MAP

የኮንራድ ኤን ሒልተን የልጅ ልጅ ወይዘሮ ሒልተን የኮንራድ ኤን ሒልተን የልጅ ልጅ ወይዘሮ ሒልተን   (Vatican Media)

ኢዮቤልዩ፡- ሒልተን ፋውንዴሽን 'የካቶሊክ እህቶችን ድምፅ ከፍ ለማድረግ' ይፈልጋል!

በደርዘን የሚቆጠሩ ገዳማዊያን እህቶች የኢዮቤልዩ ለኮሚዩኒኬሽን አንድ አካል ሆነው በሮም ሲገናኙ የኮንራድ ሒልተን ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ሊንዳ ሂልተን የበጎ አድራጎት ድርጅቷ ለካቶሊክ እህቶች የሰላም መንስኤዎችን ለማገልገል በሚያደርጉት ተልዕኮ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ገልጸዋል፣ ፍትህ እና ትምህርት አስፈላጊ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"በአለም ላይ በእውነት እየሆነ ያለውን ነገር ሁሉም ሰው እንዲረዳ ታሪኮቻቸው መነሳት አለባቸው፣ እና እነዚህ እህቶች ከልባቸው ለሌሎች ርህራሄን ያሳያሉ" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን  የሂልተን ፋውንዴሽን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሊንዳ ሂልተን ያንን በእምነት የተሞላ ውሳኔ በዓለም ዙሪያ ስላሉት የካቶሊክ እህቶች ስራ ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።

የቫቲካን የኮሙዩኒኬሽን ጽኃፈት ቤት (የእኛ ወላጅ አካል) ባዘጋጀው “ሕብረትን በኮሙዩኒኬሽን መሸመን" በሚል ርዕስ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከቫቲካን ዜና ጋር ቆይታ አድርገዋል።  

ዝግጅቱ ወደ 80 የሚጠጉ የካቶሊክ እህቶች እንዴት የሌሎችን ድምጽ ከፍ ለማድረግ ስራቸውን ማሳወቅ እንደሚችሉ ሐሳባቸውን ሰብስቧል። እ.አ.አ በ1944 ዓ.ም በሆቴል ሥራ ፈጣሪ የተቋቋመው በኮንራድ ኤን ሂልተን ፋውንዴሽን ስፖንሰር ተደርጓል።

ወይዘሮ ሒልተን በቴክሳስ በአሜሪካ-ሜክሲኮ ድንበር ላይ ከስደተኞች ጋር ስለሚሰሩት ስለ እህት ኖርማ ፒሜንቴል፣ ስራ ሲሰሙ እሳቸው እና ሌሎች የፋውንዴሽኑ ቦርድ አባላት በእንባ ታጠቡ።

ወይዘሮ ሒልተን “በመተግበሪያዎቻቸው (ለገንዘብ ድጋፍ) እዚያ ምን እየተፈጠረ እንዳለ ማወቁ ለእኔ ዓይን ከፋች ድርጊ ነበረ" ሲሉ ተናግረዋል።

ሐሙስ ዕለት ጥር 15/2017 ዓ.ም በጉባኤው ላይ እንደተናገሩት እንደ እህት ፒሜንቴል፣ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ክርስቶስን የሚያገለግሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ገዳማዊያን እህቶች አሉ፣ ብዙ ጊዜ በዝምታ ይሰራሉ፣ ግን ሁል ጊዜ በፍቅር ተግባራቸውን ያከናውናሉ ብለዋል።

የሆቴሉ ሥራ ፈጣሪ ብዙ የግዛቱን ክፍል ለኮንራድ ኤን ሒልተን ፋውንዴሽን በማውረስ የካቶሊክ እህቶች ሁል ጊዜ በፋውንዴሽኑ ገቢ ውስጥ ትልቁን ኢንቨስትመንት መወከል እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

“በእኛ ራእይ ውስጥ፣ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፣ ምክንያቱም ይህ የሕግ ሁሉ የበላይ ነው” በማለት የኮንራድ ኤን ሒልተን የልጅ ልጅ ወይዘሮ ሒልተን ትናገራለች። "የአለም ህዝቦች ሊወደዱ እና ሊበረታቱ ይገባቸዋል፣ በጭራሽ መረሳት የለባቸውም፣ ብቻቸውን በድህነት ውስጥ ይቅበዘዛሉ፣ ይህ ተገቢ አይደለም" ብለዋል።

የሂልተን ፋውንዴሽን ቦርድ ለአለም እያደጉ ያሉ ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

በፋውንዴሽኑ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ አንድ ፕሮጀክት ለእህቶች በኮሙዩኒኬሽን ውስጥ ቀጣይነት ያለው ምስረታ ይሰጣል እና ከቫቲካን የኮሙዩኒኬሽን ጽኃፈት ቤት ጋር በመተባበር ይከናወናል። በየዓመቱ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ እህቶች በዘመናዊ ሚዲያ የመስመር ላይ ሥልጠና ያገኛሉ፣ እናም ጥቂቶቹ ጥልቀት ያለው ትምህርት ለመቀበል በሮም በሚገኘው የቫቲካን የኮሙዩኒኬሽን ቢሮዎች ሶስት ወራትን ያሳልፋሉ።

ወጣት ገዳማዊያት ሴቶችን ከማሰልጠን በተጨማሪ የሂልተን ፋውንዴሽን እ.አ.አ በጥር 22/2025 ላይ "የአና እምነት ለአረጋውያን የካቶሊክ እህቶች" የተሰኘ ፕሮግራም ጀምሯል።

ከዓለም አቀፉ የበላይ ተቆጣጣሪዎች ህብረት ጋር በመተባበር የተፈጠረው ይህ ተነሳሽነት "ጤናማ፣ የተከበረ የእርጅና ሂደት" በዓለም ዙሪያ ላሉ እህቶች ድጋፍ ያደርጋል።

ወይዘሮ ሒልተን እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ረቡዕ ጥር 14/2017 ዓ.ም በቫቲካን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ተገናኝተው ነበር፣ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ እና ለአረጋውያን አሳቢነት ያላቸው ቁርጠኝነት ለመፍጠር ፋውንዴሽኑን አነሳስቶታል።

እ.ኤ.አ. በ2009 የወጣውን ዘገባ በመጥቀስ ቦርዱ መላ ሕይወታቸውን ለሌሎችን ለማገልገል የካቶሊክ እህቶችን መደገፍ አስፈላጊ እንደሆነ ተሰምቶታል፣ በወቅቱ በአሜሪካ የነበሩት የእህቶች አማካይ ዕድሜ 69 ዓመት እንደነበር ያሳያል።

 

24 Jan 2025, 16:49