MAP

ካስቴል ጋንዶልፎ ካስቴል ጋንዶልፎ  (©Buesi - stock.adobe.com)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከበጋ የዕረፍት ጊዜያቸው በፊት ካስቴል ጋንዶልፎን እንደ ጎበኙ ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በሮም አቅራቢያ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ ከተማ አጭር ጉብኝት በማድረግ በጳጳሱ መኖሪያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ጎብኝተዋል፣ ከእሑድ ሰኔ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ የበጋ የዕረፍት ጊዜያቸውን በእዚያው ስፍራ እንደ ምያሳልፉም ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ሐሙስ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም ከዓአት በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ በካስቴል ጋንዶልፎ ውስጥ በቦርጎ ላውዳቶ ሲ ("ላውዳቶ ሲ' መንደር") ውስጥ የሚገኘውን ቪላ ባርቤሪኒን ጎብኝተዋል፣ በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ / ቤት እንደተረጋገጠው በሂደት ላይ ያሉ ሥራዎችን ገምግመዋል።

ከእሑድ ሰኔ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሮም ከተማ 25 ኪሎ ሜትር (16 ማይል አካባቢ) ርቃ ወደምትገኘው ከተማ ለእረፍት እንደ ሚሄዱ የተገለጸ ሲሆን እስከ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም ድረስ በእዚያው ሥፍራ በመቆየት እረፍ እንደምያደርጉ ተገልጿል።

በነዚያ 14 ቀናት ውስጥ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እሁድ ቀን ሐምሌ 06/2017 ዓ.ም በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በቪላኖቫ ጳጳሳዊ የቅዱስ ቶማስ ቁምስና አመታዊ በዓል እንደምያከብሩ ይጠበቃል። በእለቱ በሮም የሰዓት አቆጣጠር እኩለ ቀን ላይ ከሐዋርያው ​​መንበራቸው ፊት ለፊት በሚገኘው የነጻነት አደባባይ የመልአከ ሰላም ጸሎትን እንደምያቀርቡ ይጠበቃል።

እሑድ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 9፡30 ላይ በአልባኖ ካቴድራል በድጋሚ መስዋዕተ ቅዳሴን እንደምያሳርጉ ይጠበቃል። የወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሆነው ከመመረጣቸው በፊት ካርዲናል ሮበርት ፕሬቮስት የአልባኖ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ።

በዚያው ቀን፣ ከቀኑ እኩለ ቀን ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በነጻነት አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ይመራሉ፣ ከዚያም ከሰዓት በኋላ ወደ ቫቲካን ይመለሳሉ።

ከሰኔ 29 እስከ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም ድረስ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር የሚደረጉ የግል ሆነ የቡድን ስብሰባዎች እንደ ማይኖሩ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ዘወትር ረቡዕ እለት የሚያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በዚህ የእረፍት ጊዜ ውስጥ እንደማይካሄዱ ተገልጿል።  የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከረቡዕ ሐምሌ 23/2017 ጀምሮ እንደ ሚካሄድ ከወጣው የተግባር መርሃግብር ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናትም የወጣቶች ኢዮቤልዩ ከሐምሌ 21/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም በዚህ ስነ-ስረዓት ላይ የገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

04 Jul 2025, 15:45