MAP

ር.ሊ.ጳ ሊዮ እና የፈረንሣይ የክርስቲያን የፖለቲካ ፓርቲ ተመራጮች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ሊዮ እና የፈረንሣይ የክርስቲያን የፖለቲካ ፓርቲ ተመራጮች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (@VATICAN MEDIA)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ለክርስቲያን ፖለቲከኞች ‘እሴቶች’ ያለ ክርስቶስ ዓለምን ሊለውጡ አይችሉም" ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለፈረንሣይ የክርስቲያን እምነት ተከታይ የፖለቲካ ፓርቲ ተመራጮች ባስተላለፉት መልእክት የክርስቲያን የፖለቲካ መሪዎች ወደ ኢየሱስ ዘወር እንዲሉ፣ እምነታቸውን ሳይሸራረፉ እንዲኖሩና ስለ እርሱ እንዲመሰክሩ፣ ዘመናዊ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ እና ዓለምን የተሻለች ለማድረግ እንዲተጉ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐሙስ ዕለት ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም “ኢየሱስ በሞቱና በትንሳኤው ያገኘው መዳን የሁሉንም የሰው ልጅ የሕይወት ዘርፎች ማለትም ባህልን፣ ኢኮኖሚንና ሥራን፣ ቤተሰብንና ጋብቻን፣ ለሰው ልጅ መብትና ሕይወት መከበርን፣ ጤናን፣ እንዲሁም ግንኙነትን፣ ትምህርትን እና ፖለቲካን ያጠቃልላል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከፈረንሳይ የቫል-ዴ-ማርን ፓርቲ ለተመረጡ ባለስልጣናት ባደረጉት ንግግር ወደ ሮም የሚያደርጉት የኢዮቤልዩ “የእምነት ጉዞ” ወደ እለታዊ ቃል ኪዳናቸው “በተስፋ የተጠናከሩ” እና “ፍትሃዊ፣ የበለጠ ሰብአዊ እና የበለጠ ወንድማማችነት የሰፈነበት ዓለም ለመገንባት በተሻለ ሁኔታ የታጠቁ " የሚለው የፓርቲያቸው መሪ ቃል እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን - ይህም በወንጌል ከተሞላው ዓለም የበለጠ ምንም ሊሆን አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።

ወደ ኢየሱስ ዞር በሉ እና የእርሱን እርዳታ ፈልጉ

ምዕራቡ ዓለም ክርስቲያኖች “ወደ ክርስቶስ ለመመለስ እና ኃላፊነታችንን ለመወጣት እንዲረዳን ከመጠየቅ የተሻለ ነገር ማድረግ እንደማይችሉ” ቅዱስነታቸው አበክረው አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ክርስቶስን በማቀፍ የሲቪል መሪዎች "ለራሳቸው" ብቻ ሳይሆን የሚያገለግሉትን በተሻለ ሁኔታ ሊጠቅሙ እንደሚችሉ አስረድተዋል።

በትክክል በምስጢረ ጥምቀት በተሰጠን በጎ ነገር የማድረግ ጸጋ ምክንያት ወደ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ በጎ አድራጎት ይመራናል፣ የክርስቲያን መሪዎች “የአሁኑን ዓለም ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ” ተዘጋጅተዋል፣ እናም በእምነታቸው እስከመሰከሩ ድረስ “እሴቶችን’' ማስተዋወቅ ምንም ያህል ወንጌላዊ ቢሆኑም ከክርስቶስ መንፈስ “ባዶ” ከሆኑ “ዓለምን ለመለወጥ ምንም አቅም የላቸውም” ሲሉ ቅዱስነታቸው አስጠንቅቋል።

‘በእምነት ራሳችሁን ማበርታት’

በዚሁ ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በምርጫ ላሸነፉት የፖለቲካ ፓርቲ ባለሥልጣናት በተለይም በምዕራባውያን ማህበረሰቦች ውስጥ "ክርስቶስ እና ቤተክርስቲያኑ የተገለሉበት፣ ብዙ ጊዜ ችላ የሚባሉበት እና አንዳንዴም የሚሳለቁበት" እንደ ሆነ ገልጸው ተግባራቸውን በእምነታቸው መሰረት ማከናወን ቀላል እንዳልሆነ አምነዋል።

ቢሆንም፣ ለክርስቲያን ፖለቲከኞች በክርስትናቸው እና በህዝባዊ ሚናቸው መካከል በባህሪያቸው መለያየት እንደማይቻል በማሳሰብ “ከክርስቶስ ጋር አብዝተው እንዲተባበሩ፣ በእርሱ እንዲኖሩ እና ስለ እርሱ እንዲመሰክሩ” አበረታቷቸዋል።

"ስለዚህ የተጠራችሁት በእምነት ራሳችሁን እንድታጠነክሩ ነው" ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው እናም "ስለ ትምህርቱ -በተለይም ስለ ማህበራዊ አስተምህሮው—ኢየሱስ ለአለም ያስተላለፈውን አስተምሮ በጥልቀት እንድትረዱ እና በተግባራችሁ እንድትጠቀሙ እና ህጎችን በማውጣት እንድትተገብሩት" እጠይቃችኋለሁ ብለዋል።

ይህ ትምህርት በሰዎች ተፈጥሮ እና “ሁሉም ሊገነዘበው በሚችለው” የተፈጥሮ ህግ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመጥቀስ፣ ክርስቲያን ፖለቲከኞች “በእርግጠኝነት ሀሳብ ለማቅረብ እና ለመጠበቅ አትፍሩ” በማለት በማበረታታት “ይህ ለእያንዳንዱ ሰው የሚጠቅም እና ሰላማዊ፣ ስምምነት፣ ብልጽግና እና የታረቁ ማህበረሰቦችን ለመገንባት ያለመ የመዳን ትምህርት ነው” ብለዋል።

29 Aug 2025, 11:36