MAP

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት አባላት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት አባላት   (© Uisg)

ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም የጾምና የጸሎት ቀን ሆኖ እንደሚከበር ተገለጸ!

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት በነሐሴ 08/2017 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ማሕበረሰቦች ዘንድ በሚከበረው የፍልሰታ ማርያም በዓል ዋዜማ ላይ ልዩ የሆነ ዓለም አቀፍ የጾም እና የጸሎት ቀን እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ጦርነት በአለም ላይ ብዙ ህዝቦችን እያሰቃየ ባለበት በሁኑ ወቅት - ከጋዛ እስከ ሱዳን፣ ከዩክሬን እስከ ምያንማር፣ ከሄይቲ፣ እስከ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ እስከ ሶሪያ ድረስ - የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያን/ያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት ለአለም አቀፍ የጾም እና የጸሎት ቀን እንዲሆን አስቸኳይ ጥሪ አቅርቧል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት አባላት እህቶች “የሰላም ሴቶች እንደመሆናችን መጠን በአለም ዙሪያ ያሉ እና በሰው ልጆች ስቃይ ውስጥ የተዘፈቅን፣ ድምፃችንን ከፍ ለማድረግ፣ ልባችንን አንድ ለማድረግ፣ መጸለይ እና እርምጃ መውሰድ በአስቸኳይ እንደሚያስፈልገን ይሰማናል። በጦርነት፣ መፈናቀል እና ኢፍትሃዊነት ለመጣው ዓለም አቀፋዊ ስቃይ ጸሎት እና መተሳሰብ ጠንካራ ምላሽ ነው ከሚለው እምነት በመነሳት የሀይማኖት ማህበረሰቦች እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት መግለጫ “በብዙ ቦታዎች ሰዎች ይታመማሉ፣ ቤቶች ፈርሰዋል፣ ማህበረሰቦች ተጎሳቁለዋል" ሲሉ በመግለጫቸው የገለጹ ሲሆን ይህንን ጉዳይ ደግሞ በዝምታ መመልከት አንችልም ብለዋል። 

በዝምታ መጠበቅ አንችልም

ይህ ቀን በሶስት ተጨባጭ ድርጊቶች ይመራል፡-

- አሁን ካሉት ጦርነቶች እና ሰብአዊ ቀውሶች አንፃር አብረን መጸለይ እና የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላስል።

- የፍትህ እና የእርቅ ጥሪ፣ የሲቪል እና የቤተክርስቲያን ባለስልጣናት የሰላም፣ ትጥቅ የማስፈታት እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ መንገዶችን እንዲከተሉ በማሳሰብ መጸለይ።

- አቀባበል በማድረግ እና በሰብአዊ ርዳታ ትሥሥሮች አማካይነት የሚሰቃዩትን በመደገፍ በተጨባጭ ትብብር ውስጥ ለመሳተፍ ይቻል ዘንድ መጸለይ።

"በዝምታ መጠበቅ አንችልም። ሰላም መገንባት አለበት - እና በጋራ መገንባት አለበት" ሲሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት ጥሪ አቅርበዋል።  በዓመፅ በተሞላ ዓለም ውስጥ፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያት ማሕበራት ዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ህብረት የወንጌል፣ የፍትህ እና የወንድማማችነት ብርሃን አሁንም ሊበራ እንደሚችል ተስፋ እንደምያደርጉም ገልጸዋል።

07 Aug 2025, 11:23