ር.ሊ.ጳ ሊዩ እንግዳ ተቀባይነት፣ አገልግሎት እና ማዳመጥ ከእግዚአብሔር ጋር እንድንገናኝ ይረዱናል አሉ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የጳጳሱ የበጋ መኖሪያ ሥፍራ ለሦስት ተከታታይ እለተ ሰንበት ቅዱስነታቸው በተለመደው ሰዓት በአቅራቢያው በሚገኘው የአልባኖ ካቴድራል ሥርዓተ ቅዳሴ መርተዋል።
ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ስብከት መጀመሪያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "አሁንም እዚህ በመሆኔ በእውነት ደስተኛ ነኝ፣ እናም በዚህ የወንድማማችነት እና የክርስቲያናዊ ደስታ ስሜት ለተገኙት ሁሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ" በማለት መልእክታቸውን መጀመራቸው ተገልጿል፣ በመጀመሪያው ንባብ እና በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ በማሰላሰል፣ እነዚህ መልእክቶች በእንግዳ ተቀባይነት፣ አገልግሎት እና ማዳመጥ ላይ እንድናሰላስል ይጠሩናል ብሏል።
ጥሩ አስተናጋጆች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመጀመሪያ ከዘፍጥረት መጽሐፍ ተወስዶ በተነበበው የመጀመሪያውን ንባብ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ሦስት ሰዎች አብርሃምን "በቀን ሙቀት" የጎበኙበትን ሁኔታ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የገለጹ ሲሆን አብርሃም ለእነዚህ ጎብኚዎች እንደ ቤቱ ዋና ጌታ የሰጠው ምላሽ እንዴት እንግዳ ተቀባይ እንደሆነ እንደምያሳይ ጠቁመዋል።
በዚህ አመለካከት እና ድባቡ ተለውጧል “የከሰዓት በኋላ ፀጥታ በአብርሃም፣ በሚስቱ በሳራ እና በአገልጋዮቻቸው በፍቅር ምልክቶች ተሞላ። በዚያ መቼት ውስጥ፣ ጥንዶቹ ሲጠብቁት የነበረውን ዜና እግዚአብሔር ያበስራቸዋል፣ ወንድ ልጅ እንድሚወልዱ ያበስራቸዋል" ሲሉ ቅዱስነታቸው የተናገሩ ሲሆን ይህ ገጠመኝ እግዚአብሔር ወደ አብርሃም እና ወደ ሣራ ሕይወት ለመግባት የእንግዳ ተቀባይነት መንገድን እንዴት እንደመረጠ እንድናስብ ያበረታታናል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
የእንግዳ ተቀባይነት መንታ ልኬቶች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ወደ እለቱ ቅዱስ ወንጌል ሐሳባቸውን ዘወር አድርገው እንደ ተናገሩት ከሆነ “ስለ አምላክ ድርጊት እንዴት እንደ ምያስተምረን ለመረዳት እንችላለን" በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ኢየሱስ በማርታና በማርያም ቤት እንግዳ ሆኖ ሳይሆን እንደ ጓደኛ በበዓል ጊዜ መጣ ሲሉም አክለው ገልጸዋል።
ሁለቱ እህተማማቾች ለእንግዳቸው በተለያየ መንገድ ምላሽ ሰጡ፤ ማርታ በማገልገል ተቀበለችው፤ ማርያም ግን እሱን ለመስማት እግሩ ሥር ተቀምጣለች። ኢየሱስ የማርታን ሐሳብ ማዳመጥ ያለውን ጥቅም እንድትገነዘብ በመጋበዝ ምላሽ ሰጥቷታል። ሆኖም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እነዚህ ሁለት አመለካከቶች እርስ በርሳቸው የሚጋጩ እንደሆኑ አድርጎ መመልከቱ ወይም የሁለቱን ሴቶች ጥቅም ማነጻጸር ትክክል አይደለም” ሲሉ አጽንዖት ሰጥው የተናገሩ ሲሆን አገልግሎት እና ማዳመጥ “የእንግዳ ተቀባይነት መንታ ገጽታዎች” ናቸው ብሏል።
በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እነዚህን ሁለት ገጽታዎች ለመኖር ስንጥር፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት መቅደም አለበት፥ በሕይወታችን ሁኔታ መሠረት በተጨባጭ ተግባራት እምነታችንን መምራት አለብን። ይህን ማድረግ የምንችለው ግን የእግዚአብሔርን ቃል ካሰላስልንና መንፈስ ቅዱስን ከሰማን በኋላ ነው። ይህንን ለማድረግ ጳጳሱ እንዳሉት ከሆነ የዝምታ እና የጸሎት ጊዜዎችን እንድንወስን፣ ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን እንድናስወግድ የመከሩ ሲሆን በዚህ መልኩ በእግዚአብሔር ላይ እንድናተኩር እና እንዲያናግረን ቦታ እንሰጠዋለን ሲሉ የዝምታ እና የጸሎት ጊዜዎች በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ቅዱስነታቸው አስምረውበታል።
“ይህ ለግለሰቦች እና ለማህበረሰቦች እሴት እና ለዘመናችን ትንቢታዊ ምልክት ሆኖ ዛሬ በውስጣች ሊያገግም የሚገባው የክርስትና ሕይወት ገጽታ ነው” በማለት በአጽኖት ተናግረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በበጋው ወቅት በዚህ መንገድ ለመግፋት እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ውበት ለመለማመድ እና ለሌሎች የበለጠ ክፍት እንድንሆን የሚረዳን ጥሩ ጊዜ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የበጋ ዕረፍት እና እግዚአብሔር
የበጋ ወር ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ጋር ጊዜ አግኝተን እንድንወያይ እና በጋራ ለማሳለፍ የበለጠ ነፃ ጊዜ የሚሰጥ እንደመሆኑ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሁሉም ሰው “ለጥቂት ጊዜያት የሰላም እና የማሰላሰል ጊዜን ለማጣጣም አስጨናቂ የሆነ የሥራ ጊዜን እና የጭንቀቶችን አውሎ ንፋስ በመተው ይህንን በጥሩ ሁኔታ እንዲጠቀሙበት” እና ሌሎችን እንዲጎበኙ ጠይቀዋል።
የበጋ ወቅት (በአሁኑ ወቅት መላው አውሮፓ የበጋ እና የእረፍት ወቅት ላይ ይገኛል) ሌሎችን ለመንከባከብ፣ ለመተዋወቅ እና ለማዳመጥ እድል ሊሰጥ ይችላል። እነዚህ ሁሉ የፍቅር መግለጫዎች ናቸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለው እንደገለጹት ከሆነ ሁላችንም የምንፈልገው ወቅት ነው፣ እነዚህን በድፍረት ለመኖር የምንሞክር ከሆነ “በአካባቢያችን ያሉትን መከፋፈልንና ጥላቻን እንዲያሸንፉ እንዲሁም በግለሰብ፣ በሕዝቦችና በሃይማኖቶች መካከል መግባባት እንዲፈጠር በመርዳት የሰላም ባህልን እናስፋፋለን” ሲሉ አብራርተዋል።
ይህ ጥረትና መስዋዕትነት የሚጠይቅ መሆኑን የተገነዘቡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በእነዚህ ጥረቶች ውስጥ “በሕይወት ውስጥ ጠቃሚ ነገር መገንባት ይቻላል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው በስብከታቸው የተናገሩ ሲሆን ሌሎችን ማዳመጥ እና ማገልገል ከሌሎች ጋር እውነተኛ ግንኙነት ለመፍጠር እና ለማጠናከር ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።