MAP

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን በቫቲካን ሲቀበሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን በቫቲካን ሲቀበሉ   (@VATICAN MEDIA)

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ “በእምነት እና በተስፋ አንድ ልንሆን ይገባል” ሲሉ የዩክሬን ጳጳሳትን አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን በሐዋርያዊ መንበራቸው ተቀብለው ንግግር አድርገውላቸዋል። ቅዱስነታቸው ለብጹዓን ጳጳሳቱ ባደረጉት ንግግር፥ የጳጳሳት ተግባር፥ በእያንዳንዱ ቁስለኛ እና ችግረኛ ላይ የሚታየውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማገልገል ተጨባጭ ዕርዳታን ለማግኘት ወደ ማኅበረሰቦቻችሁ የሚመጣ ሰው ማገዝ መሆኑን በማስታወስ በዩክሬን ውስጥ ቶሎ ሰላም እንዲወርድ እንደሚጸልዩ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በዚህ ሳምንት ውስጥ በሚካሄደው የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ሲኖዶስ ላይ ለመገኘት ወደ ሮም የመጡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ሰኞ ሰኔ 25/2017 ዓ. ም. በቫቲካን ተቀብለው ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል።

በአሁኑ ወቅት የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከከፍተኛ አባት እና መሪ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ስቪያቶስላቭ ጋር የተባበረ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፥ ሁሉንም የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን (UGCC) ጳጳሳት ያቀፈ እንደ ሆነ ታውቋል።

ቅዱስነታቸው ለብጹዓን ጳጳሳቱ ንግግር ሲያደርጉ
ቅዱስነታቸው ለብጹዓን ጳጳሳቱ ንግግር ሲያደርጉ   (@VATICAN MEDIA)

እምነትን እና ተስፋን መመስከር የእግዚአብሔር ጥንካሬ ምልክት ነው

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሐዋርያዊ መንበራቸው ለተቀበሏቸው ጳጳሳት ባደረጉት ንግግር፥ የዘንድሮው የጳጳሳት ሲኖዶስ በኢዮቤልዩ ወቅት እንደሚካሄድ አስታውሰው፥ ይህም “የእግዚአብሔር ሕዝብ በተስፋ እንዲታደስ የሚጋብዝ ነው” ብለዋል።

“ተስፋ፥ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ ባለው ፍቅር ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ማንንም አያስከፋም” ብለው፥ ዩክሬን ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ባለበት በዚህ ጊዜ ስለ ተስፋ መናገር ያስቸግራል ብለዋል። “በዚህ ትርጉም በሌለው ጦርነት ዘመዶቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች የማጽናኛ ቃል ማግኘት ቀላል እንዳልሆነ፥ በተለይም በየቀኑ በልብ እና በሥጋ ከቆሰሉት ሰዎች ጋር ለሚገኙ ጳጳሳት ከባድ እንደሆነ አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለብጹዓን ጳጳሳቱ የሚያደርጉትን ንግግር በመቀጠል፥ “በርካታ የእምነት እና የተስፋ ምስክርነቶች፥ በጥፋት መካከል የሚገለጥ የእግዚአብሐር ጥንካሬ ምልክት ናቸው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ከሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ስቪያቶስላቭ ጋር
ቅዱስነታቸው ከሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ስቪያቶስላቭ ጋር   (@Vatican Media)

በእምነት እና በተስፋ አንድ መሆን

ብጹዓን ጳጳሳትን የሚገጥሟቸው በርካታ የቤተ ክርስቲያን እና ሰብዓዊ ፍላጎቶችን በመገንዘብ፥ በዚህ ጊዜ የጳጳሳቱ ተግባር፥ በእያንዳንዱ ቁስለኛ እና ችግረኛ ላይ የሚታየውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማገልገል ተጨባጭ ዕርዳታን ለማግኘት ወደ ማኅበረሰባቸው ዘንድ የሚመጣን ሰው ማገዝ መሆኑን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሁሉም የዩክሬን ግሪክ ካቶሊክ ምእመናን ጋር ያላቸውን ቅርበት በማረጋገጥ፥ በአንድ እምነት እና በአንድ ተስፋ አንድ ሆነው እንዲቀጥሉ በማሳሰብ፥ ሕይወታቸውን ከዚህ ዓለም ካጡት እና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ካላቸው ጋር የሚያገናኘን ታላቅ ምሥጢር እንደሆነ አጽንዖት ሰጥተዋል። በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኙት በሙሉ በሕይወት ይኖራሉ፣ ሙሉ ትርጉምንም ያገኛሉ” ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጥብቅ ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፥ በዩክሬን ውስጥ ሰላም ቶሎ እንዲወርድ በጸሎት በመማጸን ንግግራቸውን ደምድመዋል።

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር
ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር   (@Vatican Media)

 

02 Jul 2025, 17:34