MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 'ተጠማሁ' የሚለው ቃል ኢየሱስ ለፍቅር እና ለወዳጅነት ያቀረበው ጩኸት ነው ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ “ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋችን ነው!” በሚለው የኢዮቤልዩ ዓመት መሪ ሃሳብ ላይ በመመርኮዝ ሳምንታዊውን የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እያደረጉ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ረቡዕ ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም ያደረጉት የክፍል አምስት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ "“ተ͠ማሁĝ (ዮሐ. 19፡28) በሚለው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተበትን ሁኔታ በሚገልጸው የምጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደርጉት አስተምህሮ 'ተጠማሁ' የሚለው ቃል ኢየሱስ ለፍቅር እና ለወዳጅነት ያቀረበው ጩኸት እና ጥሪ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ

የኢየሱስ መሞት

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከወዲሁ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተ͠ማሁĝ አለ። በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት። ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ “ተፈጸመĝ አለ፤ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ (ዩሐ 19፡28-30)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

በሕማማ ታሪክ ማዕከል ውስጥ፣ በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ እጅግ በጣም ብሩህ በሆነው እና በተመሳሳይ ጊዜ እጅግ በጣም ጨለማ በሆነው ወቅት፣ የዮሐንስ ወንጌል ሁለት ቃላትን ያቀርብልናል “ተ͠ማሁĝ (19፡28)፣ እና ወዲያው ከእዚያን በኋላ፡ “ተፈጸመĝ (19፡30) የሚሉትን ሁለት ቃላት ያቀርብልናል። እነዚህ የመጨረሻዎቹ ቃላቶች ናቸው፣ ነገር ግን በጠቅላላው የሕይወት ዘመን ውስጥ የተሞሉ ናቸው፣ ይህም የእግዚአብሔርን ልጅ አጠቃላይ ሕልውና ትርጉም ያሳያል። በመስቀል ላይ ኢየሱስ እንደ ድል አድራጊ ጀግና ሆኖ አልቀረበም፣ ነገር ግን እንደ የፍቅር ተማጽኖ የምያቀርብ ሰው ሆኖ ይታያል። ራሱን አያውጅም፣ አይወቅስም፣ አይከላከልም። እሱ ብቻውን በምንም መልኩ ለራሱ መስጠት የማይችለውን ነገር በትህትና ይጠይቃል።

የተሰቀለው ጌታ &ܴdz;ተጠማው&ܴdz; የሚለው ጩኸት አካላዊ ጥማት ወይም ፍላጎት ብቻ የምያሳይ አይደለም። በተጨማሪምና ከሁሉም በላይ፣ የፍቅር፣ የግንኙነት፣ የኅብረት፣ የጥልቅ ምኞት መግለጫ ነው። የሰውን ሁኔታ ሁሉ ለመካፈል ፈልጎ ራሱን በዚህ ጥም እንዲሸነፍ ያደረገው የዝምታ ጩኸት ነው። ጠብታ ውሃ ለመለመን የማያፍር አምላክ፣ ምክንያቱም በዚያ ምልክት ፍቅር፣ እውነት ለመሆን፣ መጠየቅን ብቻ ሳይሆን መስጠትንም መማር እንዳለበት ይነግረናል።

&ܴdz;ተጠማሁ&ܴdz; ይላል ኢየሱስ፣ እናም በዚህ መንገድ የእሱን እና የእኛንም ጥም ጭምር ያሳያል። ማናችንም ብንሆን ራሳችንን መቻል አንችልም። ማንም ራሱን ማዳን አይችልም። ሕይወት “የljሞላውĝ ስንበረታ ሳይሆን እንዴት መቀበል እንዳለብን ስንማር ነው። ልክ በዚያ ቅጽበት ነው፣ ከማያውቁት እጅ በሆምጣጤ የተቀዳ ስፖንጅ ከተቀበለ በኋላ፣ ኢየሱስ&ܴdz;ተፈ͸መ&ܴdz;  ሲል ተናግሯል። ፍቅር እራሱን ችግረኛ አድርጓል፣ እናም በትክክል በዚህ ምክንያት ስራውን አከናውኗል።

