MAP

ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ቪላ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ቪላ  (AFP or licensors)

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስተሳሰብ መሰረት አመታዊ እረፍቶን እንዴት ማሳለፍ እንደሚገባ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሰኔ 29/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም ደረስ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ቪላዎች በሚገኙበት ሥፍራ የተወሰነ ጊዜን ሲያሳልፉ የቫቲካን ዜና ያለፉት ሊቃነ ጳጳሳት ስለ አመታዊ እረፍት የተናገሩትን ሐሳብ እንደሚከተለው አጠናቅሯል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከሥራ ገበታ ተላቀን እረፍት ማድረግ አካላዊ ጥንካሬን መልሰን ለመጎናጸፍ፣ ወደፊት ለመጓዝ እና የተፈጥሮን ውበት ለማሰላሰል እድል የሚፈጥር ሲሆን በተጨማሪም ለንባብ እና አዲስ ጓደኛ ለማፍራት ወይም ለማሰላሰል እና ለመጸለይ እንደሚጠቅም የሚታወቅ ሲሆን እነዚህ ቀደምት ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት የዕረፍት ጊዜን አስፈላጊነት ሲያስቡ አጽንዖት ሰጥተው የተናገሯቸው ንግግሮች ናቸው።

በዚህ የአውሮፓዊያኑ የበጋ ወር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጠ በኋላ የመጀመሪያውን የበጋ እረፍታቸውን ለማድረግ የወሰኑት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛም ለማረፍ የተወሰነ ጊዜ እንደምያስፈልጋቸው ተገንዘበው በአሁኑ ወቅት በእረፍት ላይ ይገኛሉ። ከሰኔ 29/2017 እስከ ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም ደረስ ከዚያም በነሐሴ ወር ላይ ለተወሰኑ ቀናት፣ ከሮም 25 ኪሎ ሜትር (በግምት 16 ማይል) ርቃ በምትገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው ጳጳሳዊ ቪላዎች ውስጥ አሁን ይገኛሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በነሐሴ ወር አጋማሽ፣ ቅዳሜና እሁድ በሮም አቅራቢያ በሚገኘው ካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የጳጳስ መኖሪያ ውስጥ የእሁድ ቅዳሴ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በማክበር እና የመልአከ ሰላም ጸሎት እንደምያደርጉ ከወጣው የድርጊት መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

ምቹ ጊዜ

አንድ ሰው የእረፍት ጊዜውን በአግባቡ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በብዙ የጳጳሳት ንግግሮች ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ጥያቄ ነው፣ ምክንያቱም አመታዊ እረፍት በሰው ሕይወት ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው።

ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ ጊዜ እንደ ሥራ ፈትነት ብቻ መታየት እንደሌለበት አሳስበዋል። ለምሳሌ፣ የእረፍት ጊዜያት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስድስተኛ እንደተገለፀው የተፈጥሮን ውበት ወይም “የእግዚአብሔር መጽሐፍ” ብለው የጠሩትን ተፈጥሮን ቆም ብሎ ለመመልከት፣ ለማንበብ እና ለማሰላሰል እድል ሊሆን ይችላል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

በእረፍት ጊዜ ወይም ወቅት "ሁልጊዜ ክፍት፣ ሁልጊዜ አዲስ፣ ሁልጊዜ የሚያምር" ፍጥረትን እንደገና ማግኘት እንደምንችል አመልክተዋል። ተፈጥሮ “ጠፈር፣ ከባቢ አየር፣ እንስሳት፣ ባህር፣ ተራራዎች፣ ሜዳዎች፣ ሰማዩ ጎህ ሲቀድ፣ ቀትር ላይ፣ ጀንበር ስትጠልቅ እና በተለይም በከዋክብት የተሞሉ ምሽቶች” ያሉት ተፈጥሮ “ሁልጊዜ ጥልቅ እና ማራኪ ነው ሲሉ ገልጸው ነበር።

