MAP

ካርዲናል ፔይትሮ ፓሮሊን የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔይትሮ ፓሮሊን የቫቲካን ዋና ጸሐፊ 

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፡ 'አካታች የሆነ የሰላም መንገድ እና አካሄድ እንፈልጋለን' ማለታቸው ተገለጸ!

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከጣሊያን ጋዜጣ L'Eco di Bergamo ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ የባለብዙ ወገን 'የተስፋ ዲፕሎማሲ' እና ሰላምን ለመደራደር "ድፍረት" እንደሚያስፈልግ በድጋሚ ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ዓለም አቀፋዊ ዲፕሎማሲው በየቦታው የሚፈልገውን እና ውጤታማነቱን ያጣ በሚመስልበት በዚህ ወቅት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እንዳሉት ከሆነ የቅድስት መንበር የባለብዙ ጎን ጽኑ ድጋፍ በመግለጽ ለሰላም ሁሉን አቀፍ አቀራረብ አስፈላጊነት ጠቁመዋል። ለግጭቶች የሚሆኑ መፍትሄዎች በፍፁም በአንድ ወገን መጫን የለባቸውም ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

"ሁሉም ሰው ለሰላም የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል፣ ነገር ግን የመላው ሕዝቦችን መብት ሊረግጡ በሚችሉ የአንድ ወገን ጫናዎች መፍትሄዎችን መከተል የለበትም፣ ያለበለዚያ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ፈጽሞ አይኖርም" ብለዋል።

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ይህንን አስተያየት ከጣሊያን አገር በቀል ጋዜጣ L’Eco di Bergamo አዘጋጅ አልቤርቶ ቼሬዞሊ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ የተናገሩ ሲሆን በዚሁ በሰፊው በተደርገው ቃለ ምልልስ ካርዲናል ፓሮሊን በጋዛ እና በዩክሬን ጦርነቶች፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ተለዋዋጭ ሁኔታ እና የአውሮፓን ሚና በዘመናችን የጂኦፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ጨምሮ በርካታ አንገብጋቢ የጂኦፖለቲካ ጉዳዮችን አንስተዋል።

የአስተሳሰብ ዋንኛው ጉዳይ ለግጭቶች የሚሆኑ መፍትሄዎች በፍጹም በአንድ ወገን መጫን እንደሌለበት ነው፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት አካሄዶች ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን ስለሚያደርጉ ነው ብለዋል።

ለቅድስት ሀገር የተስፋ ጭላንጭል

የእስራኤል እና የፍልስጤም ግጭትን በሚመለከት፣ በተደረገው ጊዜያዊ እና አደገኛ የእርቅ ስምምነት ላይ ያለውን ጥንቃቄ የተሞላበት ተስፋ ገልጿል፡- “ፍሬዎቹ መታየት በመጀመራቸው እንደ የእስራኤል ታጋቾች መፈታት እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባቱ እና በጋዛ ውስጥ የፍልስጤም ህዝብን የሚያሰቃይ ተግባር እንዲቆም እና ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም መጀመሪያ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ስላለው ሁለቱም በእርግጥ መልካም ዜና ነው ብለዋል።

ሶሪያን ለመርዳት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያስፈልጋል

የቅርብ ጊዜውን የሶሪያን የአገዛዝ ለውጥ በተመለከተ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የሦሪያ አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸው፣ ሀገሪቱ የግዛት ይዞታዋን ለማስጠበቅ እና በተለያዩ ህዝቦቿ መካከል የተቀናጀ አብሮ መኖርን ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

እርስ በርስ አለመተማመን እና ፍርሃት ውይይትን ያደናቅፋሉ

እንደ ጋዛ እና ዩክሬን ያሉ ጦርነቶችን የመሳሰሉ ውስብስብ ሁኔታዎችን ለመፍታት ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ስላጋጠሙት ችግሮች የተጠየቁት ካርዲናል ፓሮሊን፣ ቀዳሚ እንቅፋት የሆነው የጋራ አለመተማመን እና ፍራቻ ዋልታ ረገጥነት እንዲጨምር እና ገንቢ ውይይት እንዳያደርጉ የሚያደናቅፍ ነው። በአለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣው 'የቡድን ወይም የክለብ አስተሳሰብ' ተዋናዮች ተቃራኒ አመለካከቶችን እየሸሹ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ጓደኞቻቸው ጋር ብቻ የሚገናኙበት - የዲፕሎማሲውን ውጤታማነት የበለጠ እንደሚያባብሰው በድጋሚ አረጋግጧል። ይህ በራስ ተነሳሽነት ከተለያዩ ውይይቶች መገለል ትርጉም ያለው የሽምግልና እና የመፍታት እድሎችን ይገድባል ብለዋል ።

