሮነት እና የርኅራኄን ሁለንተናዊ እሴቶች የሚያንፀባርቁ እና ለጋራ ጥቅም የሚመሩ፣ ለሰላምና ለማህበራዊ ወዳጅነት የሚሠሩ፣ በሣህል ውስጥ የሰው ልጅን ሁለንተናዊ ልማት የሚያበረታቱ ለውጦችን እንደሚያመጣ ተስፋቸውን ገልጸዋል።