ለሊቃነ ጳጳሳት አመታዊ እረፍት የመዝናናት ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ለማሰላሰል እና ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ጭምር እድሉን የምናገኝበት ወቅት ጭምር ነው ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ፡ አመታዊ እረፍት ለማንበብ፣ አዲስ ነገር ለማግኘት እና አዲስ ጓደኝነት ለመፍጠር ወሳኝ ጊዜ ነው በማለት ተናግረው ነበር።

"የእረፍት ጊዜያት እንዲሁ ፍሬያማ ጊዜያት ናቸው፣ ምክንያቱም የተለመደው የስራ ሂደት መቋረጥ ውስጣዊ ጸጥታን እና ትውስታን ያመጣል" በማለት እ.አ.አ በነሐሴ 5/1973 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ የተናገሩ ሲሆን “ይህ የዕረፍት ጊዜ የምንለው ለዕረፍት ወይም ለራስ ወዳድነት ብቻ የሚውል እንዳልሆነ እናረጋግጥ" ሲሉ አክለው ተናግረው ነበር። መዝናናት እና ማረፍ ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም አስተዋይ እና ንቁ እንድንሆን ያደርገናል ማለታቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ለምሳሌ፣ በዓመቱ ውስጥ ወደ ጎን የተተውትን “ከባድ ንባቦችን” ለመከታተል ወይም “የታሪክ እና የጥበብ ውድ ሀብቶችን” ለማግኘት “መዝናናት ወይም መንሸራሸር” አስፈላጊ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

በተጨማሪም “በዓላት ጥሩ ጓደኝነት ለመመሥረት፣ ቦታዎችን፣ ልማዶችን፣ ብዙውን ጊዜ የማንቀርባቸውን ሰዎች ፍላጎት ለማወቅ፣ ለመተዋወቅና ለውይይት የሚበቁ አዳዲስ ሰዎችን የምናገኝበት ልዩ ጊዜ ነው” በማለት ተናግሯል።

ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ፥ መገናኘት እና ከሰዎች ጋር መወያየት ለዕረፍት አስፈላጊ ናቸው።

የእረፍት ጊዜያት የተረጋጋ ጊዜዎችን ለመኖር እድል የሚሰጡ ናቸው። በተራሮች ላይ የእረፍት ጊዜ ማሳለፍን የሚወዱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብዙውን ጊዜ እራሳቸውን ለማደስ ሰዎች መግባባት እና ከሌሎች ጋር የመገናኘት ደስታ እንደሚያስፈልጋቸው አጽንዖት ሰጥተው መናገራቸው ይታወሳል።

ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.አ.አ ሐምሌ 6 ቀን 1997 ዓ.ም በመልአከ ሰላም የጸሎት ወቅት እንደተናገሩት “ዕረፍት በእውነት እንዲህ እንዲሆን እና እውነተኛ ደህንነትን እንዲያስገኝ በእሱ ውስጥ አንድ ሰው ከራሱ ጋር፣ ከሌሎች ጋር፣ እንዲሁም ከአካባቢው ጋር ያለውን ጥሩ ሚዛን መገምገም ይኖርበታል” ሲሉ ተናግረው ነበር።

ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከእረፍት እሴቶች አንዱ” ከሌሎች ጋር መገናኘትና “ራስ ወዳድነት በጎደለው መንገድ፣ ለጓደኛ እና ለራስ ደስታ ጸጥ ያሉ ጊዜያትን በጋራ ለመካፈል” ጊዜ ማሳለፍ ነው ብለው መናገራቸውም ይታወሳል።

ስለ "የሰው ልጅ አእምሮ እና የሸማች ማህበረሰብ ተጽእኖዎች" በማስጠንቀቅ "ጤናማ እረፍት" በተለይም ለወጣቶች፣ ጊዜን እና ሃብትን “ማባከን” ለማስቀረት “በጤናዎ እና በሌሎች ላይ የሚደርሱ ጎጂ ጥቃቶችን በማስወገድ ጤናማ የእረፍት ጊዜያትን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ጋብዘው ነበር።

