MAP

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ጌታ መልካም በማድረግ እንድንጸና ይጋብዘናል ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአሁኑ ወቅት በሮም አቅራቢያ በሚገኘው ካስተል ጋንዳልፎ በመባል በሚታወቀው ስፍራ የክርምት የእርፍት ጊዜያቸውን እያሳለፉ እንደ ሆነ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በነሐሴ 11/2017 ዓ.ም ከእዚያው ስፍራ ሆነው ካደረጉት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበውና “በምድር ላይ እሳትን ልጥል መጣሁ፤ አሁን ቢቀጣጠል ምንኛ በወደድሁ? ነገር ግን የምጠመቃት ጥምቀት አለችኝ፤ እስክትፈጸምም ድረስ እንዴት እጨነቃለሁ? በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፤ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ። ከአሁን ጀምሮ በአንዲት ቤት አምስት ሰዎች ይኖራሉና፤ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ሁለቱም በሦስቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ። አባት በልጁ ላይ ልጅም በአባቱ ላይ፥ እናት በልጇ ላይ ልጇም በእናትዋ ላይ፥ አማት በምራትዋ ላይ ምራትም በአማትዋ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ" (ሉቃስ 12፡49-53) በሚለው እና ሁሉን ነገር ትቶ ኢየሱስን መከተል እንደሚገባ በሚገልጸው በቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደርጉት አስተንትኖ ጌታ መልካም ነገሮችን በማድረግ እንድንጸና ይጋብዘናል ማለታቸው ተግልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በወቅቱ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ!

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል በጣም አስፈላጊ የሆነውን ጽሑፍ አቅርቦልናል (ሉቃ. 12፡49-53)፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እና የተከታዮቹ ተልእኮ እንኳ “የጽጌረዳ አልጋ” (አልጋ በአልጋ) እንዳልሆነ ለማስተማር፣ በተቃራኒው ደግሞ “የግጭት ምልክት” (ሉቃ. 2፡34) መሆኑን ለማስተማር ጠንካራ ምስሎችን እና ታላቅ ቅንነትን ይጠቀማል።

በዚህ መንገድ ጌታን በኢየሩሳሌም ሲቃወሙት፣ ሲታሰር፣ ሲሰደብ፣ ሲሰቃይ፣ ሲሰቀል ምን ሊገጥመው እንደሚችል አስቀድሞ አውቋል። የፍቅር እና የፍትህ መልእክቱ ውድቅ ሲደረግ፣ የሕዝቡ መሪዎች ለስብከቱ ክፉ ምላሽ ሲሰጡ ተመልክቷል። ከዚህም በላይ፣ ወንጌላዊው ሉቃስ የጻፈባቸው ብዙ ማህበረሰቦችም ተመሳሳይ ነገር እያጋጠማቸው ነበር። የሐዋርያት ሥራ እንደሚነግረን፣ ምንም እንኳን የራሳቸው የአቅም ገደብ ቢኖርባቸውም፣ የቻሉትን ያህል ለመኖር የፈለጉ ሰላማዊ ማኅበረሰቦች ነበሩ፣ የመምህሩን የፍቅር መልእክት (ሐዋ. 4፡32-33) ናቸው። ሆኖም ስደት ይደርስባቸው ነበር።

ይህ ሁሉ የሚያስገነዝበን መልካም መሆን ወይም መሥራት ሁልጊዜ አዎንታዊ ምላሽ እንደማይሰጥ ነው። በተቃራኒው ውበቱ አንዳንድ ጊዜ የማይቀበሉትን ስለሚያናድድ አንድ ሰው ከባድ ተቃውሞ አልፎ ተርፎም እብሪተኝነት እና ጭቆና ሊደርስበት ይችላል። በእውነት መስራት ዋጋ አለው ምክንያቱም በአለም ላይ ውሸትን የሚመርጡ ሰዎች አሉ፣ እናም ዲያቢሎስ በሁኔታው ተጠቅሞ የጥሩ ሰዎችን ድርጊት ለመት ይሞክራል።

ኢየሱስ ግን በዚህ አስተሳሰብ እኛ እንድንሸነፍ እና እንድንስማማ ሳይሆን እንድንሰቃይ ለሚያደርጉን እንኳን ለጥቅማችን እና ለሁሉ ጥቅም እንድናደርግ በእሱ እርዳታ ይጋብዘናል። ለኩራት በበቀል ምላሽ እንዳንሰጥ ይልቁንም፣ በፍቅር ለእውነት ታማኝ እንድንሆን ይጋብዘናል። ይህንንም ሰማዕታት ስለ እምነታቸው ደማቸውን በማፍሰስ መስክረዋል። እኛም የእነርሱን ምሳሌ በተለያዩ ሁኔታዎችና መንገዶች መኮረጅ እንችላለን።

ለምሳሌ ያህል ጥሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ጤናማ በሆኑ መሠረታዊ ሥርዓቶች ለማስተማር ከፈለጉ የሚከፍሉትን ዋጋ እናስብ። ውሎ አድሮ "አይ" ብለው ልጆቻቸውን ማረም አለባቸው፣ ይህ ህመም ያመጣባቸዋል። ተማሪዎችን በአግባቡ ለማስተማር ለሚፈልግ መምህር ወይም ሙያዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም ፖሌቲካዊ ተልእኳቸውን በታማኝነት ለመወጣት ለሚፈልግ መምህርም እንዲሁ ነው። በወንጌል አስተምህሮ መሰረት ኃላፊነቱን በቋሚነት ለመወጣት ለሚጥር ሁሉ እውነት ነው።

በዚህ ረገድ የአንጾኪያው ቅዱስ አትናቲዮስ ሰማዕትነትን ለመቀበል ወደ ሮም ሲሄድ ለዚያች ከተማ ክርስቲያኖች እንዲህ ሲል ጽፎላቸው ነበር፡- “እግዚአብሔርን ደስ ታሰኙ ዘንድ እንጂ ሰውን ደስ እንድታሰኙ አልሻም" (ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡1)። አክሎም፣ “እስከ በምድር ዳርቻ ድረስ ከመንገሥ ይልቅ በኢየሱስ ክርስቶስ መሞት ይሻለኛል” ሲል ጽፎ ነበር።

ወንድሞች እና እህቶች፣ የሰማዕታት ንግሥት የሆነችውን ማርያምን በአንድነት እንማጸናት፣ በማንኛውም ሁኔታ ለልጇ ታማኝ እና ደፋር ምስክሮች እንድንሆን እና ዛሬ በእምነት ምክንያት የሚሰቃዩ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እርሷ በአማላጅነቷ እንድትደግፋቸው ልንማጸናት ይገባል።

18 Aug 2025, 10:33

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >