MAP

2024.06.05 ambiente - laudato si - casa comune - brasile

ር.ሊ.ጳ ሊዮ እግዚአብሔር ምድራችንን የፈጠረው የጦር አውድማ እንድትሆን አይደለም ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለ10ኛው የዓለም የፍጥረት እንክብካቤ የጸሎት ቀን ባስተላለፉት መልእክት በላቲን ቋንቋ "ላውዳቶ ሲ" (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) ከሚለው ከቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጳጳሳዊ መልእክት በመጥቀስ በተፈጥሮ ላይ የሚደርሰው ውድመት እና ማኅበራዊ ኢፍትሐዊነትን በማውገዝ የእግዚአብሔር ፍጥረት ወሳኝ የሆኑ ሀብቶችን ለማግኘት ያለመ የጦርነት አውድማ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቤተክርስቲያን እ.አ.አ በመስከረም 1-2025 አሥረኛውን የዓለም የፍጥረት እንክብካቤ የጸሎት ቀንን ለማክበር ስትዘጋጅ፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለበዓሉ ዝግጅት ይሆን ዘንድ ያስተላለፉት መልእክት ክርስቲያኖች እና ሁሉም በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ፣ ግጭት እና ኢኩልነት እየጨመረ ባለበት ዓለም አስቸኳይ የአካባቢ እና ማህበራዊ ፍትህ አስፈላጊነትን እንዲገነዘቡ አሳስበዋል።

የሰላም እና የተስፋ ዘሮች በሚል ርዕስ በሰኔ 25/2017 ዓ.ም የተለቀቀው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክት በመካሄድ ላይ ባለው የኢዮቤልዩ ዓመት መንፈስ ያስተጋባል።

ፍትህ በቆሰለ አለም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የኢሳይያስን ትንቢታዊ ቃላት በማስተጋባት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በዛሬው ጊዜ ያለው “ደረቃማና ምድረ በዳ” ምድራችን ወደ “ፍሬያማ እርሻ” እንደሚለወጥ እንዲያስብ ጋብዘዋል። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ራዕይ፣ የግጥም ዘይቤ ሳይሆን፣ አስደንጋጭ የስነ-ምህዳር እና የሰው ልጅ ቀውሶች ሲያጋጥም አስቸኳይ የድርጊት ጥሪ እንደሆነ ያስረዳል።

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ "ላውዳቶ ሲ" (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) የተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት የተጻፈበትን 10ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ በስፋት የጠቀሰውን “ኢፍትሃዊነት፣ የአለም አቀፍ ህግጋት እና የህዝቦች መብት መጣስ፣ ከፍተኛ የሆነ የእኩልነት መጓደል እና እነሱን የሚያራምደው ስግብግብነት የደን ጭፍጨፋ፣ ብክለት እና የብዝሀ ህይወት መጥፋት እያስከተለ ነው” ሲሉ መጻፋቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የአካባቢ ውድመትን ከድሆች እና የተገለሉ ሰዎች መጠቀሚያ ከመሆናቸው ጋር በማያያዝ፣ በአገሬው ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ያልተመጣጠነ ስቃይ እና በሀብታሞች እና በድሆች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱ ተፈጥሮን እንደ የጋራ መኖሪያ ቤት ሳይሆን እንደ ሸቀጥ የሚመለከት ስርዓት መገለጫዎች መሆናቸውን አጉልተው በመልእክታቸው አሳይተዋል።  

አከባቢያችን እንደ ጦር ሜዳ

ተፈጥሮ ራሷ ከሰዎች እና ከፕላኔቷ ይልቅ ትርፍን በሚያስቀድሙ ፖሊሲዎች እና አሰራሮች ተገዝታ “እየተቆራረጠች የመደራደርያ አካል” ሆናለች በማለት በቁጭት ተናግሯል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በተቀበሩ ፈንጂዎች፣ ከተጨፈጨፉ የእርሻ መሬቶች ጀምሮ በውሃና በጥሬ ዕቃ ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶች ለቁጥጥርና ለገዢነት “ወደ ጦርነት አውድማነት ተቀይረዋል” የሚለውን ተፈጥሮን የሚያሳዝን ሥዕል ይስላሉ ብለዋል።

እነዚህ ቁስሎች፣ “የኃጢአት ውጤት” ናቸው፣ ፍጥረትን መንከባከብ ግድ ነው የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እና ትእዛዝ ይቃረናሉ፣ ነገር ግን “መጠቀም እና መንከባከብ”፣ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በመጠቀም ምድርን በእንክብካቤ እና በሃላፊነት ግንኙነት የመንከባከብ ጥሪ ነው ብለዋል።

የአካባቢ ፍትህ እንደ ሥነ ምግባራዊ አስፈላጊነት

የጳጳሱ መልእክት የቤተክርስቲያኗን ቁርጠኝነት በመጥቀስ "ለተዋሃደ ስነ-ምህዳር" ማለትም በላውዳቶ ሲ' ፅንሰ-ሀሳብ ይረጋገጣል። የአካባቢ ፍትህ፣ ቅዱስ አባታችን ያረጋግጣሉ፣ ረቂቅ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ጉዳይ ሳይሆን “ከእምነት የተወለደ ግዴታ” ነው ብለዋል።

“ለአማኞች፣ አጽናፈ ዓለም የሚያንጸባርቀው የኢየሱስ ክርስቶስን መልክ ነው፤ በእርሱም ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩበትና የተዋጁበት” ነው ሲሉ ቅዱስነታቸው ጽፈዋል። በዚህ ብርሃን ፕላኔቷን መንከባከብ ሥነ-ምህዳራዊ አስፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ መንፈሳዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጥሪም ይሆናል ብለዋል።

ፍሬ የሚያፈሩ ዘሮች

ተጨባጭ ተግባርን የሚያበረታቱ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳሉት ከሆነ ከጊዜ በኋላ የሰላምን ፍሬ የሚያፈሩ “የፍትህ ዘሮችን” የመዝራት ጽናትና ፍቅርን ጠይቀዋል። በትምህርት እና በሥነ-ምህዳር እሴቶች ላይ የተመሰረተው የማህበረሰብ ህይወት እንዴት ፍትሃዊ እና ተስፋ ሰጭ የወደፊት ሁኔታን እንደሚፈጥር የሚያሳይ ተጨባጭ ምሳሌ በካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኘውን የቦርጎ ላውዳቶ ሲ ፕሮጄክትን በዋቢነት ጠቅሷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ይህ ዓመታት ሊወስድ ይችላል፣ ነገር ግን ቀጣይነት፣ ታማኝነት፣ ትብብር እና ፍቅርን ያካተተ አጠቃላይ ሥነ-ምህዳርን የሚያካትቱ ዓመታት ናቸው” ብለዋል።

የመጪው ጊዜ ቡራኬ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲፈስ በፀሎት መልእክታቸውን ሲያጠቃልሉ ከሙታን የተነሳው የክርስቶስን ተስፋ ፈውስን ለሚናፍቀው ዓለም መሪ ብርሃን ይሆን ዘንድ ተማጽነዋል።

“[ላውዳቶ ሲ] እኛን ማበረታታቱን ይቀጥል፣ እና ወሳኙ ሥነ-ምህዳር ለመከተል ትክክለኛው መንገድ ይበልጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይረዳን” ሲሉ ጽፈዋል።

 

03 Jul 2025, 16:10