MAP

ቅዱስ አልፎንስዮስ ዘ ሊጉሪ ቅዱስ አልፎንስዮስ ዘ ሊጉሪ  

ር.ሊ.ጳ ሊዮ የግብረ ገብ ሊቃውንት የቅዱስ አልፎንስዮስን ምሳሌ እንዲከተሉ አሳሰቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የዘመናዊውን ዓለም "ተግዳሮቶች፣ ለውጦች እና ግጭቶች" በመለኮታዊ መገለጥ ላይ ሲያሰላስሉ የግበረ ገብ ምሁራን የቅዱስ አልፎንስዮስ ዘ ሊጉሪ እና የሌሎች ቅዱሳን ምሳሌ እንዲከተሉ አሳስቧቸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለ17ኛው ዓለም አቀፍ የግብረ ገብ ነገረ መለኮት ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት “እንደ ቅዱስ አልፎንስዮስ ማሪያ ዘ ሊጉሪ ያሉ ቅዱሳን ጥበበኞች እና ሁል ጊዜ ወቅታዊውን የቅዱሳን ምሳሌ በመከተል” ወደ ዘመናዊ የሥነ ምግባር ጉዳዮች እንዲቀርቡ አበረታተዋል።

የሥነ ምግባር ዶክተር ወይም ሊቅ በመባል የሚታወቀው ቅዱስ አልፎስዮስ "የእግዚአብሔርን ህግጋት፣ የሰውን ሕሊና እና የነጻነት ተለዋዋጭነት ሚዛናዊ ውህደትን ማግኘት ችሏል፣ በተመሳሳይ ጊዜ ለወንድሞቹ የበጎ አድራጎት፣ የመረዳት እና በትዕግስት የተሞላ አመለካከት በመያዝ የእግዚአብሔር ወሰን የለሽ ምህረት የሚታይ ምልክት ሆኗል" ብለዋል ጳጳሱ።

ለጉባኤው በቅዱስነታቸው ስም መልእክቱን ያስተላለፉት የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት በብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ፊርማ በተላለፈው ቴሌግራም ነው።

ቅዱስ አባታችን ዝግጅቱ “በኢየሱስ ክርስቶስ ሙላትን በሚያገኘው መለኮታዊ መገለጥ አንፃር ስላጋጠሙት ተግዳሮቶች፣ ለውጦች እና ወቅታዊ ግጭቶች ለማሰላሰል ምቹ እድል እንደሚፈጥር ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክት "የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእናቶች ጠበቃ፣ የጥበብ መቀመጫ" በአደራ በመስጠት ለተሳታፊዎች እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ከጳጳሱ ሐዋርያዊ ቡራኬ ከተሰጠ በኋላ መልእክቱ ተጠናቋል።  

 

21 Aug 2025, 15:37