የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የበጋ ወራት ሐዋርያዊ መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ -ቫቲካን
በመጪዎቹ ነሐሴ እና መስከረም ወራት ውስጥ በርካታ ሐዋርያዊ ተግባራት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን ይጠብቃቸዋል። የሊቀ ጳጳሳሱ የስርዓተ አምልኮ ጉዳዮችን የሚመለከተው ጽ/ቤት ሐሙስ ዕለት ሰኔ 26/2017 ዓ.ም የጳጳሱን የስርዓተ አምልኮ ዝግጅቶችን የሚመለከት የቀን መቁጠሪያ አሳትሟል። ከእሁድ ሰኔ 29/2017 ጀምሮ ለእረፍት በሮም ከተማ አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ ካስቴል ጋንዶልፎ እንደሚሄዱ አመላክቷል።
የነሐሴ መርሃግብሮች
የመጀመርያው ዐቢይ ዝግጅት እሁድ ሐምሌ 27/2017 ሲሆን ይህም የወጣቶች ኢዮቤልዩ በጥዋቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ይከበራል። እ.አ.አ በ2000 ዓ.ም በታላቁ ኢዮቤልዩ በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መሪነት ለተካሄደው ታሪካዊ ቅዳሴ የሚታሰበው በሮም ዳርቻ በሚገኘው በቶር ቬርጋታ በሚካሄደው ሥርዓተ ቅዳሴው ይከበራል።
በዕለተ ሐሙስ፣ ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የፍልሰታ ማርያም አመታዊ በአል የሚከበር ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የቪላኖቫ ጳጳሳዊ የቅዱስ ቶማስ ቁምስና ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ ይጠበቃል፣ በእዚያም የፍልሰታ ማርያም አመታዊ በዓል ይከበራል።
የመጪው የመስከረም ወር በዓላት
እሑድ ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ቅዱስ አባታችን ለብፁዕ ፒየር ጆርጂዮ ፍሬሳቲ እና ብፁዕ ካርሎ አኩቲስ ሲመተ ቅድስና ላይ የሚከናወነውን መስዋዕተ ቅዳሴ ይመራሉ። ከአንድ ሳምንት በኋላ፣ እሑድ፣ መስከረም 04/2018 ዓ.ም ከሰአት በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የአዳዲስ ሰማዕታት እና የእምነት ምስክሮች መታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ የሚከናወነውን መስዋዕተ ቅዳሴ ይመራሉ።
በወሩ በጳጳሱ ህዝባዊ መርሃ ግብር ላይ የመጨረሻው የስርዓተ አምልኮ ዝግጅት እሁድ መስከረም 18/2017 ዓ.ም በጠዋቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የሚከበረው የካቴኪስቶች ኢዮቤልዩ ቅዳሴ ለዚህ ለበጋው ወር ለቅዱስነታቸው የወጣው የሐዋርያዊ ተግባር መርሃግብር ይደመደማል።