MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከድሆች ጋር የምሳ ግብዣበተቋደሱበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከድሆች ጋር የምሳ ግብዣበተቋደሱበት ወቅት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር በጣም ውብ ፍጥረት ነን ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአሁኑ ወቅት በሮም አቅራቢያ በሚገኘው ካስተል ጋንዳልፎ በመባል በሚታወቀው ስፍራ የክርምት የእርፍት ጊዜያቸውን እያሳለፉ እንደ ሆነ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በነሐሴ 11/2017 ዓ.ም በጳጳሳዊ ቪላዎች የአትክልት ስፍራ ውስጥ በካሪታስ አልባኖ ድጋፍ በተዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ ከድሆች ጋር ምሳ ከመካፈላቸው በፊት እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር አምሳል እንደተፈጠርንና “የእግዚአብሔርን መገኘት በሁሉም ሰው ውስጥ ማየት እንችላለን” ሲሉ አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ተፈጥሮ እና ፍጥረት ባሳዩት ውበት በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የጳጳሳዊ ቪላ የአትክልት ስፍራ እና ከድሆች ጋር ለምሳ በተዘጋጀው ትልቅ ድንኳን ስር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ንግግር ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን “ከፍጥረት ሁሉ የላቀው የሚያምረው በእግዚአብሔር አምሳል የተሠራው ማለትም እያንዳንዳችን የሰው ልጆች ነን” የሚለውን እውነታ እንዲያሰላስሉ ጋብዘው ነበር።

እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔርን መልክ ያንጸባርቃል ብሏል። ይህንን እውነት ሁልጊዜ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት ማየት እንችላለን። እናም፣ የዛሬ ከሰአት በኋላ ያለው የምሳ ግብዣ -በቦርጎ ላውዳቶ ሲ' እና በአልባኖ ላዚያሌ ሀገረ ስብከት የተዘጋጀ -የመገናኘት፣ የወንድማማችነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ልምምድ ነው ሲሉ ቅዱስነታቸው አስረድተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በልባኖ ከድሆች ጋር ምሣ በተቋደሱበት ወቅት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በልባኖ ከድሆች ጋር ምሣ በተቋደሱበት ወቅት   (@Vatican Media)

እንጀራ መቁረስ እና የጌታን ስጦታዎች ማካፈል

ከአልባኖ ሀገረ ስብከት ካሪታስ የሚደገፉትን ድሆች እና አቅመ ደካሞችን፣ የመጠለያ እና የቡድን መኖሪያ ቤቶችን፣ ቤት የሌላቸውን እና በርዳታ መስጫ ማዕከላት የሚደገፉትን በመመልከት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እንጀራ በጋራ መቁረስ ለሁላችንም ትልቅ ትርጉም ያለው ምልክት ነው፡ ይህም በመካከላችን እንዳለ ኢየሱስ ክርስቶስን የምናውቅበት ተግባር” ስላለው ጥልቅ ትርጉም ተናግሯል።

ቀጥለውም “ይህ ልክ እንደ መስዋዕተ ቅዳሴ ነው፣ ነገር ግን ሁላችንም ጌታ የሰጠንን ስጦታዎች እየተካፈልን በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰብስበናል” ብሏል።

ከምግቡ በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “በእኛ ስጦታዎች ላይ”፣ “ይህን ምግብ ለማዘጋጀት በሠሩልን ሁሉ” እና ይህ በዓል እንዲከበር ላደረጉት ሁሉ የአምላክን በረከት እና ቡራኬ እንዲያገኙ ጠይቀዋል። “ጌታ ሆይ ሁል ጊዜ በፍቅርህ አንድ ሆነን እንድንኖር እርዳን” በማለት አክለው ጸልየዋል።

ካርዲናል ባጂዮ 'የቦርጎ ላውዳቶ ሲ' ለተቸገሩ ሁሉ በሩን ይከፍታል።

የላውዳቶ ሲ የላቀ ምስረታ ማእከል ዋና ዳይሬክተር እና የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማት ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፋቢዮ ባጂዮ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱና በቦታው ለተገኙት ሰዎች በሰጡት አስተያየት አጽንዖት ሰጥተው እንደ ተናገሩት “ዛሬ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትንቢታዊ ሕልም ፍጻሜውን እያየን ነው፡ የቦርጎ ላውዳቶ ሲ የመኖሪያ ሥፍራ ብቻ ሳይሆን ወንጌልን የምንኖርበት መንገድ ነው ለእነዚያም የመጀመሪያ መግቢያ በር ነው" ማለታቸው ተገልጿል።

ከንግግሮች ወይም ምርቃት በፊት፣ ወንድማማችነት መጋራት ይመጣል፣ ምክንያቱም “የወንጌል መስተንግዶ የሚጀምረው ከድሆች ነው ያሉ ሲሆን በተጨማሪም "ከማህበራዊ ፍትህ ውጭ ትክክለኛ ሥነ-ምህዳር ሊኖር አይችልም። ይህ የላውዳቶ ሲ' እና የቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ ታላቅ ትምህርት ነው። የክርስቲያን በጎ አድራጎት ፍትህን ያሟላ እና ወደ ተጨባጭ ፍቅር ይለውጠዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

 

18 Aug 2025, 11:44