MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከቅዱስ እንድሪያስ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ቤት አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከቅዱስ እንድሪያስ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ቤት አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "ክርስቶስን ማወጅ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ተልእኮ ነው" ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከቅዱስ እንድሪያስ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ቤት አባላት ጋር በነሐሴ 23/2017 ዓ.ም በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ሁሉም ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስን የመስበክ ተልእኳቸውን እንዲወጡ ጋብዘዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

መጥምቁ ዩሐንስ መስዋዕት የሆነበት እለት በሚዘከርበት ቀን ላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ወንጌልን በሚገባ ለማወጅ ይቻል ዘንድ የካቶሊክ ምእመናን እና ቀሳውስትን የማብቃት አገልግሎት እየሰጠ ከሚገኘው የቅዱስ እንድርያስ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ቤት አባላት ጋር ተገናኝተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ሕይወትና አገልግሎት ለዘመናችን ሚስዮናውያን እንደ አብነት ሊጠቀስ እንደ ሚችል አመልክተዋል።

የዮሐንስ ወንጌል መጥምቁ ዮሐንስ "ቃልም ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ" ብሎ እንደ መሰከረ የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “የአራተኛውን ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፎች ደግመን በጥሞና ካነበብን የእያንዳንዱ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ቤት ቁልፍ የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ማወቅ እንችላለን - ስለታሰበው ነገር ለመመስከር ከሕይወት አምላክ ጋር ስለተሰላሰለው ግንኙነት ማወቅ እንችላለን” ብለዋል።

ያየነውንና የሰማነውን ማወጅ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የቤተ ክርስቲያንንና የእያንዳንዱን ክርስቲያን ተልእኮ የሚገልጽ የቅዱስ ዮሐንስን የመጀመሪያ መልእክት በማስታወስ፡- “እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን። ኅብረታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው" (1ኛ ዩሐንስ 1፡3) የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በቅንነት ማወጅ ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ሁሉም የቅዱስ እንድርያስ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ቤት አባላት እንደ የተጠመቁ ክርስቲያኖች ተልእኳቸውን እንዲቀበሉ፣ ሁሉም ሰው ክርስቶስን እንዲያውቅ እና እንዲወድ ማገዝ እንደ ሚገባ ተናግረዋል።

“በእነዚህ የአምልኮ ቀናት ውስጥ፣ “እንደ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በቃልና በበጎ ሥራ​​በመግለጥ ታማኝ የኢየሱስ ተከታዮች የሆኑትን የቅዱሳንን ሕይወት እንድታስቡ በልዩ መንገድ እጋብዛችኋለሁ" ያሉ ሲሆን  በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የአሜሪካ አህጉር ደጋፊ የሆነችው የጓዳሉፔ እመቤታችን እንድትጠብቃቸው እና በአዲስ ተስፋ እንድትመራቸው ጸሎት አድርገዋል።

የቅዱስ እንድርያስ የወንጌል ትምህርት ቤት

የቅዱስ እንድርያስ የወንጌል ትምህርት ቤት ምእመናንን እና ቀሳውስትን ኢየሱስ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለመስበክ ያቀረበውን ጥሪ ምላሽ በመስጠት እየተጋ የሚገኝ ተቋም ሲሆን በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ እንደተገለጸው የኢየሱስን ስብከት ከሰማ በኋላ ወንድሙን ጴጥሮስን የሰበከው በሐዋርያው​​እንድርያስ ስም የተሰየመ ተቋም እንደ ሆነም ተገልጿል።

የወንጌል ትምህርት ቤት ተልእኮ “እንደ ጴጥሮስ ከራሳችን በተሻለ ጌታን መውደድ፣ ማገልገል እና ማወጅ የሚችሉ ሰዎችን በማግኘታችን የእንድርያስን ምሳሌ መከተል ነው።

29 Aug 2025, 14:18