MAP

የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነትን ሸሽተው የሚሄዱ ስደተኞች የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነትን ሸሽተው የሚሄዱ ስደተኞች  (ZOHRA BENSEMRA)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ፡- ስደተኞች በተበላሸ ዓለም ውስጥ “የታደሉ የተስፋ ምስክሮች” ናቸው ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለ111ኛው ለዓለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን ዝግጅት ይሆን ዘንድ ባስተላለፉት መልእክት፣ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በግጭት እና በኢ-እኩልነት በተጎዳ ዓለም ውስጥ የተሻለ እና ሰላማዊ የወደፊት መልካም ጊዜን ተስፋ በማድረግ እና በመፈለግ የሚሰጡትን ጠቃሚ ምስክርነት አጽንኦት ሰጥተው በመልእክታቸው ላይ ቅዱስነታቸው አስፍረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በመከራ ውስጥ የተስፋ እና የፅናት ምስክሮች መሆናቸውን በማጉላት ለወደፊት ሰላም እና ለሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር መከበር ጥሪ አቅርበዋል ፣ አርብ ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም በተለቀቀው 111ኛው የዓለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን ዝግጅት ይሆን ዘንድ ባስተላለፉት መልእክት ነበር ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት።

በሚቀጥለው አመት እንደተለመደው በመስከረም 14/2018 ዓ.ም ከሚከበረው የዓለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን ጋር የአለም የስደተኞች እና የተልእኮዎች ኢዮቤልዩ መሳ ለመሳ ሆኖ የሚከበር ሲሆን  ይህም በሚቀጥለው አመት የሚከበረው ይህ አመታዊ ዝግጅት ምእመናን ቤታቸውን እና የትውልድ ቦታቸውን ለቀው ለሚሰደዱ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ እና ቅርበት እንዲያሳዩ ያበረታታል። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ ከሆነ እ.አ.አ. በ2024 ዓ.ም መገባደጃ ላይ 123.4 ሚሊዮን ሰዎች በአለም ዙሪያ በስደት፣ በግጭት፣ በአመጽ ወይም በሌሎች ጉዳዮች ምክንያት በግዳጅ ተፈናቅለዋል።

የሰላም ፍላጎት ለሰው ልጅ አስፈላጊ ነው።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ዓለም “አስፈሪ ሁኔታዎችና ዓለም አቀፋዊ ውድመት ሊያጋጥም እንደሚችል” በማሰመር መልእክታቸውን ጀምረዋል።

"በአዲስ መልክ የተጀመረው የጦር መሳሪያ ውድድር እና የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ጨምሮ አዳዲስ የጦር መሣርያ ትጥቅ ልማት፣ የቀጣይ የአየር ንብረት ቀውስ ለሚያደርሱት ጎጂ ውጤቶች ግምት አለመስጠት፣ እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ እኩልነት አለመመጣጠን የሚያሳድሩት ተጽዕኖ የአሁኑን እና የወደፊቱን ተግዳሮቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ያደርገዋል" ሲሉም አስረድተዋል።

“የተስፋፋው ዝንባሌ የጥቂት ማህበረሰቦችን ጥቅም ብቻ ከግምት ባስገባ መልኩ” የመመልከት አዝማሚያ “የኃላፊነት ፣ የባለብዙ ወገን ትብብር ፣ የጋራ ጥቅምን እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን” የመጋራት ስጋት እንደሚፈጥር ጠቁመዋል ።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ "በሰዎች ልብ ውስጥ ለወደፊቱ ሰላም እና የሁሉንም ሰው ክብር የመጠበቅ ፍላጎት እያደገ መምጣቱ አስፈላጊ ነው" በማለት በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ የዘካርያስን መጽሐፍ ምንባቦችን በመጥቀስ "እንዲህ ያለው የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስፈላጊ ነው" ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል፣ እንደ ክርስቲያን "እኛ እናምናለን፣ እናም ሙሉ በሙሉ እውን እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን፣ ጌታ ሁል ጊዜ ለተስፋ ቃሉ እግዚአብሔር ታማኝ ነው" ብለዋል።

ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ በታሪካቸው የተስፋ ምስክሮች

ስለዚህ የተሻለ የወደፊት ተስፋን ለማሳየት ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ጳጳሱ አስረድተዋል። ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን "የተስፋ በጎነት እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ወንድና ሴት ልብ ውስጥ ላስቀመጠው የደስታ ምኞት ምላሽ ይሰጣል"፣  እናም ይህ ፍለጋ ለስደተኞች፣ ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ለተፈናቀሉ ሰዎች "መልእክተኞች" እና "የተስፋ ምስክሮች" እንዲሆኑ "ከዋናዎቹ ማበረታቻዎች አንዱ" ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን የእስራኤል ሕዝብ ተሞክሮ በማነጻጸር፣ “በእርግጥም፣ ይህንን ዕለት ዕለት የሚያሳዩት በአምላክ ላይ በመታመናቸው ነው፣ የወደፊት ጊዜን ሲፈልጉ መከራ ሲደርስባቸውና ይህም የሰው ልጅ መሠረታዊ ልማትና ደስታ ሊኖር እንደሚችል በጨረፍታ ይገነዘባሉ” ብሏል።

"በጦርነት እና በፍትህ እጦት በጨለመ አለም፣ ሁሉም ነገር የጠፋ ቢመስልም" በማለት አፅንዖት ሰጥው በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ድፍረት እና ጽናት ዓይኖቻችን ማየት ከሚችሉት በላይ ለሚመለከተው እምነት ጀግንነት ይመሰክራሉ፣ እናም በተለያዩ የዘመናችን የስደት መንገዶች ሞትን ለመቋቋም የሚያስችል ጥንካሬ ይሰጣቸዋል ብለዋል።

ስደተኞችን የመቀበል አስፈላጊነት

በተመሳሳይ ጊዜ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን የሚቀበሉ ማህበረሰቦች “የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን መጠን የሚታወቅበት የአሁንና የወደፊት ተስፋ” ስለሚያሳዩ “የተስፋ ሕያው ምስክር” ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጿል።

"በዚህ መንገድ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ወንድሞች እና እህቶች ተሰጥኦአቸውን የሚገልጹበት እና በማህበረሰብ ሕይወት ውስጥ ሙሉ ተሳትፎ የሚያደርጉበት የቤተሰብ አካል እንደሆኑ ይታወቃሉ" ሲሉ ተናግሯል።

የካቶሊክ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቤተክርስቲያንን ማነቃቃት ይችላሉ።

በመንፈሳዊ ደረጃ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳሉት ከሆነ፣ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቤተክርስቲያኗን “በሥነ-መለኮት በጎነት ባለው ተስፋ በመታገዝ ወደ መጨረሻው አገሯ ያለማቋረጥ የምትጓዝበትን መንፈሳዊ ጉዞ መጠን” እንድታስታውስ አጉልተው ገልጸዋል። ቤተክርስቲያኗን እና አባላቶቿን "ወደ ሰማያዊው ሀገር የሚጓዙ የእግዚአብሔር ሰዎች" እንዲሆኑ እና "ከማግለል" ፈተና እንዲርቁ እና ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች "የአለም" አካል እንደሆኑ ማመን ይኖርብናል ብለዋል።  

በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የካቶሊክ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች “በሚቀበሏቸው አገሮች ውስጥ የተስፋ ሚስዮናውያን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ መልእክት ገና ያልደረሰባቸውን አዳዲስ የእምነት መንገዶችን በመቀየስ ወይም በዕለት ተዕለት ሕይወት እና የጋራ እሴቶችን ፍለጋ ላይ የተመሠረተ የሃይማኖቶች ውይይት ለመጀመር ልዩ ተልእኮ እንዳላቸው ቅዱስነታቸው ያምናሉ።

"ይህ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ነው፣ በስደተኞች የሚከናወን ተልዕኮ ነው፣ ለዚህም በቂ ዝግጅት እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በውጤታማ የቤተክርስቲያን ትብብር መረጋገጥ አለበት" ሲሉ ተናግሯል።

“በመንፈሳዊ ጉጉታቸው እና ጉልበታቸው፣ ግትር እና ሸክም የሆኑትን መንፈሳዊ በረሃማነት በሚያስደነግጥ ፍጥነት እየገሰገሰ ያለውን የቤተክርስቲያን ማህበረሰቦችን ለማነቃቃት ይረዳሉ” ብሏል። "እንግዲህ የእነሱ መገኘት እንደ እውነተኛ መለኮታዊ በረከት፣ እራሱን ለእግዚአብሔር ፀጋ ለመክፈት እድል ሆኖ መታወቅ እና አድናቆት ሊሰጠው ይገባል፣ እናም ለቤተክርስቲያኗ አዲስ ጉልበት እና ተስፋ" ይሰጣል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

25 Jul 2025, 16:06