ካርዲናል ፓሮሊን፡ በእዚህ ኢዩቤሊዩ አመት ኩባ እስረኞችን ለመልቀቅ ፈቃድ ማሳየቷ ትልቅ ተስፋን ያሳያል አሉ
ለቫቲካን መገናኛ ብዙኃን ምላሽ የሰጡት የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ጉዳዩን በተመለከተ ከሃቫና በደረሰው ዜና ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ለቫቲካን መገናኛ ብዙኃን አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ “553 የኩባ እስረኞችን ቀስ በቀስ መፈታት ይፋ መደረጉ በዚህ ኢዮቤልዩ መጀመሪያ ላይ ትልቅ ተስፋ የሚያሳይ ነው” ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ በፈረንሳይ የሚገኙት ካርዲናል አክለውም “የሃቫና ባለሥልጣናት ይህንን ውሳኔ በቀጥታ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጥሪ ጋር ማገናኘታቸው ጠቃሚ ነው፣ እሱም በኢዮቤልዩ አመት ሰነድ ውስጥና ከዚያም በሌሎች በርካታ አጋጣሚዎች እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። በቅዱስ ዓመት ውስጥ ብዙ ጊዜ እንደታየው የምህረት ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ መግለጻቸው ይታወሳል።
ካርዲናል ፓሮሊን እ.ኤ.አ. 2024 ዓ.ም “በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በደርዘን የሚቆጠሩ የሞት ፍርዶች ወደ ዕድሜ ልክ እስራት በመቀየር እና ዚምባብዌ የሞት ቅጣትን እንደሰረዘች በሚገልጽ ዜና ይፋ መሆኑ የሚደነቅ መሆኑን አስታውቀዋል።
"እ.ኤ.አ. 2025 ዓ.ም በዚህ አቅጣጫ እንደሚቀጥል እና የምስራች እንደሚበዛ ተስፋ እናደርጋለን በተለይም ለብዙ ግጭቶች እርቅ እና ሰላም እንደሚፈጠር ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል ።
16 Jan 2025, 15:45