ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ገዳማውያት እግዚአብሔርን ሁለንተናቸው እንዲያደርጉት አሳሰቡ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ቅዱስ አጎስጢኖስ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ቀዳሚነት ሲገልጽ፥ “እግዚአብሔር ሁለመናችን ነው፤ ስንራብ እንጀራችን፤ ስንጠማ ውሃችን፤ ጨለማ ውስጥ ስንሆን የማይጠፋ ብርሃናችን፤ ስንታረዝ የዘላለም ልብሳችን ነው” ማለቱን ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ እነዚህ ቃላት ምን ያህል እውነት ናቸው? እግዚአብሔር የሕይወት፣ የፍቅር እና የብርሃን ፍላጎቴን ምን ያህል ያረካል?” ብሎ ራስን መጠየቅ መልካም እንደሆነ ተናግረዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ይህንን ምልከታ በቫቲካን ለተቀበሏቸው የመለኮታዊ በጎ አድራጎት ሥራ ማኅበር እህቶች፣ ለታላቁ ቅዱስ ባዚሊዮ ገዳም እህቶች፣ በአምፓሮ የቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበር እህቶች እና ለቅዱስ ልበ ኢየሱስ ፍራንችስካውያን እህቶች ያቀረቡት ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ. ም. እንደ ነበር ታውቋል።
ኢየሱስን&Բ;መሠረትማድረʵ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለገዳማውያቱ ባደረጉት ንግግር፥ “መሠረታቸውን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጉ፣ እንደ እኛ ልዩ ልዩ ስጦታዎች እና ውስንነቶች ያሏቸው ከእኛ በፊት የኖሩ ወንዶች እና ሴቶች ይህን ለማድረግ እንደሚችሉ ያላሰቡ ነገር ግን ያሳኩ ናቸው” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በተጨማሪም፥ “ኢየሱስ ክርስቶስን መሠረት ማድረጋቸው በዘመናት ውስጥ በአኅጉራት በሙሉ ጸንተው መቆየታቸው እና እዚህ መገኘታችሁ እንደሚያሳየው ሁሉ ዛሬ በተግባር ወደ ዓለም ሁሉ የደረሰውን መልካም ዘር እንዲዘሩ አስችሏቸዋል” ብለዋል።
በቅድስና መንፈስ መነሳሳት
ወደ ሮም ከመጡት መነኮሳት መካከል አንዳንዶች ለጠቅላላ ጉባኤያቸው ሌሎች ደግሞ የኢዮቤልዩ በዓል ለማክበር መንፈሳዊ ንግደት ማድረጋቸውን ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በሁለቱም ረገድ ከእግዚ አብሔር ጋር ያላቸውን ፍቅር እና ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ታማኝነት ለማደስ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ መካነ መቃብር መምጣታቸውን አስታውሰዋል።
የገዳማውያቱ ማኅበራት በተለያዩ ጊዜያት እና ሁኔታዎች ውስጥ መመሥረታቸውን የገለጹት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ታሪካቸው እንደ ቅዱስ አጎስጢኖስ፣ እንደ ቅዱስ ባዚሊዮስ እና እንደ ቅዱስ ፍራንችስኮስ ካሉ ታላላቅ የታሪክ ምስክሮች አንፃር ሊታይ የሚችል እና የጋራ ጉዞን የሚካፈል ሲሆን፥ እነዚህ የማኅበራችሁ መሥራቾች ሌሎችን የማገልገል ስልቶችን እንዲያሳድጉ ያነሳሳቸው ድፍረታቸው እና የሕይወት ቅድስናቸው ነው” ብለዋል።
“ይህም ሕፃናትን፣ ድሃ ልጃገረዶችን እና ወንዶች ልጆችን፣ ወላጅ አልባ ሕፃናትን፣ ስደተኞችን እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአረጋውያን እና ለሕሙማን እንዲሁም በሌሎች የበጎ አድራጎት ሥራዎች አማካይነት በሚያደርጉት እንክብካቤ በግልጽ ይታያል” ብለዋል።
አስፈላጊ ምርጫዎችን ፊት ለፊት መጋፈጥ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ንግግራቸውን በመቀጠል፥ “ላለፉት ተግዳሮቶች የሰጡት ምላሽ እና አሁን ላለው ሕይወት ጠቃሚነት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ራሳቸውን በመስጠት አዲስ መንገዶችን ለሚጓዙ፣ እግዚአብሔርን እና ባልንጀራን ለመውደድ ለማገልገል የወሰኑ እና የዘመኑን ምልክቶች በትኩረት በመመልከት ለጥንታዊው የወንጌል ጥበብ ታማኝ መሆን ከሁሉ የተሻለው መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት የገዳማውያቱን ኃላፊነት ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ገዳማውያቱ የራሳቸውን፣ የእህቶቻቸውን እና የቤተ ክርስቲያኒቱን የወደፊት ሕይወት ከሚወስኑ ጠቃሚ ምርጫዎች ጋር ፊት ለፊት መገናኘታቸውን ተናግረው፥ በዚህም ምክንያት ሁላችንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች የተናገረውን መልካም ተስፋ በድጋሚ መልክቱ ተገቢ ይሆናል ብለዋል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ክርስቲያኖች በላከው መልዕክቱ በምዕ. 3:17 ላይ፥ “ሥር ሰዳችሁ፣ በፍቅርም ታንጻችሁ ክርስቶስ በልባችሁ በእምነት እንዲኖር” ያለውን በማስታወስ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱ እና ርዝመቱ፣ ከፍታው እና ጥልቅነቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፣ ከእውቀትም በላይ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ በእግዚአብሔር ጥበብ ትሞሉ ዘንድ እጸልያለሁ” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በመጨረሻም፥ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከመስጠታቸው በፊት ገዳማውያቱን በሙሉ ለመልካም ሥራዎቻቸው እና ለታማኝነታቸው በማመስገን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አብራቸው እንድትጓዝ ጸሎታቸውን አቅርበዋል።