ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለሪሚኒ ስብሰባ ባስተላለፉት መልእክት "ተስፋ ቅር አያሰኘንም" ማለታቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን ዋና ጸኃፊ በብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ሐሙስ ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም ተፈርሞ ይፋ በሆነው መልእክት፣ በሕዝቦች መካከል ሊኖር ስለሚገባው ወዳጅነት የተመለከተ ስብሰባ ላይ የሚሳተፉትን -በተለምዶ “የሪሚኒ ስብሰባ” እየተባለ የሚጠራውን፣ ሰላም ገንቢ፣ በተስፋ የተሞሉ፣ ለጋራ ጥቅም የሚሠሩ እንዲሆኑ አበረታተዋል።
እ.አ.አ ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ በየአመቱ በሰሜናዊ ጣሊያን የባህር ከተማ ሪሚኒ በነሐሴ ወር ማገባደጃ ላይ በህዝቦች መካከል ወዳጅነትን ለመፍጠር ታስቦ የሚካሄድ ስብሰባ አካል ነው። የዘንድሮው ስብሰባ መሪ ሃሳብ "በባዶ ቦታዎች ላይ በአዲስ ጡቦች እንገነባለን" የሚል ነው።
የሪሚኒ ስብሰባ በሕብረት እና የነጻነት ንቅናቄ የሚዘጋጅ አመታዊ ዝግጅት ሲሆን በርካታ ምእመናን የሚገኙበት እና ከተለያዩ ከፍተኛ ግለሰቦች ጋር በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የሚነጋገሩበት ነው። እንዲሁም ለግለሰቦች፣ ቤተሰቦች እና ልጆች ለዝግጅቱ የሚሆን የተለያዩ ድንኳኖችን እና እንቅስቃሴዎችን ያቀርባል።
ተስፋ ቅር አያሰኘንም (ሮሜ 5፡5)
ለረሚኒ ስብሰባ ተካፋዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ባስተላለፉት መልእክት “ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ (. . .) የተመረጠና የከበረ፣ የሚያምንም አያፍርም” በማለት ይህንን “በደስታ እንዲገነዘቡ” ያላቸውን “ልባዊ ተስፋ” ለአዘጋጆቹ፣ ለበጎ ፈቃደኞች እና ለመላው ተሳታፊዎች በመግለጽ ሰላምታ ያቀረቡ ሲሆን "ተስፋ በፍጹም ቅር አያሰኘንም" (ሮሜ 5፡5) ማለታቸው ተገልጿል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በረሃዎች በተለምዶ “ወደ ጎን የተጣሉ” እና “ለሕይወት የማይበቁ ተብለው የሚታሰቡ” ቦታዎች ሲሆኑ፣ ጳጳሱ ግልጽ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። “ምንም ነገር ሊወለድ የማይችል በሚመስልበት ቦታ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔርን ማለፍ ያለማቋረጥ ይናገራሉ” ሲሉ አስታውሷል።
የአልጄሪያ ሰማዕታት
ቅዱስ አባታችን አክለው እንደ ገለጹት “በእነሱ ውስጥ የእግዚአብሔር ልጅ የመወለድ እንቅስቃሴ እና ራስን የመስጠት እንቅስቃሴ በመኮረጅ፣ ሃይማኖቶችን እና ባህሎችን የሚከፋፍሉትን ያለመተማመን ግንቦችን በማሸነፍ ከሁሉም የሰው ዘር ጋር በጥልቅ መግባባት የቤተክርስቲያንን በምድረ በዳ የመኖር ጥሪን ያበራል" ማለታቸው ተገልጿል።
ይህም የአንድነት ጥሪ ነው ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሰኔ ወር በቫቲካን ውስጥ የኢጣሊያን ጳጳሳትን ባነጋገሩበት ወቅት “በአመጽ የትምህርት ጎዳናዎችን፣ በአካባቢው ግጭቶች ውስጥ የሽምግልና ውጥኖችን እና የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮጄክቶችን ለማስፋፋት የሌላውን ፍርሃት ወደ የመገናኛ ዕድል የሚቀይሩ ፕሮጄክቶችን በአደራ እንደ ሰጧቸው በመግለጽ፣ እኛም ሕዝቦች እንዲገናኙ የራሳችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።
ሰላም በየዕለቱ በምናከናውናቸው ተግባራት የሚገነባ ትሁት መንገድ ነው።
በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እያንዳንዱ ማህበረሰብ ‘የሰላም ቤት’ እንዲሆን፣ “ጠላትነት በውይይት የሚቀልጥበት፣ ፍትህ የሚከበርበት፣ ይቅርታ የሚደረግበት” እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ቅዱስ አባታችን በዚህ ስሜት ሁሉም ሰዎች "እምነት፣ ተስፋ፣ እና ፍቅር ወደ ጥልቅ የባህል ለውጥ እንዲተረጉሙ" አበረታተዋል።
ለጋራ ጥቅምና ሰላም
ይህም “ፍትሃዊና ዘላቂነት የጎደለው የእድገት ጎዳና አማራጭ” የሆኑትን የዕድገት መንገዶችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግ ቅዱስ አባታችን ጠቁመዋል።
“ሕያው እግዚአብሔርን ለማገልገል፣ ፍትሕን፣ የመገናኘትና ሐሳብ የመለዋወጥ ነፃነትን፣ የሁሉንም የጋራ ተጠቃሚነት-በመጨረሻም ራሱ ሰላምን የሚጎዳውን ትርፍ የማጋበስ ጣዖት አምልኮን መተው አለብን ያሉ ሲሆን
"ራሱን ከአለም በረሃማነት የማያርቅ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለመታገስ አስተዋፅኦ የማያደርግ እምነት ከንግዲህ የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዝሙር አይሆንም" ሲሉ አስጠንቅቋል።
ቀጣይነት ያለው የዲጂታል አብዮት አደጋዎች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዘመናዊው ኅብረተሰብ ላይ በማሰላሰል በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ሊዘነጉ እንደማይችሉ አስተውለዋል።
"በመካሄድ ላይ ያለው ዲጂታል አብዮት አድልዎ እና ግጭትን የሚያባብስ አደጋ አለው፤ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስን የሚታዘዙ ልጆች እንጂ ባሪያዎች ባልሆኑ ሰዎች የፈጠራ ችሎታ መኖር አለበት" ሲሉ አስጠንቅቋል። ከዚያም በረሃው የአትክልት ስፍራ ይሆናል፣ እናም በቅዱሳን ትንቢት የተነገረላት "የእግዚአብሔር ከተማ" ባድማ ቦታዎቻችንን ይለውጣል ያሉ ሲሆን በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ቡራኬያቸውን ሰጥተው የንጋት ኮከብ የሆነችውን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት ከተማጸኑ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።