ር.ሊ.ጳ. ሊዮ በራችንን የሚያንኳኳውን ጌታ እንኳን ደህና መጣህ ብለን ልንቀበል ይገባል አሉ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ/ቫቲካን
በወቅቱ እለተ ሰንበት ሥርዓተ አምልኮ ላይ በተነበቡ ምንባባት ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ በአብርሃምና በሚስቱ ሣራ እንደተገለፀው፣ የእንግዳ ተቀባይነትን መሪ ቃል የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን ንባቦችን በማስታወስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የመስጠትና የእንግዳ ተቀባይነትን መስተንግዶ አቀላጥፈን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ!
የአብርሃም እና የሚስቱ የሳራ፣ ከእዚያን በመቀጠል የኢየሱስ ወዳጆች የሆኑት እህተማማቾቹ ማርታ እና ማርያም ለኢየሱስ ያደረጉትን መስተንግዶ የተመለከቱ ታሪኮች በዛሬው ሥራዓተ አምልኮ ላይ የተነበቡት ንባባት ትኩረት ነበረ (ዘፍ. 18፡1-10፤ ሉቃ. 10፡38-42)። የጌታን እራት ግብዣ ስንቀበል እና በቅዱስ ቁርባን ማዕድ በተሳተፍን ቁጥር፣ “ለማገልገል የሚመጣው እግዚአብሔር ራሱ ነው” (ሉቃስ 12፡37)። ሆኖም፣ አምላካችን በመጀመሪያ እንግዳ መሆንን ያውቅ ነበር፣ እናም ዛሬም በደጃችን ቆሞ ያንኳኳል (ራዕ. 3፡20)። በጣልያንኛ ቋንቋ እንግዳው የሚያስተናግደውም ሆነ የሚስተናገደው ሰው እንደሆነ ይጠቁማል። ስለዚህ በዚህ ዕለተ ሰንበት ሕይወታችን ድህነት ውስጥ የሚወድቅበትን የጋራ ተቀባይነት ጨዋታን ማሰላሰል እንችላለን። ለማስተናገድም ሆነ ለመስተናገድ ትህትናን ይጠይቃል። መስዕብ፣ ትኩረት እና ግልጽነት ያስፈልጋል። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ማርታ ወደዚህ ሰጥቶ ወደ መቀበል ደስታ ሙሉ በሙሉ እንዳትገባ ስጋት አለኝ። ኢየሱስን ለመቀበል ምን ማድረግ እንዳለባት በጣም በማሰብ ስለተጨነቀች የማይረሳውን የግንኙን ጊዜ ልታበላሽ ትችላለች። ማርታ ለጋስ ነች፣ ነገር ግን ከልግስና ይልቅ ወደ ሚያምር ነገር እግዚአብሔር ጠራት። ከራሷ እንድትወጣ ይጠራታል።
ውድ እህቶቼ እና ወንድሞቼ፣ ይህ ብቻ ነው ህይወታችንን እንዲያብብ የምያደርገው፣ ራሳችንን ከራሳችን የሚያዘናጋን እና በተመሳሳይ ጊዜ ለሚሞላን ነገር ራሳችንን መክፈት አለብን። ማርታ እህቷን ብቻዋን እንግዳውን እንድታስተናግድ እንደተወቻት በመጥቀስ ስታማርር (ሉቃስ 10፡40 )፣ ማርያም በኢየሱስ ቃላቶች ተሸንፋ ጊዜዋን ያጣች ይመስላል። እሷ የሚታስብ ተጨባጭ ነገር ወይም ከእህቷ ያነሳ ልግስና የነበራት ሴት አይደለችም። ለዚህም ነው ኢየሱስ ማርታን የገሰጸው፡ ምክንያቱም እሷም ታላቅ ደስታን ከሚያመጣላት ግንኙነት ውጭ ቆይታለች (ሉቃስ 10፡ 41-42 ይመልከቱ)።
የበጋው የአየር ሁኔታ (የአውሮፓዊያኑን የበጋ ወቅት ማለት ነው) ከማርታ ይልቅ “ፍጥነት እንድንቀንስ” እና እንደ ማርያም እንድንሆን ይረዳናል። አንዳንድ ጊዜ ለራሳችን የተሻለውን ክፍል አንሰጥም። ስለ እንግዳ መስተንግዶ ጥበብ የበለጠ ለመማር ፍላጎት ለማሳየት የተወሰነ እረፍት ማግኘት አለብን። በዚህ በእረፍት ጊዜ ኢንዱስትሪው ሁሉንም ዓይነት ልምዶች እና ሸቀጦች ሊሸጥልን ይፈልጋል፣ ነገር ግን ምናልባት ይህ ለእኛ የምያስፈልግ ነገር አይደለም። ነፃ ነው፣ በእውነቱ፣ እና እያንዳንዱ እውነተኛ ገጠመኝ ሊገዛ አይችልም፡ ከእግዚአብሔር፣ ከሌሎች ጋር፣ ወይም ከተፈጥሮ ጋር። እኛ በቀላሉ እንግዶች መሆን አለብን፣ ለእርሱ ቦታ በመስጠት እና ደጋግመን እሱን በመጠየቅ፣ እርሱን ለመቀበል እና እርሱ እንዲቀበለን ቦታ በመስጠት ልናሳልፈው የሚገባን ጊዜ ነው። ለመስጠት ብቻ ሳይሆን የምንቀበለው ብዙ ነገር አለ። አብርሃም እና ሳራ ምንም እንኳን አረጋውያን ቢሆኑም፣ ጌታን በሦስት መንገደኞች በእርጋታ ሲቀበሉት ፍሬያማነታቸውን አወቁ። ለእኛም ገና የምንቀበለው ብዙ ሕይወት አለ።
ጌታን በማህፀኗ ተቀብላ ከዮሴፍ ጋር መኖሪያ ቤት የሰጠችውን፣ እንግዳ ተቀባይ እናት ወደ ሆነችው ወደ ቅድስተ ማርያም እንልይ። በእሷ ውስጥ፣ ጥሪያችን ይበራል፣ የቤተክርስቲያን ጥሪ ለሁሉም ክፍት የሆነች ቤት እንድትሆን፣ ለመግባት ፍቃድ የሚጠይቀውን ጌታዋን መቀበል ለመቀጠል ነውና በዚህ ረገድ እርሷ በአማላጅነቷ ትርዳን።