ቤኔዲክቶስ 16ኛ፡- በተፈጥሮ ውስጥ ሰው ራሱን እንደገና ያገኛል

ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ፣ በተፈጥሮ ውስጥ ራስን ማጥለቅ በጣም አስፈላጊ ነው፣ በተለይም “በከተማ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ለዝምታና ለማሰላሰል ትንሽ ቦታ በማይሰጥባቸው ከተሞች ውስጥ ለሚኖሩ” ሰዎች አስፈላጊ ነው ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

እ.አ.አ ሐምሌ 17 ቀን 2005 በሰሜናዊ ኢጣሊያ በአኦስታ ሸለቆ ተራሮች ውስጥ በሌስ ኮምብስ ውስጥ “ከተፈጥሮ ጋር ዘና ባለ ግንኙነት” “በአካልና በአእምሮ መሞላት አስፈላጊ መሆኑን” ገልጸው ነበር።

"በተጨማሪም እረፍት በራሳችን ቤተሰብ እና የምንወዳቸው ሰዎች ሰላማዊ አውድ ውስጥ የህይወትን ጥልቅ ትርጉም ለጸሎት ፣ ለማንበብ እና ለማሰላሰል የበለጠ ጊዜ የምንሰጥባቸው ቀናት ናቸው" ብለዋል ።

“የተፈጥሮን ቀስቃሽ አመለካከቶች፣ ሁሉም ሰው፣ ጎልማሶች ወይም ልጆች ሊደርሱበት የሚችለውን አስደናቂ 'መጽሐፍ' ሲመለከቱ፣ ሰዎች “ትክክለኛውን ገጽታቸውን እንደገና ማወቅ ይችላሉ ሲሉም አክለው ተናግረው ነበር።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ “እነሱ ፍጡራን እንደሆኑ ይገነዘባሉ፣ ነገር ግን ልዩ የሆነ ‘የእግዚአብሔር ችሎታ ያላቸው’፣ በውስጣቸው ለዘለዓለም ክፍት የሆኑ የእግዚአብሔር ፍጡር መገለጫ ናቸው' ሲሉ ተናግረዋል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በእረፍት ጊዜ የአንድን ሰው መንፈሳዊ ጉዞ ማጠናከር

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 2017 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቱሪስት መዳረሻዎች መካከል በሚጓዙበት ወቅት እረፍት ማድረግ መንፈሳዊ ጉዞን ለማጠንከር ጥሩ ጊዜ ሊሆኑ እንደሚችሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረው ነበር።"የበጋ ወቅት ጌታን የመፈለግ እና የመገናኘት ተግባራችንን የምናዳብርበት የዝግጅት ጊዜ ነው" ሲሉ አጽኖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በዚህ “በእረፍት ጊዜ እና ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መራቅ፣ የአካል እና የነፍስ ጥንካሬያችንን ማጠናከር እንችላለ" ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ምእመናን የእረፍት ጊዜያቸውን ለድንግል ማርያም በአደራ እንዲሰጡ “ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዲስማሙ፣ ክርስቶስ በሕይወታቸው ሁሉ ብርሃንና ኮከብ እንዲሆን” ራሳቸውን ክፍት እንዲያደርጉ አሳስበው ነበር።

“በእድሜ እክል፣ በጤና ወይም በሥራ ምክንያት፣ በኢኮኖሚ ገደብ ወይም በሌሎች ችግሮች ምክንያት ዕረፍት መውጣት የማይችሉትን ሰዎች የበጋው ወቅት፣ ጓደኞቻቸውን መገኘትና አስደሳች ጊዜዎች ማሳለፍ ይችሉ ዘንድ ልንደግፋቸው የገባል" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

 

09 Jul 2025, 16:42