MAP

የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ሲምፖዚዬም 20ኛ ጉባኤ በኪጋሊ የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ሲምፖዚዬም 20ኛ ጉባኤ በኪጋሊ  

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ፥ የአፍሪቃ ጳጳሳት ተግባር የኢየሱስን ፍቅር ጥልቅ ልምድ የሚያዳብር እንዲሆን አሳሰ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ ለአፍሪካ እና ማዳጋስካር ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ሲምፖዚዬም (SECAM) 20ኛ ጉባኤ መልዕክት አስተላልፈዋል። የጉባኤው ተካፋዮች “ኢየሱስ ክርስቶስ የተስፋ፣ የእርቅ እና የሰላም ምንጭ ነው” የሚለውን መሪ ርዕሥ መሠረት በማድረግ ያቀረቡት ጸሎት፥ የሰዎችን ልብ የሚያነቃቃ እና የእግዚአብሔርን ፍቅር ጥልቅ ልምድ ለማዳበር አስፈላጊ እንደሆነ ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ከሐምሌ 23-28/2017 ዓ. ም. ድረስ ለተካሄደው 20ኛው የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ጠቅላላ ስብሰባ በላኩት መልዕክት፥ በአኅጉሪቱ ውስጥ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለሰው ልጆች በሙሉ ተጨባጭ የተስፋ ምልክት ሆና እንደምትቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ የተስፋ፣ የእርቅ እና የሰላም ምንጭ ነው” የሚለውን የጉባኤውን መሪ ርዕሥ መሠረት በማድረግ፥ በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ከሐምሌ 23-28/2017 ዓ. ም. ድረስ ጉባኤያቸውን ላካሄዱት ለኪንሻሳ ሊቀ ጳጳስ እና የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ሲምፖዚዬም ፕሬዚዳንት ለብፁዕ ካርዲናል ፍሪዶሊን አምቦንጎ ቤሱንጉ እና ለጉባኤው ተሳታፊዎች በሙሉ መልዕክት ልከዋል።


በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የቴሌግራም መልዕክት ለጉባኤው ተሳታፊዎች የላኩት በቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እንደሆኑ ታውቋል።

ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ ክርስቶስ የተስፋ፣ የእርቅ እና የሰላም ምንጭ ነው” የሚለውን የጉባኤውን መሪ ሃሳብ መሠረት በማድረግ በላኩት መልዕክት፥ የጉባኤው ተሳታፊዎች በመሪ ሃሳቡ ላይ በማስተንተን ያደረጉት ውይይት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን አስተማማኝ የመዳን ተስፋን እና ልባቸውን የሚያነቃቃ የእግዚአብሔርን ፍቅርን ለማዳበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፥ ይህም በተለይም በመከፋፈል እና በልዩነት በተጎዳ ኅብረተሰብ ውስጥ አንድነትን እንዲያነሳሳ እና እንዲያበረታታ በማለት ጸሎት አድርሰዋል።

“በዚህም መንገድ በየአገሮቻቸው የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለሰው ልጆች በሙሉ የተስፋ ምልክት ሆና እንደምትቀጥ ያላቸውን እምነት ገልጸው፥ መልዕክታቸውን ሲያጠቃልሉት በሰጡት ማረጋገጫም ቀጣይ ዕቅዶቻቸውን የተስፋ እናት ለሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በአደራ ሰጥተው፥ ከእግዚአብሔር በሚገኝ ኅብረት ጸንተው እንዲቆዩ በአፅንዖት በማሳሰብ ለጉባኤው ተሳታፊዎች በሙሉ ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ሰጥተዋቸዋል።

 

04 Aug 2025, 17:17