ይህ የክርስቲያን አያዎ (እርስ በእርሱ የሚጻረር አባባል) ነው፡ እግዚአብሔር የሚያድነው በመስራት ብቻ ሳይሆን ራሱን በመስጠት ጭምር ነው። ክፉን በኃይል በማሸነፍ ሳይሆን የፍቅርን ድካም እስከ መጨረሻው በመቀበል ነው። በመስቀል ላይ፣ ኢየሱስ ሰው እራሱን ኃይል እንዳለው አድርጎ እንደማይገነዘብ፣ ነገር ግን ለሌሎች ክፉ እና ጠላቶች በሚሆኑበት ጊዜም ታማኝ በሆነ ግልጽነት ውስጥ እንዳለ ያስተምረናል። መዳን በራስ ገዝነት ውስጥ አይገኝም፣ ነገር ግን የራስን ፍላጎት በትህትና በማወቅ እና በነጻነት መግለጽ በመቻል ነው።

በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የሰውነታችን መሟላት የጥንካሬ ተግባር ሳይሆን የመተማመን ምልክት ነው። ኢየሱስ የሚያድነው በአስደናቂ መንገድ ሳይሆን ራሱ ሊሰጥ የማይችለውን ነገር በመጠየቅ ነው፣ የእውነተኛ ተስፋ በር የሚከፈተው እዚህ ነው፡ የእግዚአብሔር ልጅ እንኳን ራሱን መቻልን ካልመረጠ፡ ጥማችን - ለፍቅር፣ ለትርጉም፣ ለፍትህ - የእውነት እንጂ የውድቀት ምልክት አይደለም።

ይህን እውነት፣ በጣም ቀላል የሚመስል፣ ነገር ግን ለመቀበል አስቸጋሪ የሆነ ነገር ነው። የምንኖረው እራስን መቻልን፣ ቅልጥፍናን፣ አፈጻጸምን በሚሸልመው ጊዜ ላይ ነው። ነገር ግን ወንጌሉ የሚያሳየን የሰው ልጅ መሆናችን የሚለካው ልናሳካው በምንችለው ነገር ላይ ተንተርሶ ብቻ ሳይሆን ራሳችንን እንድንወደድ በመፍቀድ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በመረዳዳት ነው።

ኢየሱስ ያድነናል፣ መጠየቅ የማይገባን ነገር ሳይሆን ነጻ የሚያወጣ መሆኑን በማሳየት ነው። እንደገና ወደ ኅብረት ቦታ ለመግባት ከኃጢአት መደበቂያ መውጫ መንገድ ነው። ከመጀመሪያው ጀምሮ ኃጢአት እፍረትን ወልዷል። ነገር ግን ይቅርታ - እውነተኛ ይቅርታ - የሚወለደው ፍላጎታችንን ማሟላት ስንችል እና ውድቅ መደረግን ሳንፈራ ነው።

የኢየሱስ በመስቀል ላይ የነበረው ጥማት የእኛም ጥማት ነው። የህይወት ውሃ የሚፈልገው የቆሰለው የሰው ልጅ ጩኸት ነው። ይህ ጥማት ደግሞ ከእግዚአብሔር አያርቀንም፣ ይልቁንም ከእርሱ ጋር አንድ ያደርገናል። እውቅና ለመስጠት ድፍረት ካገኘን ደካማነታችን እንኳን ወደ ሰማይ የሚያደርሰው ድልድይ መሆኑን ልናውቅ እንችላለን። የነፃነት መንገድ የሚከፈተው በትክክል በመጠየቅ - በመያዝ ሳይሆን - እራሳችንን የቻልን መስሎ መቅረብ ስናቆም ነው።

በወንድማማችነት፣ በቀላል ሕይወት፣ ያለ እፍረት በመጠየቅ ጥበብ ውስጥ ያለ ስውር ዓላማ፣ ዓለም የማያውቀው ደስታ ተወለደ። ወደ መጀመሪያው የመሆናችን እውነት የሚመልሰን ደስታ፡ ፍቅርን እንድንሰጥ እና እንድንቀበል የተፈጠርን ፍጡራን ነን።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በክርስቶስ ጥማት የራሳችንን ጥማት ሁሉ ማወቅ እንችላለን። እናም፡- ያስፈልገኛል ከማለት የበለጠ ሰብአዊ፣ ምንም መለኮታዊ ነገር እንደሌለ ለመማር ዝግጁ መሆን አለብን። በተለይ የማይገባን መስሎን ለመጠየቅ አንፍራ። እጃችንን ለመዘርጋት አንፈር። እዚያ ነው፣ በዚያ የትህትና እንቅስቃሴ ውስጥ መዳን ተሸሽጎ ይገኛል።

03 Sep 2025, 11:43