MAP

ር.ሊ.ጳ ሊዮ አሥራ አራተኛ የአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንትን ከሆኑት አቶ አብደልማጅድ ቴቡን በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ሊዮ አሥራ አራተኛ የአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንትን ከሆኑት አቶ አብደልማጅድ ቴቡን በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ አሥራ አራተኛ የአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንትን በቫቲካን ተቀብለው አነጋገሩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ አብደልማጅድ ቴቡን በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን በመቀጠልም የአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ አብደልማጅድ የቅድስት መንበር ዋና ጸኃፊ ከሆኑት ከካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አቶ አብደልማጂድ ቴቦን ሐሙስ ማለዳ ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም በቫቲካን ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፣ ስለግንኙነቱ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ፕሬዝዳንቱ በመቀጠል የቅድስት መንበር ዋና ጸኃፊ ከሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊንን ጨምሮ፣ ቫቲካን ከተለያዩ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት የሚመለከተው ዋና ጽ/ቤት ምክትል ፀሃፊ የእኔታ አባ ዳንኤል ፓኮ ጋር ተገናኝተዋል፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መመካከራቸው ተገልጿል።

መግለጫው በቅድስት መንበር እና በአልጄሪያ ሪፐብሊክ መካከል ያለው መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የቫቲካን ዋነ ጸኃፊ ከሆኑት ከካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር በተካሄደው መልካም ውይይት ላይ ተስተውሏል ።

"በአገሪቱ ውስጥ ያሉ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ ሕይወት ገጽታዎች በመልካም ሁኔታ ቀጥለዋል እንዲሁም ተስተካክለዋል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

በመጨረሻም መግለጫው አሁን ያለውን ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታን በማጣቀስ በሀይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርገው ውይይት እና የባህል ትብብር ለአለም ሰላምና ወንድማማችነት ያለውን ጠቀሜታ በመጥቀስ መወያየታቸውንም መግለጫው አክሎ ገልጿል።

 

 

25 Jul 2025, 16:04