MAP

የር.ሊ.ጳ የነሐሴ ወር የጸሎት ሐሳብ፣ በጋራ መኖር ይቻል ዘንድ እንጸልይ የሚለው ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም ይሆን ዘንድ ያቀረቡት ወራዊ የጸሎት ሐሳብ “ማኅበረሰቦች በጎሳ፣ በፖለቲካ፣ በሃይማኖት ወይም በርዕዮተ ዓለም ምክንያት ከውስጣዊ ግጭቶች እንዲርቁ፣ የውይይት መንገዶችን እንድንፈልግ እና በወንድማማችነት ምልክቶች ለሚፈጠሩ ግጭቶች ምላሽ እንድንሰጥ” እንድንጸልይ ጋብዘውናል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም ይሆን ዘንድ ይፋ ባደረጉት የጸሎት ሐሳብ  “አብሮ መኖር አስቸጋሪ የሚመስላቸው ማኅበረሰቦች በጎሳ፣ በፖለቲካ፣ በሃይማኖት ወይም በርዕዮተ ዓለም ምክንያቶች ግጭት ውስጥ እንዳይገቡ እንጸልይ" ማለታቸው የተገለጸ በጸሎት ውስጥ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ በኢየሱስ ፊት መቆምን፣ የእርሱ ሰላም እንደሚያስፈልገን ያስታውሰናል ማለታቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የምንኖረው በፍርሃት እና በመከፋፈል ጊዜ ውስጥ ነው" ብለዋል። “አንዳንድ ጊዜ ወንድማማቾችና እህቶች መሆናችንን እየረሳን እርስ በርስ የሚለያዩን ግድግዳዎች እየገነባን ብቻችንን እንደሆንን ይሰማናል" ያሉ ሲሆን ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን እንዲልክ “እርስ በርሳችን የመረዳዳትን፣ የመደማመጥን፣ በመከባበርና በመተሳሰብ የመኖርን ፍላጎት በውስጣችን እንዲያድስልን” ልንማጸን እና ልንጸልይ ይገባል ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በመቀጠል ጌታን “የንግግር መንገዶችን ለመፈለግ ድፍረትን እንዲሰጠን፣ በወንድማማችነት መገለጫዎች ለግጭት ምላሽ ለመስጠት፣ ልዩነትን ሳንፈራ ልባችንን ለሌሎች ክፍት ለማድረግ እንችል ዘንድ በዚህ ነሐሴ ወር ለየት ባለ ሁኔታ ጸሎት ማድርግ እንችል ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “ድልድዮችን ገንቢዎች፣ ድንበርና ርዕዮተ ዓለምን ማሸነፍ የምንችል፣ ሌሎችን በልብ ዓይን እንድንመለከት፣ በእያንዳንዱ ሰው የማይናወጥ ሰብዓዊ ክብር እንዲኖረን አድርገን” በማለት ጸልዮዋል።

ሰላማዊ አብሮ መኖርን ማሳደግ

ከዚህ ወር የጸሎት ዓላማ ጋር ተያይዞ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አባ ክሪስቶባል ፎንስ፣ የቅዱስ አባታችንን የጸሎት ሐሳብ በየወሩ የሚያሳትመው የጳጳሱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር - “ሁላችንም ሰላማዊ አብሮ መኖርን ማሳደግ እንችላለን" ሲሉ መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን ይህም፣ “በመጀመሪያ በራስ ላይ የመሥራት አስፈላጊነትን፣ የሰውን ልብ ከኩራት፣  የሚጎዱ እና የሚገድሉ ግምቶችን እና አሉታዊ ቃላትን ማስወገድን ያካትታል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እንደሚያስተምሩን፣ ሰላም በልብ እና ከልብ ይገነባል" ማለታቸው ተዘግቧል።

በሁለተኛ ደረጃ ጭፍን ጥላቻን ወደ ጎን መተውና 'የተለያዩ' ሰዎችን በግምት መፍራትን ማስወገድ ይኖርብናል  ያሉት አባ ፎኔስ በመቀጠል “ሌሎች የሚያበረክቱትን ልዩ የሆነ ነገር ለማዳመጥ በአክብሮት መቅረብ አለብን ብለዋል። በውይይት አንድ የሚያደርገንን መፈለግ እና ለጋራ ጥቅም በጋራ የምንሰራበትን መንገዶች መክፈት ይቻላል ሲሉ የተናግረዋል።

በመጨረሻም አባ ፎንስ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እርስ በርስ የሚስማሙና ሰላማዊ ማኅበረሰቦችን ለመገንባት መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። ይህንንም ማድረግ የሚቻለው፡ በቤተሰብ ላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ፣ የእያንዳንዱን ሰው ክብር በመጠበቅ፣ በተለይም በጣም ደካማ እና በጣም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ፍትህን በማስፈን፣ አለመመጣጠንን ለመፍታት መፈለግ፣ መመሥረት የሚቻለውን እውነት መጠበቅ ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም፣ በዚህ የኢዩቤሊዩ ቅዱስ ዓመት አውድ ውስጥ፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቪዲዮ የተደገፈ መልእክት ልዩ ጠቀሜታ ይኖረዋል፣ ምክንያቱም በእሱ በኩል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በልባቸው የያዙትን የጸሎት ዓላማዎች እናውቃለን። የኢዮቤልዩ ውለታዎችን በትክክል ለመቀበል ለጳጳሱ ዓላማዎች መጸለይ አስፈላጊ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

07 Aug 2025, 11:19