የባለብዙ ወገንነት ፍላጎት እና አዲስ ‘የተስፋ ዲፕሎማሲ’

እነዚህን ተግዳሮቶች ለማሸነፍ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ‘የተስፋ ዲፕሎማሲ’ ብለው በሚጠሯቸው  ውይይት፣ ትዕግስት እና መተማመንን በመገንባት ላይ ያተኮረ የተለየ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ እንዳለም ካርዲናል ፓሮሊን ጠቁመዋል። እንዲህ ያለው አካሄድ መግባባትን እና የረጅም ጊዜ ዕርቅን ቅድሚያ የሚሰጠውን ማዕቀፍ በማቅረቡ አሁን ካለው የግጭት እና የማግለል ተለዋዋጭነት አማራጭ ነው ብለዋል፣ ስለሆነም ሰላምን በማስፈን ረገድ የበለጠ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ለዚህ ነው ብለዋል፣ ካርዲናል ፓሮሊን አክለውም “በብዙ ወገንተኝነት” ማመን እና የተባበሩት መንግስታትን በተጨባጭ የሚወክሉትን ዓለም አቀፍ ተቋማትን ሚና ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል ።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን እና የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቃላትን በማስተጋባት ሰላም ድፍረትን፣ ፍትህን እና ይቅርታን እንደሚጠይቅ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ በዘመናዊው ኅብረተሰብ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠፉ ያሉ የሚመስሉትን ሦስት እሴቶች ጠቁመዋል። "ዛሬ ለመደራደር ያለው ድፍረት ብዙውን ጊዜ ደካማነት ነው፣ ወታደራዊ ኃይል እና የጦር ማሳያዎች የግጭት መፍቻ መሳሪያዎች ሆነው ሲቀጥሉ፣ ካርዲናል ፓሮሊን እንዳሉት ከሆነ "በሌላ በኩል ሰላም በይቅርታ ላይ በፍትህ ላይ መገንባት አለበት፣ ምክንያቱም "እውነተኛ ሰላም ያለ ፍትሃዊ ስርዓት ሊኖር አይችልም" ብለዋል።

“ድፍረት፣ ፍትህ እና ይቅር ባይነት እንደ መሰረታዊ እሴቶች ሲኖሩ ብቻ ነው ወደ እውነተኛ የሰላም መንገድ መሄድ የሚቻለው” ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ካርዲናል ፓሮሊን ተናግረዋል።

አውሮፓ ራዕይ ያስፈልጋታል

ወደ አውሮፓ በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለውን ሚና ስንመለከት፣ ካርዲናል ፓሮሊን እናድሉት ከሆነ የአህጉሪቱን ወቅታዊ ፈተናዎች በአውሮፓ ህገ-መንግስት ውስጥ ክርስቲያናዊ ውርሷን አለመቀበልን ተከትሎ የመጣ ነው። የዚህ ዕውቅና እጦት እንደ ካርዲናል ፓሮሊን ገለጻ ለአውሮፓውያን ማንነትና አንድነት መዳከም አስተዋጽኦ አድርጓል። አውሮፓ በወቅታዊው የዓለም አውድ ድምጽና ሚና እንዲኖራት፣በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ እና በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጥሪ መሠረት ስለዚህ በአንድ ወቅት ጥንካሬዋን ወደ ሰጣቸው ታሪካዊና ባህላዊ መነሻዎች መመለስ አለባት ያሉ ሲሆን “በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተስተጋቡት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጥሪ፣ 'አውሮፓ፣ እንደገና ራሷን መልሳ ማግኘት አለባት፣ አውሮፓ ራሷን ትሁን!' ዛሬ ጠቃሚ ነው እና በዓለም መድረክ ውስጥ ማዕከላዊ ሚና መጫወቷን ለመቀጠል ከተፈለገ መከተል ያለበት መንገድ ይህ ነው" ማለታቸው ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን አስታውሰዋል።

 

17 Feb 2025, 15:47