ር.ሊ.ጳ ሊዮ በኢዮቤልዩ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ የሚገኙትን የቬኔስ እስረኞችን ተቀብለው አነጋገሩ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ከቬኒስ የቅድስት ማርያም ዐብይ እስር ቤት ሶስት እስረኞች ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐሙስ በቫቲካን ከተቀበሏቸው ምዕመናን መካከል ይገኙበታል። የቡድኑ የኢዮቤልዩ ጉዞ ወደ 500 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን የመጨረሻውን መቶ ኪሎ ሜትሮች ከጣሊያን ከተማ ቴርኒ ተነስተው ወደ ሮም በእግር መጓዝን ያካትታል።
መንፈሳዊ ተጓዦቹ የቬኒስ ፓትርያርክ ሊቀ ጳጳስ ፍራንችስኮስ ሞራሊያ ያካተተ ሲሆን፣ የእስር ቤቱ መንፈሳዊ አባት የሆኑት አባ ማሲሞ ካዳሙሮ ከሌሎች የጠቅላይ ቤተ ክህነት ባለስልጣናት ጋር አብረው እንደ ሆነም ተግልጿል።
አባ ካዳሙሮ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ እንደ ተናገሩት “ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር የተደረገው ስብሰባ ይህን የኛን ልምድ፣ መንፈሳዊ ንግደት እና የአምልኮ ጉዞ በእውነት ሙሉ ያደርገዋል፣ ይህም ሙሉ በሙሉ በታመነ ተስፋ ስር የተደረገ ነው፣ ይህም ሙሉ በሙሉ የታመነ ተስፋ ምልክት የሆነ መንፈሳዊ ጉዞ ነው፣ ለሁሉም ሰዎች እውነተኛ ህይወት፣ ነፃ እና ለታሰሩ አስፈላጊ ልኬትን የሚወክል ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የቅድስት ማርታ ዐብይ እስር ቤት ዳይሬክተር አቶ ኤንሪኮ ፋሪና ሐሙስ ዕለት ከቅዱስነታቸው ጋር በነበረው ቆይታ ላይ የተገኙ ሲሆን በወቅቱ በሰጡት አስተያየት እስረኞች “በከባድ ሰብዓዊና መንፈሳዊ ጉዞ” እንዲካፈሉ የመፍቀድ አጋጣሚ የእርሳቸው በመሆኑ እጅግ በጣም ደስ እንደሚያሰኛቸው አክለው ገልጸዋል። እስረኞቹም “በዚህ ጥልቅ ትርጉም ያለው ጉዞ” በመነሳሳት አስተያየቶችን እና ጸሎቶችን የያዘ ማስታወሻ ደብተር እንደሚሰጣቸውም ጠቁመው ሂደቱን ከመንፈሳዊ ነጋዲያን ጋር በጋራ በመካፈላቸው ትልቅ ክብር እንደተሰማቸው ተናግሯል።
በሰኔ ወር ከቬኔስ እና አካባቢው ለመጡ የዘርዓ ክህነት ተማሪዎች (ሴሚናሪስቶች) የኢዮቤልዩ ታዳሚዎችን ተከትሎ፣ የሐሙስ የነሐሴ 1/2017 ዓ.ም ክስተት "ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር የተደርገ ሌላ ታላቅ ገጠመኝ እና ስጦታ" ነው፣ እሱም የሕግ ታራሚዎች በመንፈሳዊ ንግደቱ መጨረሻ ላይ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር ለመገናኘት ጥያቄ አቅርበው እንደ ነበረ ሊቀ ጳጳስ ሞራሊያ ተናግረዋል።
የቬኒስ ፓትርያርክ አክለው እንደ ገለጹት ከሆነ ይህ መንፈሳዊ ንግደት እና ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሚደርገው ግንኙነት “እርግጠኛ ነኝ—በእነዚህ ታራሚዎች ነፍስ፣ ህይወት እና ታሪክ ላይ የማይጠፋ አሻራ የሚተው ተሞክሮ ነው፣ አብረዋቸው ባሉ ሰራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች እና እንዲሁም በሁሉም የሀገረ ስብከት አገልግሎት በማረሚያ ቤቶች እና እንዲሁም በወንድ እና ሴት እስረኞች ሕይወት እንደገና እንዲዋሃዱ የሚያደርግ ልምድ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
"የኢዮቤልዩ ጉዞ፣ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር የመገናኘት እድል የፈጠረ ነበረ" በማለት በድጋሚ የተናገሩት የቬኒስ ሊቀ ጳጳስ "ቀጣይ እና ሁሉን አቀፍ ቁርጠኝነት" በአካባቢ እስር ቤቶች ውስጥ እስረኞችን ለመንከባከብ ያለው ቁርጥ ፈቃድ አካል ነው። የዚያ ቃል ኪዳን አካል የሆነው ሊቀ ጳጳስ ሞራሊያ በቅርብ ሳምንታት ከጣሊያን የፍትህ ሚኒስትር ካርሎ ኖርዲዮ ጋር ተገናኝተው በቬኒስ እና አካባቢው ስላለው የእስር ቤቶች ሁኔታ እንዲሁም እስረኞችን የቅጣት ፍርዳቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ሲቪል ማህበረሰብ ለመቀላቀል በሚደረገው ጥረት ላይ ተወያይተዋል።